Read Time:42 Second
ዛሬ የተከለከለው ጋዜጣዊ መግለጫ በተመለከተ!
.
~ በዛሬው እለት አዲስ አበባ ባለአደራ ምክር ቤት /ባልደራስ/ ይሰጠው የነበረው ጋዜጣዊ መግለጫ “ከበላይ አካል በመጣ” ቀጥተኛ ትዕዛዝ ክልከላ ተደርጎበታል ።
.
~ የክልከላው ምክንያት አስመልክቶ በቦታው ላይ በዋነኛነት መመሪያ ሲሰጥ የነበረው አዛዥ ፖሊስ “ክልከላው ከበላይ አካል የተሰጠ ትዕዛዝ ነው”ከማለት ውጪ ለጋዜጠኞችም ሆነ ጋዜጣዊ መግለጫ ላዘጋጅቱ አካላት ምንም ዓይነት ምላሽ ለመስጠት ፍቃደኛ አልነበረም ።
.
~ ይሁን እንጂ የአዲስ አበባ ባለአደራ ም/ቤት (ባልደራስ ) በሆቴል ውስጥ ይሰጠው የነበረው ጋዜጣዊ መግለጫ ክልከላ አስመልክቶ ጥሪ ላደረገላቸው ጋዜጠኞች ማብራሪያ በሆቴሉ በራፍ ላይ ለመስጠት ሙከራ ቢያደርጉም በድጋሚ ፖሊሶች ክልከላ አድርገዋል ።
.
~ ጋዜጣዊ መግለጫ ለመዘገብ የተገኙ ጋዜጠኞች እንዲሁም ጉዳዩን ለመከታተል የመጡ ሰዎችን ፖሊስ በማስገደድ ከአካባቢው እንዲርቁ አድርጓል ።

.
~ በዛሬው እለት መግለጫ እንዳይሰጥ ክልከላ የተደራገበት ባለአደራ ምክር ቤት /ባልደራስ/ በመጪው አጭር ቀናት ውስጥ ጉዳዩን አስመልክቶ እንዲሁም ተያያዥ በሆነ ነገሮች ቦታው እና ሰዓቱ ኮሚቴው ግልጽ በሚያደርገው ቀን ለህዝብ መግለጫ እንደሚሰጥ ጋዜጠኛና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች እስክንድ ነጋ መልዕክቱን አስተላልፏል።
.
Wondering where the comments are? We encourage you to use the share buttons below and start the conversation on your own!
- Click to email a link to a friend (Opens in new window)
- Click to share on Facebook (Opens in new window)
- Click to share on Twitter (Opens in new window)
- Click to share on LinkedIn (Opens in new window)
- Click to share on Pinterest (Opens in new window)
- Click to share on Tumblr (Opens in new window)
- Click to print (Opens in new window)
Average Rating