www.maledatimes.com የሪፍት ቫሊ ዩኒቨርሲቲ ባለቤት የ11.3 ሚሊዮን ብር የፍትሐ ብሔር ክስ ተመሠረተባቸው - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የሪፍት ቫሊ ዩኒቨርሲቲ ባለቤት የ11.3 ሚሊዮን ብር የፍትሐ ብሔር ክስ ተመሠረተባቸው

By   /   March 26, 2019  /   Comments Off on የሪፍት ቫሊ ዩኒቨርሲቲ ባለቤት የ11.3 ሚሊዮን ብር የፍትሐ ብሔር ክስ ተመሠረተባቸው

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 2 Second

ከግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት አንዱ የሆነው የሪፍት ቫሊ ዩኒቨርሲቲ ባለቤት፣ የ11.3 ሚሊዮን ብር ዕዳ የፍትሐ ብሔር ክስ ተመሠረተባቸው፡፡

ከትምህርት ዘርፍ በተጨማሪ በተለያዩ የኢንቨስትመንት ሥራዎች ላይ ተሰማርተው የሚገኙት፣ የዩኒቨርሲቲው ባለቤት አቶ ድንቁ ደያሳ የተከሰሱት፣ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 21ኛ ፍትሐ ብሔር ችሎት ነው፡፡

አቶ ድንቁ ክሱ የተመሠረተባቸው ናፍያድ ትሬዲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር በሚል ድርጅት ስም ከከፈቱት ሒሳብ፣ አቶ አንተነህ ፈለቀ ለተባሉ ግለሰብ 11,395,000 ብር እንዲከፈል ለባንክ በመጻፋቸውና በተጠቀሰው ሒሳብ ውስጥ በቂ ስንቅ ባለመገኘቱ መሆኑን ክሱ ያስረዳል፡፡

ከሳሽ ክፍያውን እንዲፈጽሙላቸው በተደጋጋሚ ቢጠይቁም ሊከፍላቸው ባለመቻሉ፣ ሒሳቡ የተከፈተበት ወጋገን ባንክ አክሲዮን ማኅበር በማቅረብ እንዳስመቱበትም ክሱ ይጠቁማል፡፡ በመሆኑም አቶ ድንቁ ቼኩ በስማቸው የወጣ በመሆኑና በቼኩም ላይ የፈረሙት እሳቸው በመሆናቸው፣ ክፍያው እንዲፈጸም ክሱ መቅረቡን ሰነዱ ያስረዳል፡፡

ከሳሽ አቶ አንተነህ ክሱን ያቀረቡት በሰበር መዝገብ ቁጥር 57923 የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በሰጠው አስገዳጅ ውሳኔ  መሠረት፣ አቶ ድንቁ በቼኩ ላይ በመፈረማቸው ከማኅበሩ ጋር በአንድነትና በተናጠል ኃላፊነት ያለባቸው በመሆኑ እንደሆነም ክሱ ያስረዳል፡፡ክሱ የቀረበለት የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 21ኛ ፍትሐ ብሔር ችሎትም፣ ተከሳሹ ሚያዝያ 30 ቀን 2011 ዓ.ም. ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡ በቂ ስንቅ የሌለው ቼክ የወንጀል ኃላፊነትን የሚያስከትል ከመሆኑ ጋር ተያይዞ፣ ግለሰቡ ቀርበው ቃላቸውን እንዲሰጡ የፌዴራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት ቦሌ ምድብ ሁለተኛ ወንጀል ችሎትም ለቦሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምርያ ትዕዛዝ መስጠቱን ማረጋገጥ ተችሏል፡፡ 

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 6 years ago on March 26, 2019
  • By:
  • Last Modified: March 26, 2019 @ 10:37 am
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar