አንድ መቶ አምሳ ሰባት ተሳፋሪውቾችን አሳፍሮ ወደ ኬንያ ያቀና የነበረው አውሮፕላን በቢሾፍቱ ከስድስት ደቂቃ በረራ በኋላ መውደቁ የተነገረ በአለም ላይ አስደንጋጭ ዜና ነበር።
ሰባት ሰላሳ ሰባት ማክስ 8 -9 የተሰኙት ነዳጅ ቆጣቢ አውሮፕላኖች በውስጣቸው በሚሊዮን የሚቆጠሩ የኮምፒዩተር ፕሮግራም ወይንም ኮድ ሚስጥራዊ ቁጥር የተሞላ ዘመናዊ እና ቴክኖሎጂን ያዋቀረ አውሮፕላን መሆኑ ተነግሮለታል ፣ ይህ አውሮፕላን በፋብሪካው ተሰርቶ ከወጣ ጊዜ ጀምሮ ሁለት ግዙፍ አውሮፕላኖቹ በጣም በአጭር ጊዜያት ውስጥ መውደቃቸው እና የብዙ ዜጎች ህይወት መጥፋቱን አለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ሲገልጹ መክረማቸው ይታወቃል።
በአውሮፕላኑ የመቆለፊያ ዘለበት( lock knob) ከተሰኘው ችግር ውጭ፡ብዙ የኮፕምዩተር፡ፕሮግራም፡ስህተት፡እንዳለበት፡እና፡በበረራ፡ወቅት፡በፍጥነጥ አፍጫውን ወደ ሰማይ በማሾል ወይንም ወደ መሬት በማቆልቆል እራሱን የሚወረውር ሃይል እንዳለው በተለያዩ አለም አቀፍ የመረጃ ተቋማት ሳምንቱን ሙሉ ሲዘገብ ከርሟል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ከኢትዮጵያ አውሮፕላን በረራ መከስከስ በኋላ የአሜሪካው ፕረዚደንት ዶናልድ ትራምፕ በአስቸኳይ የቦይንግ 737 max 8 እና 9 ከአገልግሎታቸው እንዲቆሙ እና አስፈላጊው ምርመራ ተደርጎ ፣ ችግሮቻቸው ተፈቶ ወደ ስራ የሚመለሱበትን አስቸኳይ አዋጅ ማውጣታቸው ይታወሳል። 737 የበረራ ክልከላም መደረጉን ተደገልጿል::
በዚህ ባሳለፍነው ሳምንት ፋክስ ቢዝነስ አለም አቀፍ የዜና አውታር ስለ ቦይንግ ካምፓኒ የንግድ ክስረት ሃያ አምስት ቢሊዮን ደላርስ እንደደረሰበት የተገለጸ ሲሆን ፣ 5100 737 ማክስ 8-9 በአጭር ጊዜ መሸጣቸው የተገለጸ ሲሆን ፣ በዚህ አደጋ የስቶክ ማርኬት ኤክስቸንጅ 10% ዋጋው በአንድ ጊዜ እንደወደቀበት ፋክስ ገልጿል።
በዛሬው እለት በጋራ የተቀበሩት የአየር መንገዱ ሰራተኞች እና ተሳፋሪዎች በጸባኦት ቅድስት ስላሴ መካነ መቃብር ሲሆን ፣ የተጓዦቹን አስም በማቃጠል አመድ ለቤተሰቦቻቸው እንደተሰጠ እና ባዶ ሳጥን በማረፊያ ክፍል ውስጥ መቀመጡን አለም አቀፍ መረጃ ማእከሎች እየዘገቡት ይገኛሉ ። ብዙሃንን ያሳዘነው የዚህ አየር መንገድ በረራ
በዛሬው እለት እየሩሳሌም ፖስት የተሰኘው ጋዜጣ ደግሞ በአሳተመው ጋዜጣ
የሟቾች ንብረቶች በአካባቢው ነዋሪዎች መዘረፋቸው እንዳሳዘናቸው ገልፀው፤ የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚንስትር ወደ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ በመደወል ለጉዳዩ መፍትሄ እንዲሰጠው ቢጠይቁም ቀና መልስ እንዳላገኙ ታውቋል ሲል ጄሩሳሌም ፖስት ዘግቧል። ለበለጠ መረጃ ከስር ሊንኩን ይጫኑት
ይህ በእንዲህ እንዳለ ከዘሃበሻ ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው ከሆነ ለተከሰከሰው አውሮፕላን ዛሬ የሰማናቸው 5 መረጃዎች!
1. በዛሬው እለት የ17ቱ ኢትዮጵያዊያን የቀብር ስነስርአት በቅድስት ስላሴ ቤተክርስቲያን ተከናውኗል፡፡ አሶሺየትድ ፕሬስ እንደዘገበው እነዚህ 17ቱ ባዶ የአስከሬን ሳጥኖች ከአየር ማረፊያው በሰንደቅ አላማ ተሸፍነው ሲሸኙ በሺህ የሚቆጠር ህዝብ ተገኝቶ ነበር፡፡
2. አየር መንገዱ ለሟች ቤተሰቦች አደጋው ከደረሰበት ቦታ ላይ የተዘገነ አንድ ኪሎ አፈር እንደሰጠም የዜና ምንጩ ዘግቧል፡፡
3. ቢቢሲ እንደዘገበው ደግሞ የሟች ቤተሰቦች በአዲስ አበባ ወይም በማንኛውም አገር በሚገኝ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሽያጭ ቢሮ በመገኘት የዲኤንኤ ሳምፕል መስጠት እንደሚችሉ አስታውቋል፡፡
4. ኬንያ በአውሮፕላን አደጋው የሞቱብኝ ዜጎቼ ቁጥር 36 ነው አለች፡፡ ከዚህ ቀደም የሞቱት 32 እንደነበሩ የተገለፀ ሲሆን በኢትዮጵያ ምክትል የኬንያ አምባሳደር የሆኑት ጆርጅ ኦሪና ግን ዛሬ በሰጡት መግለጫ ‹‹አራቱ ዜጎቻችን የተጓዙት በሌላ አገር ፓስፖርት ስለሆነ ነው›› ብለው ቁጥሩ እንዲስተካከል ጠይቀዋል፡፡
5. ዴይሊ ኔሽን የተሰኘው የኬንያ ጋዜጣ በዛሬ እትሙ የሟች ቤተሰቦች እያንዳንዳቸው የ170 ሺህ ዶላር ካሳ እንደሚሰጣቸው ዘግቧል፡፡ በሞንትሪያል ኮንቬንሽን መሰረት አንድ ሰው በአውሮፕላን በረራ ላይ እያለ ለህልፈት ከተዳረገም ሆነ ጉዳት ከደረሰበት የሚሰጠው ካሳ መነሻ የ170 ሺህ ዶላር መሆኑንም ጋዜጣው አስታውቋል፡፡
Average Rating