www.maledatimes.com ፓርላማው በአስተዳደሩ የተነጠቀውን መሬት ለማስመለስ የጠቅላይ ሚኒስትሩን ድጋፍ አገኘ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ፓርላማው በአስተዳደሩ የተነጠቀውን መሬት ለማስመለስ የጠቅላይ ሚኒስትሩን ድጋፍ አገኘ

By   /   February 10, 2019  /   Comments Off on ፓርላማው በአስተዳደሩ የተነጠቀውን መሬት ለማስመለስ የጠቅላይ ሚኒስትሩን ድጋፍ አገኘ

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 47 Second

ፓርላማው በአስተዳደሩ የተነጠቀውን መሬት ለማስመለስ የጠቅላይ ሚኒስትሩን ድጋፍ አገኘ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ከፓርላማው አፈ ጉባዔ አቶ ታገሰ ጫፎ ጋር

በአቅራቢያው ተጨማሪ ቢሮ በ15 ሚሊዮን ብር ተከራየ

በቅርቡ ለዓመታት ታጥረው የቆዩ መሬቶችን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በወሰደው ዕርምጃ ሲያስመልስ አብሮ የተነጠቀው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የተወሰደበትን መሬት ለማስመለስ የጠቅላይ ሚኒስትሩን ድጋፍ ማግኘቱ ታወቀ፡፡

ሪፖርተር ከታማኝ ምንጮች ማወቅ እንደቻለው ጥር 24 ቀን 2011 ዓ.ም. ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው ሪፖርት ካቀረቡ በኋላ፣ ከአፈ ጉባዔው አቶ ታገሰ ጫፎ ጋር ምክር ቤቱ በተነጠቀው ቦታ ጉዳይ መጠነኛ ውይይት አድርገዋል፡፡ ለውይይቱ መነሻ የሆነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቀደም ብሎ ፓርላማው የአዲስ ሕንፃ ግንባታ ለማካሄድ ጀምሮት የነበረው እንቅስቃሴና  ዕቅዱ የት እንደ ደረሰ፣ ለአፈ ጉባዔው ጥያቄ በማንሳታቸው መሆኑን ምንጮች ጠቁመዋል፡፡

ቀድሞ የቤተ መንግሥት ጋራዥ ተብሎ ይታወቅ የነበረው ቦታ ላይ፣ ለፓርላማው አዲስ የጉባዔ አዳራሽን ጨምሮ ግዙፍ ሕንፃ ለመገንባት ታቅዶ እንደነበር ይታወሳል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጥያቄ ካቀረቡ በኋላ አፈ ጉባዔው የግንባታ ቦታውን የከተማ አስተዳደሩ የነጠቀው መሆኑን በመግለጽ እንዴት ሊገነባ ይቻላል ሲሉ ምላሽ መስጠታቸውን፣ በሥፍራው የነበሩ ምንጮች መስማታቸውን ገልጸዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በበኩላቸው የፓርላማ ቦታ መነጠቁን እንደማያውቁ ገልጸው፣ ፓርላማው መልሶ ተረክቦ ግንባታ መጀመር እንደሚችል ገልጸውላቸዋል ተብሏል፡፡

የተነጠቀው መሬት የሸራተንን ይዞታ ጨምሮ የቀድሞ እሪ በከንቱን ይዞ አራት ኪሎ ድረስ የሚገኙ ቦታዎችን መሀል ይገኛል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዕለቱ በምክር ቤቱ ቀርበው ባስረዱበት ወቅት፣ በቦታው አዲስ ፓርክ ለመገንባት የዲዛይንና የቅድመ ዝግጅት ሥራ እየተከናወነ መሆኑን ለፓርላማ አባላት ገልጸው እንደነበር ይታወሳል፡፡

ነገር ግን ቦታውን መልሰው መረከብ እንደሚችሉ ለአፈ ጉባዔው የገለጹበት ሁኔታ ቀደም ብለው ከጠቀሱት የፓርክ ዲዛይን ጋር ሊፋለስ እንደሚችል፣ ወይም ክለሳ እንዲደረግ ያስገድድ ወይም አያስገድድ የታወቀ ነገር የለም፡፡

በሥፍራው ይገነባል ስለተባለው ፓርክ የከተማዋ ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ (ኢንጂነር)፣ በተለይ ከሪፖርተር ጋር በነበራቸው ቃለ መጠየቅ ይህንኑ ማረጋገጣቸው ይታወሳል፡፡

ከጠቅላይ ሚኒስትሩና ከአፈ ጉባዔው ውይይት በኋላ ፓርላማው ወደ ከተማ አስተዳደሩ በመሄድ ጥያቄ ያቅርብ አያቀርብም የታወቀ ነገር የለም፡፡

ነገር ግን ሪፖርተር ያነጋገራቸው የጽሕፈት ቤት ሠራተኞች ግን፣ ፓርላማው የጠቅላይ ሚኒስትሩን ድጋፍ ካገኙና ወደ አስተዳደሩ የማይሄድበት ምክንያት የለም ሲሉ ገልጸዋል፡፡

በተጨማሪም ረቡዕ ጥር 29 ቀን 2011 ዓ.ም. በፀደቀው የፓርላማ ጽሕፈት ቤት አዋጅ መሠረት፣ የቴሌቪዥን ጣቢያ ለመጀመር እንቅስቃሴ ላይ የሚገኝ ቢሆንም የቦታ ጥበት አጋጥሞታል ብለዋል፡፡

እነዚሁ ምንጮች ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ፓርላማው በአቅራቢያው የሚገኝ ሕንፃ 15 ሚሊዮን ብር ከግል ባለሀብት ተከራይቷል፡፡

አዲስ የተከራየው ሕንፃም ከአርበኞች ሕንፃ ወደ አሮጌው ቄራ በሚወስደው መንገድ ላይ ሲሆን፣ ሐሙስ ጥር 30 ቀን 2011 ዓ.ም. ርክክብ ተፈጽሟል ተብሏል፡፡

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 6 years ago on February 10, 2019
  • By:
  • Last Modified: February 10, 2019 @ 12:19 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar