www.maledatimes.com በስድስት ወራት ውስጥ ከ100 ሺሕ በላይ ሕገ ወጥ የጦር መሣሪያዎች በቁጥጥር ሥር ዋሉ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

በስድስት ወራት ውስጥ ከ100 ሺሕ በላይ ሕገ ወጥ የጦር መሣሪያዎች በቁጥጥር ሥር ዋሉ

By   /   April 9, 2019  /   Comments Off on በስድስት ወራት ውስጥ ከ100 ሺሕ በላይ ሕገ ወጥ የጦር መሣሪያዎች በቁጥጥር ሥር ዋሉ

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 55 Second

ሕገ ወጥ የጦር መሣሪያ ዝውውርን ለመቆጣጠር በተሠራው ሥራ በ2011 በግማሽ ዓመት 103 ሺሕ 311 የተለያዩ ጥይቶች፣ 1 ሺሕ 560 ሽጉጦች፣ 5 መትረየስ (ብሬይን) መሣሪያ፣ 5 ክላሽንኮቭ ጠብመንጃ በሕገ ወጥ የጦር መሣሪያ አዘዋዋሪዎች ቤት ሲበረበር መያዙን የፌደራል ወንጀል ምርመራ ቢሮ ለአዲስ ማለዳ አስታውቋል። ይህ የጦር መሳሪያ ዝውውር በ2010 ሙሉ ዓመት ከነበረው ተቀራራቢ መሆኑን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ከተለያዩ አቅጣጫዎች ድንበር አቋርጠው ወደ አገሪቱ የሚገቡ ሕገ ወጥ መሣሪያዎች የመያዛቸው መረጃ መሰራጨት ከጀመረ ውሎ አድሯል። ለአብነትም ነዳጅ ጭኖ ከሱዳን ወደ ኢትዮጵያ ይጓዝ የነበረ መኪና በምዕራብ ጎንደር ዞን ገንደ ውሃ አካባቢ ተገልብጦ፤ ፖሊሶች ባደረጉት ፍተሻ ወደ 1 ሺሕ 291 የቱርክ ሽጉጥ እንዲሁም 97 ክላሽ በቁጥጥር ስር የመዋሉ ዜና የተሰማው ከጥቂት ወራት በፊት ታኅሣሥ ላይ ነበር። ባለፉት ጥቂት ወራት ባልተለመደ መልኩ መዲናዋ አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ ክልሎች ሕገ ወጥ የመሣሪያ ዝውውር መበራከቱ እየተሰማ ነው።

ኅዳር 10/ 2011 ፌደራል ፖሊስ እንዳስታወቀው በያዝነው በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሦስት ወራት 2 ሺሕ 516 የተለያዩ የጦር መሣሪያዎች በሕገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወሩ መያዛቸውን አስታውቋል። ይህም የመሣሪያ ዝውውሩ በኹለተኛው ሩብ ዓመት ከሦስት እጥፍ በላይ ዕድገት ማሳየቱ ነው።

ከፌደራል ወንጀል ምርመራ ቢሮ ባገኘነው መረጃ መሰረት የሕገ ወጥ መሣሪያ ዝውውሩ ለንጹሐን ዜጎች ሕይወት መጥፋት፣ በየአካባቢው ለሚከሰቱ የማኅበረሰብ ግጭቶች ማባባሻ፣ በተለያዩ ቦታዎች ለሚፈጸሙ ዘረፋዎች፣ ስርቆቶች፣ ለሕገ ወጥ ንግድ ኮንትሮባንድ ማስፈጸሚያ እየሆነ ይገኛል።

በመሆኑም በአሁኑ ወቅት ከሱዳን በመተማ በኩል፤ ከደቡብ ሱዳን በጋምቤላ በኩል ወደ አገር ውስጥ በተለያየ መልኩ እንዲገባ እየተደረገ መሆኑን የፌደራል ወንጀል ምርመራ ቢሮ ያስታወቀ ሲሆን በተለይ በአሁኑ ወቅት በመኪና ተደብቆ እየገባ ያለው የጦር መሣሪያ እጅግ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ ለአዲስ ማለዳ አስታውቀዋል።

ቤኒሻንጉል ጉሙዝ በሕገ ወጥ መሣሪያ ዝውውር ሥማቸው ከሚነሱ ክልሎች ሌላው ነው። ክልሉ ከደቡብ ሱዳን ጋር አዋሳኝ ከተማ በሆነችው ናኮሞ በተባለች ወረዳ ሕገ ወጥ መሣሪያዎች እንደሚገቡ የክልሉ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አበራ ባየታ ከወር በፊት ለሚዲያዎች በሰጡት መግለጫ መናገራቸው ይታወሳል።

ቡዋ አልመሀል በተባለ ኬላ አልፎ አልፎም ከመሀል አገር መሣሪያ እንደሚገባ ተናግረው፤ ሕገ ወጥ መሣሪያዎችን በግንባር ቀደምነት “በፍተሻ እንይዛለን” ብለዋል። በዘላቂነት የሕገ ወጥ መሣሪያ ዝውውርን ለመግታት ደግሞ በክልሉና በፌደራል መንግሥት ጥምረት የተዋቀረ ግብረ ኃይል ማቋቋማቸውን ጠቁመዋል።

የካቲት 8/2011 በቅርቡ እየተስፋፋ ለመጣው የሕገ ወጥ የጦር መሣሪያ ዝውውር ተጠያቂው ማነው? ተብለው የተጠየቁት የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል እንደሻው ጣሰው፤ “የሕገ-ወጥ የጦር መሣሪያ ዝውውሩ የሚከናወነው ለውጡን በማይደግፉ አካላት ነው” ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

በየዕለቱ ከሚወጡት ዘገባዎች አንጻር ከአራቱም የአገሪቱ አቅጣጫዎች ሕገ ወጥ የጦር መሣሪያ እንቅስቃሴ እንዳለ አመልካቾች ናቸው። በፀጥታ ኃይሎች የተያዙት የጦር መሣሪያዎች መጠን ከፍተኛ ቢሆንም፤ ሳይያዙ ወደ ተለያዩ ሰዎች እጅ የገቡት ቁጥር ምን ሊያስከትሉ እንደሚችሉ አለመታወቁ በርካቶችን ሥጋት ላይ ጥሏል።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 6 years ago on April 9, 2019
  • By:
  • Last Modified: April 9, 2019 @ 8:23 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar