www.maledatimes.com በጌዲኦ የተፈናቃዮች ሰብኣዊ ቀውስ ሕዝቡን አስቆጣ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

በጌዲኦ የተፈናቃዮች ሰብኣዊ ቀውስ ሕዝቡን አስቆጣ

By   /   March 23, 2019  /   Comments Off on በጌዲኦ የተፈናቃዮች ሰብኣዊ ቀውስ ሕዝቡን አስቆጣ

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 58 Second

• ኮሚሽኑ ድጋፍ እንዳደርግ የተጠየኩት መጋቢት 1 ነው ብሏል

ከኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ጉጂ የተፈናቀሉ የጌዲኦ ተወላጆች ላይ የደረሰው የሰብኣዊ ቀውስ መንግሥት ትኩረት ነፍጎታል በሚል ሕዝቡን አስቆጣ። የብሔራዊ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን በግጭት ምክንያት በቅርቡ ለተፈናቀሉ 54 ሺሕ በላይ ዜጎች ድጋፍ እንዳደርግ የተጠየኩት መጋቢት 1/2011 ነው ብሏል።

ከወራት በፊት በኦሮሚያ ምዕራብ ጉጂና በደቡብ ጌዲኦ አዋሳኝ አካባቢዎች በተፈጠረ ግጭት ከ600 ሺሕ በላይ ኢትዮጵያዊያን መፈናቀላቸው ይታወሳል። ግጭቱን ተከትሎ ተፈናቃዮችን ወደ ቀያቸው ለመመለስና መልሶ ለማቋቋም በተደረገው ውይይትና የማግባባት ሥራ አብዛኞቹን መመለስ ስለመቻሉም ሪፖርች ያመለክታሉ።

ይሁንና በቅርቡ እንደአዲስ ባጋጠመ አለመረጋጋት የጌዲኦ ተወላጆች ከጉጂ ተፈናቅለው ወደ ደቡብ ክልል መሔዳቸው ይታወቃል። ሆኖም በቅርቡ የተፈናቀሉት ወገኖች የሰብኣዊ ድጋፍ ተነፍጓቸዋል፤ መንግሥትም ትኩረት አልሰጣቸውም በሚል በተለይም በማኅበራዊ የመገናኛ አውታሮች ሰዎች ቁጣቸውን ሲገልፁ ሰንብተዋል። ከተፈናቃዮቹ መካካልም ህፃናትንና አራስ እናቶችን ጨምሮ የከፋ ችግር ተጋርጦባቸውና የምግብ እጦቱም ወደ ከፋ ረሃብ እየተሻገረባቸው መሆኑን የሚያሳዩ መረጃዎች በፎቶ ግራፍም ጭምር በማኅበራዊ መገናኛ አውታሮች ሲዘዋወሩ ሰንብቷል። መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችም ለመገናኛ ብዙኃን አውታሮች ችግሩ የከፋ መሆኑን አረጋግጠዋል።

ይህን ተከትሎ የደቡብ ክልል መንግሥት ተፈናቃዮቹ በዚህ ደረጃ የሰብኣዊ ጉዳት እስኪደርስባቸው ድረስ ምን ሲሰራ ነበር፣ ስለምንስ ትኩረት ነፈጋቸው ስትል አዲስ ማለዳ ለክልሉ ፕረስ ሰክሪታሪ ኃላፊ ፍቅሬ በስልክ ጥያቄን ብታቀርብም ኃላፊው ‹‹በአካል ካልመጣችሁ በስልክ መረጃ አልሰጥም›› በማለት ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል።

የብሔራዊ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊው ደበበ ዘውዴ ለአዲስ ማለዳ እንዳሉት በደቡብ ክልል ለ208 ሺሕ 275 በግጭት ተፈናቅለው የነበሩ ዜጎች በቋሚነት መደበኛ ድጋፍ እየተደረገላቸው ነው። እርዳታው የሚደረገውም መንግሥታዊ ባልሆኑ ድርጅትች ኅብረት አማካኝነት እንደሆነ ገልጸዋል።

ይሁንና በቅርቡ 54 ሺሕ 864 በአዲስ መልክ የተፈናቀሉ የጌዲኦ ተወላጆች ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው ለኮሚሽኑ ሪፖርት መድረሱን የተናገሩት ደበበ ኮሚሽኑ እርዳታ ማቅረብ የሚችለው የክልል መንግሥታት ከአቅማቸው በላይ መሆኑን በመግለፅ የተረጅዎቹን ቁጥር በደብዳቤ ሲያሳውቁ ብቻ እንደሆነም አስምረውበታል።

በዚህም ክልሉ መጋቢት 1/2011 ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል ያላቸውን 54 ሺሕ 864 አዲስ ተፈናቃዮች በደብዳቤ በማሳወቁና እርዳታ በመጠየቁ ኮሚሽኑ መጋቢት ኹለትና ሦስት እርዳታ መላኩን ገልፀዋል። በዚህም ለድጋፍ ፈላጊዎቹ ‹‹200 ኩንታል ብስኩት፣ 200 ኩንታል አልሚ ምግብ፣ 200 ኩንታል አተር ክክ፣ 200 ኩንታል ዱቄት እና ኹለት ሺሕ ሊትር ዘይት ተልኳል›› ነው ያሉት።

በቅርቡ እንደ አዲስ ከተፈናቀሉት 54 ሺሕ 864 ዜጎች ውስጥ 38 ሺሕ 258ቱ በጌዲኦ ዙሪያ ጎቲቲ፣ ሰባት ሺሕ 263ቱ በገደብ ከተማ እንዲሁም ዘጠኝ ሺሕ 343ቱ በዲላ ዙሪያ ጫጩ የተሰኙ ቦታዎች እንደሚገኙም የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊው ደበበ ለአዲስ ማለዳ ገልፀዋል። ስለተፈናቃዮቹ ሁኔታ የሚመለከት ቡድንን ያቋቋመው ኮሚሽኑ ከሰሞኑ ወደ ሥፍራው መላኩንም አሳውቋል።

በተያያዘ ዜና መፈናቀልና ሌሎችም ችግሮች ሲያጋጥሙ ሕዝቡ ለተጎጂዎች የሚያደርገው ድጋፍ በጎ ቢሆንም ያለ ክልሎችና ኮሚሽኑ እውቅና የባንክ ሒሳብ ቁጥር በመክፈት የገንዘብ ድጋፍ የሚያሰባሰቡ ወገኖች በተለያዩ ጊዜያት እንደሚስተዋሉ ያስታወሰው ኮሚሽኑ ሕጋዊ አካሔድ ባለመሆኑ ሊታረም እንደሚገባ አሳስቧል።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 6 years ago on March 23, 2019
  • By:
  • Last Modified: March 23, 2019 @ 10:13 am
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar