በቅርስነት የተመዘገበውን የደጃዝማች ዐምዴ አበራ ካሳ መኖሪያ ቤት ያፈረሰው የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ቤቱ በቅርስነት ስለመመዝገቡ ምንም ዓይነት መረጃ የለኝም ማለቱ እያነገጋረ ነው፡፡
***********************************
በትላንትናው ዕለት መፍረሱ የተሰማው በአዲስ አበበ ከተማ በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ አንድ የሚገኘው እና በቅርስነት የተመዘገበው የደጃዝማች ዐምዴ አበራ ካሳ መኖሪያ ቤት በቅርስነት ስለመመዝገቡ ምንም ዓይነት መረጃ የለኝም ሲል የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ተናገረ፡፡
የአዲስ አበባ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ በበኩሉ ቤቱ በቅርስነት ከተመዘገቡ ከ400 በላይ ቅርሶች መካከል አንዱ መሆኑን ገልጾአል፡፡
የደጃዝማች ዐምዴ አበራ ካሳ መኖሪያ ቤት በትናንትናው እለት በፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን አማካኝነት የፈረሰ ሲሆን ቤቱከ90 ዓመታት በላይ ያስቆጠረ ነው፡፡
በአዲስ አበበ ከተማ በቅርስነት ከተያዙ ታሪካዊ ግንባታዎች አንዱ እንደሆነ የሚነገርለት የደጃዝማች ዐምዴ አበራ ቤት ለምን እንዳፈረሰ የተጠየቀው የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በበኩሉ ቤቱ በቅርስነት ስለመመዝገቡ ምንም ዓይነት መረጃ የለኝም ያለ ሲሆን በቅርስነት ተመዝግቧል የተባለውን የዚህን መኖሪያ ቤት ጉዳይ ወደ ፊት በህግ አግባብ ለመፍታት እንደሚንቀሳቀስ የአዲስ አበበ ከተማ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ መግለፁን የኢቢሲ ዘግቧል፡
Wondering where the comments are? We encourage you to use the share buttons below and start the conversation on your own!
- Click to email a link to a friend (Opens in new window)
- Click to share on Facebook (Opens in new window)
- Click to share on Twitter (Opens in new window)
- Click to share on LinkedIn (Opens in new window)
- Click to share on Pinterest (Opens in new window)
- Click to share on Tumblr (Opens in new window)
- Click to print (Opens in new window)
Average Rating