www.maledatimes.com የቡራዩ አዳሪ ትምህርት ቤት ግንባታ ቢዘገይም የበጀቱ ግማሽ ተከፍሏል - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የቡራዩ አዳሪ ትምህርት ቤት ግንባታ ቢዘገይም የበጀቱ ግማሽ ተከፍሏል

By   /   March 23, 2019  /   Comments Off on የቡራዩ አዳሪ ትምህርት ቤት ግንባታ ቢዘገይም የበጀቱ ግማሽ ተከፍሏል

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 30 Second

• በከተማዋ የነበረው አለመረጋጋት ግንባታው እንዲዘገይ አድርጓል ተብሏል

ኅዳር 2011 መጠናቀቅ የነበረበት የቡራዩ አዳሪ ትምህርት ቤት የመጀመሪያውን ዙር ግንባታን ለማከናወን የሚያስፈልገው 700 ሚሊዮን ብር ሙሉ ወጪ ቢከፈልም የተጠናቀቀው ግንባታ 45 በመቶ ብቻ መሆኑ ታወቀ።

የአዳሪ ትምህርት ቤቱ ግንባታ በኹለት ምዕራፎች ይከናወናል በሚል በመንግሥት ከአንድ ነጥብ አራት እስከ አንድ ነጥብ አምስት ቢሊዮን ብር የተመደበለት ነበር፡፡ ልዩ ችሎታ ያላቸውን ተማሪዎች ከመላ አገሪቱ በመመልመል እንዲያስተምር ታስቦ በቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለ ማሪያም ደሳለኝ የሥልጣን ዘመን በሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚንስቴር አስተባባሪነት ግንባታው የተጀመረው ትምህርት ቤቱ የመጀመሪያው ዙር የማሰልጠኛ ተቋም ግንባታ 50 በመቶ እንኳን በተያዘለት ጊዜ ማጠናቀቅ አልቻለም።

ግንባታው በዚህ ዓመት እንደሚጠናቀቅ ታቅዶ የነበረ ቢሆንም ባለመሳካቱ የማጠናቀቂያ እቅዱ ወደሚቀጥለው ዓመት እንዲዛወር ሆኗል፡፡ ግንባታው በጊዜው እንዳይገባደድ ምክንያት የሆነው ደግሞ ትምህርት ቤቱ በሚገነባባት ቡራዩ ከተማዋ ባለፉት ዓመታት በነበረባት ሁከትና ብጥብጥ ነው ተብሏል።
ይህም ግንባታው በተያዘለት ጊዜ እና በተመደበለት ወጪ እንዳይጠናቀቅ ማድረጉን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚንስቴር የሚዲያና ፕረስ ዳይሬክተሩ ተስፋዬ አለምነው ለአዲስ ማለዳ አሳውቀዋል።

በአፍሪካም ሆነ በኢንኩቤሽን ማዕከል የመጀመሪያው እንደሚሆን እና ሀገሪቱን በቴክኖሎጂ የተሻለ ደረጃ እንድታድግ እድሉን ይፈጥራል በማለት በኦሮምያ ክልል ቡራዩ ከተማ ውስጥ እየተገነባ ያለው አዳሪ ትምርት ቤት በሀገሪቱ ልዩ ተሰጦና ችሎታ ያላቸውን ወጣቶች በመመልመል ሥራቸውን ለማጠናከር እና ሀሳባቸውን ወደ ተግባር ለውጦ አገልግሎት ላይ ለማዋል በማለም ወደ ግንባታ የገባ መሆኑ ይታወቃል። በዚህም በሚኒስቴሩ ስር እየተገነባ ያለውና የኢንኩቤሽን ማዕከል ይሆናል በሚል ብዙ ተስፋ የተጣለበት አዳሪ ትምህርት ቤቱ ችሎታና ተሰጥዖው ያላቸውን ኢትጵያዊያን ታዳጊዎች በማገዝ በዓለም ዐቀፍ መድረኮችም ጭምር ተወዳዳሪ እንዲሆኑ የማድረግን ራዕይ አንግቧል።

ከትምህርት ቤቱ ጋር አብሮ የሚገነባው የማሰልጠኛ ማዕከሉም ሁለገብ ተቋም ሲሆን እስከ አንድ ሺሕ የሚሆኑ ሰልጣኞችን ይይዛል ተብሎ ይታሰባል። በውስጡም የቦርድ ክፍሎች፣ ቢሮዎች፣ ዘመናዊ ቤተ መጻሕፍት፣ ክሊኒክ እንዲሁም የተማሪዎች ማደሪያና ቤተ ሙከራዎችን የሚያካትት ሲሆን የኹለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ ተማሪዎችን እና በየአካባቢው የሚገኙ የልዩ ችሎታ ባለቤት ወጣቶች በይበልጥ ያሳተፈ ይሆናልም በሚልም ነበር የግናባታ እቅዱ የወጣው።

የቡራዩ አዳሪ ትምርት ቤት ግንባታው የተጀመረው በ2009 ሲሆን፣ ከቡራዩ ከተማ አስተዳደር በተገኘ አምስት ሺሕ ካሬ ሜትር ላይ የሚገነባ ነው፡፡ የማሰልጠኛ ተቋሙ ግንባታም በተክለ ብርሀን አምባዬ ከንስትራክሽን እየተካሄደ ይገኛል።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 6 years ago on March 23, 2019
  • By:
  • Last Modified: March 23, 2019 @ 10:00 am
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar