www.maledatimes.com 157 ተሳፋሪዎችን ጭኖ ሲበር የነበረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በተነሳ በስድስት ደቂቃ ልዩነት ውስጥ ተከሰከሰ !! - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

157 ተሳፋሪዎችን ጭኖ ሲበር የነበረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በተነሳ በስድስት ደቂቃ ልዩነት ውስጥ ተከሰከሰ !!

By   /   March 10, 2019  /   Comments Off on 157 ተሳፋሪዎችን ጭኖ ሲበር የነበረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በተነሳ በስድስት ደቂቃ ልዩነት ውስጥ ተከሰከሰ !!

    Print       Email
0 0
Read Time:2 Minute, 21 Second

በበረራ ቁጥሩ ኢቲ 302 የተመዘገበና ንብረትነቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሆና 149 መንገደኞችንና 8 የበረራ ሰራተኞችን አሳፍሮ ዛሬ ጠዋት ከአዲስ አበባ ወደ ናይሮቢ ሲበር የነበረ ቦይንግ 737 አውሮፕላን ከቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ከጠዋቱ 2 ሰዓት ከ44 ደቂቃ ላይ ከተነሳ ከስድስት ደቂቃ በኋላ ግንኙነቱን ማቋረጡን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታወቋል።

አውሮፕላኑ ቢሾፍቱ አካባቢ የተከሰከሰ ሲሆን፥ የነፍስ አድን ስራ በመከናወን ላይ ይገኛል። በአደጋው ሙሉ በሙሉ ተሳፋሪዎቹ እና የበረራ አገልግሎት ሰራተኞቹ ህይወታቸው ማለፉን መረጃው ይጠቁማል ። እነደ አየር መንገዱ አመራር ገለጻ ከሆነ በረራውን በጀመረ በስድስት ደቂቃ ውስጥ የአደጋው ክስተት መፈጠሩን የጠቆሙ ሲሆን በበረራው ሰአት ፕሌኑ ችግር እንዳለበት እና ወደ ዋናው ሃብ ወይንም የበረራ ጣቢያ ለመመለስ ጥያቄ አቅርቦ በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ ከበረራ መስመር ውጭ እንደሆነ ገልጠዋል።

ዋናው አብራሪ እና እረዳት አብራሪው ጥሩ ብቃት ያላቸው መሆናቸውን ገልጠው ነገር ግን በአጭር ጊዜ ውስጥ የተገዛው ፕሌን የተከሰከሰበት ዋና ምክንያት ሊያውቁት እንዳልቻሉ ገልጠዋል ። ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ ከኢንዶኔዢያው ፕሌን ጋር ተመሳሳይ የሆነው ይሄው ፕሌን አወዳደቁም ተመሳሳይ እና አጭር ጊዜ ውስጥ ሲሆን ምናልባትም ከፋብሪካው ያልታወቀ እና ያልተጣራ ችግር ሊኖርበት ይችል እነሚችል ጥርጣሬ ውስጥ በጋዜጠኞች የተጠቆመ ስሆን ይህንን ምላሻቸውን አናውቀውም ገና በማጣራት ላይ ነን ሲሉ ገልጸዋል።

የአየር መንገዱ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞችም አደጋው ወደ ደረሰበት ስፍራ ማምራታት የሚቻላቸውን የአደጋ ጊዜ ስራ በማከናወን ላይ ይገኛሉ፡፡

ከአዲስ አበባ ወደ ናይሮቢ ሲበር የነበረው የኢትዮጵያ አየርመንገድ ቦይንግ 737 ላይ በደረሰው አደጋ የሁሉም 157 መንገደኞችና የበረራ ሰራተኞች ህይወት ማለፉ ታውቋል። ተሳፉሪዎቹ ከ33 ሀገራት የተውጣጡ መሆናቸውን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ገልጿል።
ከሞቱት ውስጥ 32 ኬንያውያን፣ 9 ኢትዮጵያውያን፣ 8 ቻይናውያን እና 11 የሚሆኑ የመንግስታቱ ድርጅት የስራ ባልደረቦች ይገኙበታል።

Image may contain: sky, cloud, mountain, outdoor and nature

ዛሬ ማለዳ የመከስከስ አደጋ የደረሰበትን፣ ተሳፋሪዎቹንና የበረራ አስተናጋጆቹን በሙሉ ህይወት የቀጠፈውን ቦይንግ 737 አውሮፕላን ሲያበሩ የነበሩት በትውልድ ኢትዮጵያዊና በዜግነት ኬንያዊ የሆነው ካፒቴን ያሬድ ሙሉጌታና ረዳት አብራሪው አህመድ ኑር ሙሐመድ ኑር ነበሩ። ሁለቱም ጥሩ ብቃት የነበራቸውን አብራሪዎች መሆናቸውን አየር መንገዱ ገልፇል።
አደጋ የደረሰበት አውሮፕላን በቅርብ የተገዛና ዛሬ ማለዳ ከደቡብ አፍሪካ ጆሀንስበርግ የገባ ነበር።

የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈፃሚ ኣይተ ተወልደ ገብረማርያም የአውሮፕላን አደጋው በደረሰበት ስፍራ

Image may contain: one or more people, people standing, mountain, outdoor and nature

Image may contain: 1 person, smiling

Image may contain: 1 person, smiling

ዋናው አብራሪ ያሬድ

Image may contain: 1 person, smiling, closeup
ረዳት አብራሪ አህመድኑር ሞሃመድ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ኢቲ 302 ቦይንግ 737 አውሮፕላን ዛሬ ማለዳ ባጋጠው የመከስከስ አደጋ ህይወታቸውን ያጡ የ33 ሃገራት ዜጎች :
32 ኬንያውያን 🇰🇪 
18 ካናዳውያን 🇨🇦 
17 ኢትዮጵያውያን 🇪🇹 
8 ጣሊያናውያን 🇮🇹 
8 ቻይናውያን 🇨🇳 
8 አሜሪካውያን 🇺🇸 
7 ብሪታኒያውያን 🏴󠁧󠁢󠁥󠁮󠁧󠁿 
7 ፈረንሳውያን 🇫🇷 
6 ገብፃውያን 🇪🇬 
5 ሆላንዳውያን 🇳🇱 
4 የመንግስታቱን ድርጅት ፓስፖርት የያዙ 
4 ህንዳውያን 🇮🇳
4 ስሎቫኪያውያን 🇸🇰 
3 ኦስትሪያዊያን🇦🇹 
3 ስዊድናውያን 🇸🇪 
3 ራሻውያን🇷🇺 
2 ሞሮኳውያን 🇲🇦
2 ስፔናውያን 🇪🇸 
2 ፖላንዳውያን 🇵🇱 
2 እስራኤላውያን 🇮🇱 
1 ቤልጂዬም 🇧🇪 
1 ኢንዶኔዠያ 🇮🇩 
1 ኡጋንዳ 🇺🇬 
1 የመን 🇾🇪 
1 ሱዳን 🇸🇩 
1 ሰርቢያ 🇷🇸 
1 ቶጎ 🇹🇬 
1 ሞዛምቢክ 🇲🇿 
1 ሩዋንዳ 🇷🇼 
1 ሶማሊያ 🇸🇴 
1 ኖርዌይ 🇳🇴 
1 አየርላንድ🇮🇪 
1 ሳዑዲ አረቢያ 🇸🇦

የሁሉንም ነፍስ በእግዚአብሄር እጅ ያሳርፍ ፣ ለቤተሰቦቻቸው መጽናናትን እንለምናለን እንመኛለንም !! ማለዳ ታይምስ ሚዲያ ግሩፕ

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 6 years ago on March 10, 2019
  • By:
  • Last Modified: March 10, 2019 @ 10:31 am
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar