የመረጃ ዘጋቢ ወደ ለገጣፎ ያቀናው ዛሬ ማለዳ ከሌሎች ባልደረቦቹ ጋር ሲሆን በቦታው እንደደረሱ ፖሊሶች አፍሰዋቸው ወደ ፖሊስ ጣቢያ በር ላይ እንዳመጧቸው ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያመለክታል ።
ደብዳቢዎቹም በፖሊስ መኪና መጥተው ነው የደበደቧቸው ። ኢንስፔክተር ግርማ የከንቲባዋ ደጋፊ በመሆኑ ይህንን አይነት ህገ ወጥ ስራ የሰሩት ። አስር ሰዎች ከሶማሌ ተፈናቃይ የነበሩትን ሰብስበው ይዘው እንደመጡና ጋዜጠኞቹን ከበው እንደደበደቧቸው ገልጠዋል ። ነዋሪዎቹ አመራሮቹን ለምን መደብደብ አስፈለገ በለው በተደጋጋሚ ሲጠይቁ ኢሳት የተባለው የቴሌቪዝን ድርጅት «ዘርን ያማከለ ጥቃት እያደረሰ ስለሆነ ጋዜጠኞች መደብደብ አለባቸው ሲሉ አቶ ወርቁ ደጋግመው ሲናገሩ መስማታቸውን ገልጠዋል።»
ጋዜጠኞቹን ያፈኗቸው እና ያስደበደቡት ፖሊሶች ናቸው ያሉት እማኝ ምንጮቻችን ከተደብዳቢዎቹ አንዱ በዚህ ምስል ላይ የምትመለከቱት ፣ የጓደኛዬን ነው የምፈልገው እያለ ደሙ የፈሰሰ ሳለ ፣ ካሜራውን ቀምተውታል ፣ልጁን ወደ ጤና ጣቢያ ሲወስዱት በእግሩ እንደሆነ ገልጠዋል።
የለገጣፎ ዞእሮ አራት ሊቀመንበር የሆኑት ነጋሽ ወርቁ የውሸት ጋዜጠኞች ናቸው መጥተው እየዘገቡ ነው ያሉት ዘረኝነትን እና ጥላቻን እንጂ እውነተኛ መረጃን አይደለም የሚዘግቡት በማለት በሃገሪቱ ያሉትን የመገናኛ ብዙሃን አጥላልተዋል ። ትንሹ ትራምፕ ሲሏቸውም ነበር ።
ለገጣፎ ፖሊስ ጣቢያ በር ላይ ይሄው ጋዜጠኛ በአሁን ሰአት ከጓደኞቹ ጭምር ያለበት ሁኔታ ባይታወቅም የአካባቢው ነዋሪዎች በፖሊስ መኪና ትራንስፖርት አምጥታችሁ ካወራድችኋቸው በኋላ እንዴት እንዴት ይደበደባሉ ብለን ስንጠይቅ ዘረኝነትን እየዘገቡ ስለሆነ ይደበደባሉ በማለት ሊቀመንበሩ መልሷል ። ይህ የጋዜጠኝነትን ስነ ምግባር እና የመገናኛ ብዙሃንን ህልውና የሚጋፋ ከመሆኑም በላይ እኝህ የቀበሌ አስተዳደር (አቶ ነጋሽ ወርቁ) በህግ ሊጠየቁ ይገባል ፣የስም ማጥፋት ወንጀል በመገናኛ ብዙሃን ላይ መስርተዋል ሲሉ አንዳንድ ነዋሪዎች ጠቁመዋል።
Average Rating