www.maledatimes.com የትግራይ መንግሥት በአማራ ላይ አፈሙዝ የማዞርበት ምክንያት የለኝም አለ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የትግራይ መንግሥት በአማራ ላይ አፈሙዝ የማዞርበት ምክንያት የለኝም አለ

By   /   March 16, 2019  /   Comments Off on የትግራይ መንግሥት በአማራ ላይ አፈሙዝ የማዞርበት ምክንያት የለኝም አለ

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 34 Second

የትግራይ ሕዝብና መንግሥት በወንድሙ የአማራ ሕዝብ ላይ አፈሙዝ የሚያዞርበትና ጦርነት የሚገጥምበት ምንም ምክንያት እንደሌለው የክልሉ የሕዝብ ግንኙነትና የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ገለጸ። የአማራ ክልል ምክር ቤት በአማራና በትግራይ መካከል ጦርነት ለመክፈት የሚሰሩ ወገኖችን ማስጠንቀቁ ይታወሳል።

በአማራና በትግራይ ሕዝቦች መካከል ጦርነትን ለመቀስቀስ የሚሰሩ የቀድሞ አመራሮች አሉ ያለው የአማራ ክልል ምክር ቤት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ማስጠንቀቁ ይታወቃል። ሰሞኑን ለጉባኤ የተሰበሰበው ምክር ቤቱ ያሳለፈውን ውሳኔ አስመልክቶ መግለጫ የሰጡት የክልሉ መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ዳይሬክተር አሰማኸኝ አስረስ የኹለቱ ክልል ሕዝብ ችግርና ደስታን ለዘመናት በጋራ ያሳለፈ ነው ብለዋል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን በኹለቱ ክልሎች መካከል እርስ በእርስ ከመጠራጠር አልፎ የደኅንነት ስጋት መፈጠሩም በተደጋጋሚ እየተገለጸ ነው። አሰማኸኝ ‹‹ከትግራይ ክልል አመራሮች በኩል የጦርነት ቅስቀሳዎች፣ ሰፊ ወታደራዊ ዝግጅት፣ ወደ አማራ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች ሠራዊት የማቅረብና አንዳንድ ፀብ አጫሪ አካሔዶች በአስቸኳይ እንዲቆሙ፣ ከዚህ ድርጊታቸውም እንዲቆጠቡ ምክር ቤቱ አፅንኦት ሰጥቶ አሳስቧል።›› ሲሉ ተደምጠዋል።

ዋና ዳይሬክተሩ ‹‹ከዚህ አልፎ በትግራይ ክልል የመሸገው በተለይ በለውጡ የተገፋው ሥልጣኑን ያጣው ዘራፊው ቡድን የመቀሌው ቡድን ጦርነት ለመለኮስ ወይም ግጭት ለመፍጠር ቢፈልግ እንኳን ሰላም ወዳዱ የትግራይ ሕዝብ ዝም ብሎ ይመለከተዋል ብለን አናምንም። ምክንያቱም ከጦርነት የሚገኝ ምንም ነገር ስለሌለ።›› ሲሉም አክለዋል።

በአማራ ክልል በኩል የሚደረጉ ግጭት የሚያጭሩ የጥላቻ ንግግሮች፣ የትግራይን ሕዝብ ለስጋት የሚጥሉ ትንኮሳዎች ማድረግ እንደማይቻልም ምክር ቤቱ መወሰኑን የተናገሩት አሰማኸኝ፣ ይህንን ተላልፎ ወንድምና እህት የሆነውን የትግራይ ሕዝብ ለስጋት የሚጥል የጥላቻ ንግግር፣ በሚያደርግ ማንኛውም አካል ላይ የእርምት እርምጃ እንዲወሰድም ምክር ቤቱ ውሳኔ ማሳለፉን አሳውቀዋል።

ይህን ተከትሎ ሐሙስ የካቲት 28 መግለጫ የሰጠው የትግራይ ክልል መንግሥት የትግራይና አማራ ሕዝብ በጋራ ሆነው ለነፃነት መታገላቸውንና የሚጋሩት በርካታ ነገር መኖሩን በማስታወስ ‹‹የትግራይ ሕዝብና መንግሥት የታገሉለትን ሕዝባዊ መስመር አንግበው ወደ ፊት ከመገስገስ ውጭ በወንድም የአማራ ሕዝብ ላይ አፈሙዝ የሚያዞርበት አንዳች ምክንያት የላቸውም›› ብሏል።

የትግራይ ክልል መንግሥት አክሎም ላለፉት ሦስት ዓመታት ‹‹ሽፍቶችን ጨምሮ የተለያየ ፀረ ሰላምና ፀረ ልማት ኃይሎች የተለያዩ የሚዲያ አማራጮችን ተጠቅመው በትግራይ ላይ የጦርነት ቅስቀሳና ትንኩሳ ሲደረግበት እንደነበርና በትግራይ ወሰኖችም ሔድ መለስ ሲሉ ቆይተዋል›› ሲል ወቅሷል። ይሁንና የትግራይ ጠላት ድኽነት ስለሆነ ጦርነቱ ድኽነትን ለማሸነፍ ነው ያለው የክልሉ መንግሥት ማንኛውም ሰላም ወዳድ ዜጋ ስጋት ሊገባው አይገባምም ብሏል።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 6 years ago on March 16, 2019
  • By:
  • Last Modified: March 16, 2019 @ 8:05 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar