www.maledatimes.com በ3 ቢሊየን ብር የገበያ ማዕከል እገነባለው ያለው ድርጅት ውጥረት ውስጥ ገብቷል - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

በ3 ቢሊየን ብር የገበያ ማዕከል እገነባለው ያለው ድርጅት ውጥረት ውስጥ ገብቷል

By   /   March 31, 2019  /   Comments Off on በ3 ቢሊየን ብር የገበያ ማዕከል እገነባለው ያለው ድርጅት ውጥረት ውስጥ ገብቷል

    Print       Email
0 0
Read Time:2 Minute, 46 Second

• ድርጅቱ 28 ሚሊዮን ብር ከ3500 ባለአክሲዮች ሰብሰቧል

የዛሬ ኹለት ዓመት ገደማ በ3 ቢሊየን ብር የገበያ ማዕከል እገነባለው ብሎ እስካሁን ወደ 28 ሚሊየን ከተለያዩ ባለሀብቶች የሰበሰበው የሕዳሴ አክስዮን ማኅበር ከአዲስ አበባ መስተዳድር ምንም ዓይነት ይሁንታ አለማግኘቱና የግንባታውን ተፈፃሚነቱ አጠራጣሪ ደረጃ መድረሱ ታወቀ። በዚህም የተነሳ ባለአክሲዮኖች ከድርጅቱ ኃላፊዎች ጋር እሰጣ ገባ ውስጥ ገብተዋል።

አዲስ ማለዳ ባደረገችው ማጣራት ድርጅቱ የገበያ ማዕከሉን የመጀመሪያ ዙር ግንባታ በቀጣይ ዓመት አጠናቅቃለው ብሎ የነበረ ቢሆንም ለመሬት አስተዳደር ቢሮ ምንም ዓይነት ጥያቄ አለማቅረቡ ታውቋል። ይህንንም የቢሮው የለማ መሬት አስተዳደር ዳይሬክተር የሆኑት መኩሪያ ለማ ለአዲስ ማለዳ አረጋግጠዋል።

ይሁን እንጂ፤ የድርጅቱ የመሬት ጥያቄ በልዩ ጨረታ እንዲስተናገድ በከንቲባ ቢሮ መወሰኑን ተናግረዋል። ነገር ግን፤ ድርጅቱ ሊያስገባ የሚችለው የውጭ ምንዛሬ፣ ለከተማው ገፅታ ያለው አስተዋፅኦ እና መነሻ ካፒታሉ ከታየ በኋላ ሕዳሴ መስፈርቱ እንደማያሟሉ ተደርሶበታል ያሉት መኩሪያ ከድርጀቱ አስተዳደሮች ውስጥ በአካል መጥቶ ያናገራቸው እንደሌለ ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።

በተጨማሪም፤ የገበያ ማዕከሉ በውስጡ 5 ሺሕ ሱቆች፣ 2 ዘመናዊ ባለ አራት ኮከብ ሆቴሎች፣ ባንክና ኢንሹራንስ እንዲሁም ካፌና ሬስቶራንቶችን የሚይዝ ነው በማለት የአክሲዮን ማኅበሩ መሰራቾች ከምስረታ ወቅት አንስቶ በሚሊዮን ብሮች ቢሰበሰብም አንድም በመሬት ላይ የሚታይ ነገር አለመኖሩ ባለአክሲዮኖች ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።
ከዚህ ባሻገር፤ አክሲዮን ማኅበሩ በመሐል አዲስ አበባ ስምንት ሺሕ ተሽከርካሪዎችን የሚይዝ የመኪና ማቆሚያ፣ የመኖሪያ አፓርታማዎች፣ ሬስቶራንቶችና የፋይናንስ ተቋማት የሚገለገሉባቸው ግዙፍ የገበያ ማዕከል ለመገንባት ዕቅድ ይዞ የነበረ ቢሆንም ተግባራዊ መደረግ አልተቻለም።

አክሲዮኑ 3500 ባለአክስዮኖች ያሉት ሲሆን ባለበት ውጥረት ምክንያት የአክስዮን ማኅበሩ ሠራተኞች ቁጥር ተቀናሽ ማድረጋቸውን ገልፀው አሁን ምዝገባ አንመዘገብም ያሉት የአክስዮን ማህበሩ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሸምሰዲን አብድራህማን ክፍያ የፈፀሙ ባለ አክስዮኖች 402 እንደሆኑ ተናግረዋል።

የዛሬ ኹለት ዓመት ገደማ በምሥረታ ወቅት የአክሲዮን ማኅበሩ አስተዳደሮች የገበያ ማዕከሉን ግንባታ ለማስጀመር ተቋራጮችን በግልጽ ጨረታ ለማወዳደር ዝግጅት ማጠናቀቃቸውን ቢገልፁም ምንም ዓይነት እንቅስቃሴ በዚህ አኳያ አለመደረጉ ታውቋል።

በ2009 መሟላት ያለበትን ቅድመ ሁኔታዎች ድርጅቱ አሟልቶ 250 ሺሕ ካሬ ሜትር ለመልሶ ማልማት ከሚነሱ ቦታዎችን ጠይቆ ነበር ያሉት ሸምሰዲን የአዲስ አበባ ከተማ የቀድሞ ከንቲባ የነበሩት ድሪባ ኩማ ይሁንታ አግኝተን ነበር ብለዋል። ይሁን እንጂ፤ አዲስ ማለዳ ባደረገችው ማጣራት ድርጅቱ ከውይይት ባለፈ ከቀድሞ ከንቲባ መሬት ይሰጣቸው የሚል ይሁንታ አለማግኘቱ ተረጋግጧል።

ይሁን እንጂ፤ የምንገነባው ግዙፍ የገበያ ማዕከል በመሆኑ ለአገር ይጠቅማል አይጠቅምም የሚለው ጥናት መደረግ አለበት በሚል የከተማው ከንቲባ ቢሮ አዘግይቶብናል በማለት ሸምሰዲን ገልጸዋል። በተጨማሪ፤ ትላልቅ ፕሮጀክቶችን አገራዊ ፋይዳቸው ከፍተኛ ስለሆነ ለጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ ደብዳቤ ያስገባን ቢሆንም፤ በመስተዳደሩ የተሰጣቹ ምላሽ አርኪ ካልሆነ ነው ወደ እኛ መምጣት የምትችሉት የሚል ምላሽ ተሰጥቶናል ሲሉ ሸምሰዲን ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።

ይሁን እንጂ፤ ከከንቲባም ቢሮ ሆነ ከመሬት ልማት ቢሮ ይሁንታ ያላኘው አክሲዮን ማኅበሩ ሆቴልና ሞል ዘርፍ ላይ የሚሰሩ ፕሮጀክቶች በምደባና በልዩ ጨረታ ሊስተናገዱ የሚችሉበት መንገድ ቢኖርም በዚህ አኳያ ያደረገው ነገር እንደሌለ ታውቋል። ባለፉት ስምንት ወራት የተለያዩ ሥራዎች በመሬት አስተዳደር 144 አልሚዎች በየዘርፋቸው ለይቶ 102 መሬት ያዘጋጀ ቢሆንም ከሕዳሴ ያቀረበው ምንም ዓይነት ጥያቄ እንደሌለ ተረጋግጧል።

አክስዮኖች ለምን ይቋጣሉ የሚል ጥናት አጥንተን ነበር ወደ ሥራ የገባነው ያሉት ሸምሰዲን በበኩላቸው የአዲስ አበባ መሬት አስተዳደር የመሬት አቅርቦት ችግር ምክንያት ወደ ሥራ መግባት እንዳልተቻለና ለባለአክስዮኖቻቸው በአጭር ጊዜ ውስጥ ለመጨረስ የገቡትን ቃል ለማጠፍ መገደዳቸውን ገልፀዋል። በተጨማሪም ድርጅታቸው ሊገነባ አስቦት የነበረው የገበያ ማዕከል ለአገር ገፅታ ግንባታ ከፍተኛ አስተዋፅኦ የነበረው ቢሆንም ምንም መፍትሔ እየተሰጠን አይደለም ብለዋል። የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ጋር ገለፃ እንደምናደርግ ተነግሮን እየጠበቅን ነው ሲሉ አክለዋል።

በሌላ በኩል መሬት በመንግሥት እንጂ በግለሰብ የሚተዳደር ባለመሆኑ የፈለጉትን ያህል ካሬ ሜትር ቦታ እዚህ ቦታ ላይ እፈልጋለው ብለው በአማራጭና በቀላሉ መውሰድ አይችሉም ያሉት የመሬት ባንክና ማስተላለፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ተስፋዬ ጥላሁን ˝ለአንድ ባለሀብት መሬት ለመስጠት አርሶ አደር ማስነሳትና ካሳ መከፈል አለበት ስለዚህም አልሚዎችን መፈተሸና ማጥናት አለብን˝ ብለዋል።

˝ይህን አድርገን ባለሀብቱ ምንም የማይሠራበት ከሆነ የመሬት ብክነት ስለሚያጋጥም መስፈርቱን አሟልተው መስተናገድ ይችላሉ˝ ያሉት ተስፋዬ የሕዳሴ መሥራቾች ምንም ይሁንታ ሳያገኙ አክስዮን መሰብሰብ አልነበረባቸውም ብለዋ

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 6 years ago on March 31, 2019
  • By:
  • Last Modified: March 31, 2019 @ 1:24 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar