www.maledatimes.com ኢዴፓ የፓርቲው አርማና ሥም ቅርሶች ሆነው እንዲቀመጡለት ወሰነ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ኢዴፓ የፓርቲው አርማና ሥም ቅርሶች ሆነው እንዲቀመጡለት ወሰነ

By   /   March 23, 2019  /   Comments Off on ኢዴፓ የፓርቲው አርማና ሥም ቅርሶች ሆነው እንዲቀመጡለት ወሰነ

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 31 Second

የኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) ከሌሎች የፖለቲካ ኃይሎች ጋር ውኅደት ከፈጸመ በኋላ ኢዴፓ የሚለው መጠሪያ፣ የፓርቲው አርማና ሌጋሲዎች ለሌላ ወገን እንዳይተላለፉና ለታሪክ ቋሚ ቅርሶች ሆነው እንዲቀመጡ ወሰነ።

ኢዴፓ ኹለተኛ ልዩ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤውን መጋቢት 1/2011 በራስ ሆቴል የስብሰባ አዳራሽ ከመላው አገሪቱ የተገኙ የጠቅላላ ጉባኤ አባላት በተገኙበት አካሄዷል።

በእለቱም የጠቅላላ ጉባኤ አባላት በአጀንዳነት የተወያዩበት ‹‹ኢዴፓ ከሰማያዊ ፓርቲ፣ ከአርበኞች ግንቦት ሰባት፣ ከመላው ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (መኢዴፓ) እና ከሌሎችም ፍላጎት ካላቸው ፓርቲዎች ጋር ሊያደርገው ስላሰበው ውኅደት ጉባኤው ተነጋግሮ መወሰንና አቅጣጫ ማስቀመጥ›› የሚል ነበር።
በጉባኤው ላይ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጽሕፈት ቤት ተወካይ በታዛቢነት በመገኘት ምልዐተ ጉባኤው መሟላቱን ጨምሮ ውሳኔዎች ዴሞክራሲያዊና ሁሉን አሳታፊ በሆነ መንገድ ስለመካሔዳቸው ተከታትሏልም ተብሏል።

የፓርቲው ሊቀመንበር ጫኔ ከበደ (ዶ/ር)፣ ፓርቲው በውኅደት ሊቀላቀላቸው ካሰባቸው የፖለቲካ ኃይሎች ጋር በተያያዘ የጉባኤ አባላት በቂ ውይይት ተደርጎ በውኅደቱ አስፈላጊነት ላይ ሙሉ ስምምነት መደረሱን ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።

ለውኅደቱ እውን መሆን መከወን ያለባቸው ተግባራት መጠናቀቃቸውን የኢዴፓ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ሲያረጋግጥ ሌላ ተጨማሪ ጉባኤ መጥራት ሳያስፈልግ ውኅደቱን ተከታትሎ እንዲያስፈጽም ጉባዔተኛው የጉባዔውን ሙሉ ውክልና ለሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው በሙሉ ድምጽ በመወሰን መስጠቱንም ጫኔ ገልጸዋል።
ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው፣ የሚመሰረተው አዲሱ ውኅድ ፓርቲ ኢዴፓ ሲታገልላቸው ነበር የተባሉትን ኅብረ ብሔራዊነት፣ ምክንያታዊነት፣ አገራዊ አንድነትን ማስጠበቅ የሚሉ መሰረታዊ መርሆዎች የሚያስጠብቅ የአገር ዐቀፍ ፓርቲ አደረጃጀት ይዞ የሚቋቋም መሆኑን ማረጋገጡን ገልጿል።

ውኅደቱ የፓርቲውንና የአባላቱን ውኅደትና መሰረታዊ ጥቅም ባስጠበቀ መልኩ መከናወኑን ሲያረጋግጥ፣ ውኅደቱ ከወረዳ ጀምሮ የሚካሄድና የባለፉትን ስህተቶች በማይደግም መልኩ የሚጠናቀቅ መሆኑን እንደሚያረጋግጥም ፓርቲው አሳውቋል።

ጠቅላላ ጉባኤው የሰየመውና ሦስት አባላት ያሉት ኮሚቴ፣ የፓርቲውን የሚንቀሳቀሱም ሆነ የማይንቀሳቀሱ ንብረቶች ኦዲት አድርጎ ለሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው ሪፖርቱን አቅርቦ ሲያጠናቅቅ ውኅደቱን ሙሉ በሙሉ እንዲያስፈጽም በእለቱ የተገኙት የጠቅላላ ጉባኤ አባላት በሙሉ ድምጽ ወስነዋል።

በተጨማሪም፣ በጉባኤው ፓርቲው እየተጠቀመበት ያለው ‹‹ኢዴፓ›› የሚለው መጠሪያ ስም የፓርቲው አርማና ሌጋሲዎች ከውኅደቱ በኋላ ለሌላ የማይተላለፉ ይልቁንም ለታሪክ ቋሚ ቅርሶች ሆነው እንዲቀመጡ ተወስኗል። በፓርቲው ስም የተመዘገቡ የሚንቀሳቀሱም ሆነ የማይንቀሳቀሱ ንብረቶች በዚህ ጉባኤ በተቋቋመው ኮሚቴ ተቆጥረው ከተጠናቀቁ በኋላ የሚመሰረተው አዲሱ ውኅድ ፓርቲ ንብረቶች ሆነው እንዲያገለግሉም የጉባኤው አባላት በሙሉ ድምጽ ወስነው መውጣታቸውን ሊቀመንበሩ ጫኔ ለአዲስ ማለዳ አሳውቀዋል።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 6 years ago on March 23, 2019
  • By:
  • Last Modified: March 23, 2019 @ 10:06 am
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar