www.maledatimes.com የሚዲያ ሕግ ጥናት ቡድን የሕጎችን ችግሮች ለየ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የሚዲያ ሕግ ጥናት ቡድን የሕጎችን ችግሮች ለየ

By   /   March 16, 2019  /   Comments Off on የሚዲያ ሕግ ጥናት ቡድን የሕጎችን ችግሮች ለየ

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 32 Second

በጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ሥር የሕግና የፍትሕ ጉዳዮች አማካሪ ጉባዔ፣ የሚዲያ ሕግ የጥናት ቡድን የሚዲያ ሕጎች ችግሮችን በመለየት ሪቂቅ ሪፖርት አዘጋጀ፡፡

በ15 አባላት የተዋቀረው ቡድን፣ ዋነኞቹ የሚዲያ ሐጎች በይዘታቸውም ሆነ በአተገባበራቸው በዘርፉ ተዋንያን ላይ ከፍተኛ ጫና መፍጠራቸውንና ዘርፉም እንዲዳከም አስተዋጽኦ ያደረጉ መሆኑን መረጋገጡን የገለጸ ሲሆን፣ ‹‹በአገራችን ሐሳብን የመግለጽ መብት ላይ በሕግ የተጣሉ ገደቦችን ስናይ፣ ገደቦቹ ኢትዮጵያ ካፀደቀቻቸው ስምምነቶች፣ ከሕገ መንግሥቱ ድንጋጌዎችና ከሌሎች አገሮች ልምድና ተሞክሮ አንፃር ሲታይ መብቱን ከማክበር፣ ከመተግበርና ከማስቻል ይልቅ ቁጥጥር ላይ ያተኮሩና አሉታዊ ውጤት እንደነበራቸው ማየት ተችሏል፤›› ሲልም ይገመግማል፡፡

በዚህም መሠረት፣ ‹‹የሚዲያ ተቋማት ገለልተኛ፣ ተፅዕኖ ፈጣሪና ሞጋች መሆን አልቻሉም፤›› ብሏል፡፡

በዋናነት የመገናኛ ብዙኃንና የመረጃ ደኅንነት አዋጅ የብሮድካስቲንግ አገልግሎት አዋጅና የኮምፒዩተር ወንጀል አዋጆችን የገመገመው ቡድኑ፣ በተጓዳኝ የወንጀል ሕጉን፣ የፀረ ሽብርተኝነትና የማስታወቂያ አዋጆችን የተመለከተ ጥናት ማድረጉን ያሠራጨው ረቂቅ ሰነድ ያስረዳል፡፡

ለሕጎቹ መመዘኛነት ዓለም አቀፋዊና አኅጉራዊ የሰብዓዊ መብቶች ድንጋጌዎችና የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥታትን የተጠቀመ ሲሆን፣ ሕጎቹን አንቀጽ ገምግሟል፡፡  

የመገናኛ ብዙኃን የመረጃ ነፃነት አዋጅን በተመለከተ በአንቀጽ 5 የሚዲያ ሥራዎች ለአገር ውስጥ ባለሀብቶች ብቻ የተገደቡ መሆናቸው፣ እንደ አስፈላጊ ክልከላ ሊቆጠር የሚችል እንደሆነና የትውልደ ኢትዮጵያዊያንን ሚና የገደለ እንደሆነ ተጠቅሷል፡፡

በተመሳሳይ ተደራራቢ የሚዲያ ባለቤትነትን የሚነደግገው አንቀጽ 7 ዘርፉን ማዳከሙ፣ አንድ ግለሰብ ብቻውን የመገናኛ ብዙኃን ሊያቋቋም የሚችልበት አሠራር በመቅረቱ ፕሬስን ለማስፋፋት እንቅፋት መሆኑና በተመሳሳይ ስያሜ የሚታተሙ መጽሔትና ጋዜጣ ባለቤት መሆን አለመቻሉ በዘርፉ ዕድገት ላይ እንቅፋት መፍጠሩን በረቂቅ ሪፖርቱ ተገልጿል፡፡

የመረጃ ነፃነትን የተመለከቱ ድንጋጌዎች፣ ምዝገባና ፈቃድን የተመለከቱ ድንጋጌዎችና የተቆጣጣሪ ተቋማት ገለልተኛነትን በተመለከተ ሊስተካከሉ የሚገባቸውን ችግሮች ተነቅሰው ቀርበዋል፡፡

ለአዋጁ የማስፈጸሚያ ደንቦችና መመርያዎች አለመኖር፣ የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያዎች አመዳደብና አድሏዊ አሠራር መኖርና መረጃ የመስጠት መብትን ለማረጋገጥ አስገዳጅ ሥርዓት አለመኖር፣ የመገናኛ ብዙኃን የመረጃ ነፃነት አዋጅ ለማስፈጸም አዳጋች ማድረጋቸውን ሰነዱ ያስረዳል፡፡

የብሮድካስቲንግ አገልግሎት አዋጅን በሚመለከት የብሮድካስቲንግ ባለሥልጣን ገለልተኛ አለመሆን፣ የአገልግሎት ፈቃድ ለይዘት ክትትልና ቁጥጥር የሚጋብዝ መሆኑን፣ በዝርዝር ያልተተረጎሙ የክልከላ ድንጋጌዎች ላልተገባ ቁጥጥርና ጫና ለማድረግ የተጋለጡ መሆናቸው ተመልክቷል፡፡

ይኼንን ግምገማ ተከትሎ አዋጆቹን የማስተካከልና የማሻሻል ሥራ ከሰፋፊ ውይይቶች በኋላ ይከተላል ተብሏል፡፡ ቅዳሜ መጋቢት 7 ቀን 2011 ዓ.ም. በረቂቅ ሪፖርቱ ላይ በኢሊሌ ሆቴል የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ውይይት አድርገዋል፡፡  

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 6 years ago on March 16, 2019
  • By:
  • Last Modified: March 16, 2019 @ 8:42 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar