www.maledatimes.com የባለ አደራ ምክርቤቱ በአዲስ አበባ ጉዳይ ላይ ግልጽ ሃሳቡን አስቀመጠ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የባለ አደራ ምክርቤቱ በአዲስ አበባ ጉዳይ ላይ ግልጽ ሃሳቡን አስቀመጠ

By   /   March 26, 2019  /   Comments Off on የባለ አደራ ምክርቤቱ በአዲስ አበባ ጉዳይ ላይ ግልጽ ሃሳቡን አስቀመጠ

    Print       Email
0 0
Read Time:54 Second

Image may contain: 4 people, people smiling, people on stage, people standing and indoor

የአዲስ አበባ ባለአደራ ም/ቤት (ባልደራስ)፣ መጋቢት 1 ቀን 2011 ዓ.ም በባልደራስ አዳራሽ በስፍራው በአካል ከተገኙ ከከተማዋ ነዋሪዎች ጋር ውይይት አድርጎ፣ ግልጽ፣ ጥርት ያሉና አጭር የሆኑ ባለአራት ነጥብ የአቋም መግለጫዎችን ማውጣቱ፣ እንዲሁም በዕለቱ የተገኙ በሺዎች የሚቆጠሩ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች፣ አራቱን ጥያቄዎች በሰላማዊ መንገድ ብቻ ምላሽ ያገኙ ዘንድ ውክልና እንደሰጠው ይታወቃል።

ይህንንም ተከትሎ ም/ቤቱ፣ ወደ ተግባር እንቅስቃሴ በመግባት፣ ለአብይ አህመድ (ዶ/ር)፣ ለአቶ ታከለ ኡማ (ኢ/ር)ና ለአቶ ለማ መገርሳ፤ በአሁን ወቅት የያዙትን የሥልጣን ቦታና ሃላፊነት በግልጽ በመጥቀስ፣ ከአራቱ ጥያቄዎች መካከል አንዱን በሚመለከት፤ ምላሽ እንዲሰጥበት ለሶስቱም የገዥው ሃይል ባለሥልጣናት ግልጽ ደብዳቤ አስገብቶ ምላሻቸውን በመጠባበቅ ላይ እንደሚገኝ የሚታወስ ነው።

ሆኖም፣ ም/ቤቱ ሰላማዊ እንቅስቃሴውን ለህዝብ ተደራሽ የሚያደርግበትንና መረጃዎችን የሚያሰራጭበት፤ እንዲሁም ግልጽ ዓላማና ግቡን የሚያስተዋውቅበት ኦፊሻል የማኅበራዊ ሚዲያ ገፅ በቅርቡ በመክፈት እንደሚያስተዋውቅ መግለጽ ይወድዳል።

ነገር ግን፣ ከአዲስ አባባ ባለአዳራ ም/ቤት (ባልደራስ) እውቅና ውጪ፣ በማኅበራዊ ሚዲያ የተከፈቱ የፌስ ቡክ ገፆች መኖራቸውን ደርሰንበታል። ይሄም ስህተት በመሆኑ፣ አንባቢያንም ግንዛቤ በመውሰድ፣ የተከፈቱት የፌስ ቡክ ገፆች በአዲስ አበባ ባለአዳራ ም/ቤት ያልተከፈቱ መሆናቸው ግንዛቤ እንዲወሰድ ማስገንዘብ እንወድዳለን።

በተያያዘም፣ በትናንትንው ዕለት፣ የም/ቤቱ ስድስት አባላት የተለመደ ሰላማዊ ውይይትና ምክክራቸውን አድርገዋል።

የአዲስ አበባ ባለአደራ ም/ቤት (ባልደራስ)

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 6 years ago on March 26, 2019
  • By:
  • Last Modified: March 26, 2019 @ 11:03 am
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar