www.maledatimes.com በኹለት ክልሎች ያለሰሌዳ የሚንቀሳቀሱ ‘ሕገ ወጥ’ 134,345 ሞተር ሳይክሎች መኖራቸው ታወቀ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

በኹለት ክልሎች ያለሰሌዳ የሚንቀሳቀሱ ‘ሕገ ወጥ’ 134,345 ሞተር ሳይክሎች መኖራቸው ታወቀ

By   /   April 9, 2019  /   Comments Off on በኹለት ክልሎች ያለሰሌዳ የሚንቀሳቀሱ ‘ሕገ ወጥ’ 134,345 ሞተር ሳይክሎች መኖራቸው ታወቀ

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 41 Second

  • ሞተር ሳይክሎቹ ከ3-4 ሰዎች በመጫን አደጋ እያደረሱ መሆኑ ታውቋል

የፌደራል ትራንስፖርት ባለሥልጣን በሕገ ወጥ መንገድ የገቡ ባለኹለት እግር ሞተር ሳይክሎች አስፈላጊውን ማስረጃና የሠሌዳ ቁጥር እንዲኖራቸው ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት የመሥራት ኃላፊነት ቢኖርበትም 134 ሺሕ 345 ሞተር ሳይክሎች ተመዝግበው ሰሌዳ ሳይሰጣቸው በመንገድ ላይ የሚንቀሳቀሱ መሆናቸውን በፓርላማ የመንግሥት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አስታወቀ።

በደቡብ ብሔር፣ ብሔረሰቦች ክልል 109 ሺሕ 345 ሞተር ሳይክሎች፣ እንዲሁም በኦሮሚያ 25 ሺሕ ሞተር ሳይክሎች፤ በጠቅላላው 134 ሺሕ 345 ሞተር ሳይክሎች ተመዝግበው ሰሌዳ ሳይሰጣቸው በመንገድ ላይ እንደሚንቀሳቀሱ ቋሚ ኮሚቴው አስታወቋል።

ቋሚ ኮሚቴው የፌደራል ትራንስፖርት ባለሥልጣን የመንገድ ደኅንነት አፈጻጸምን በተመለከተ የተከናወነውን የክዋኔ ኦዲትን መሰረት በማድረግ ለተቋሙ የበላይ የሥራ ኃላፊዎች ለውይይት መነሻ ባቀረበው ጥያቄ፣ እነዚህን ሞተሮች የሚያሽከረክሩ አሽከርካሪዎች መንጃ ፈቃድ ሳይኖራቸው ከ2 እስከ 5 ሰዎችን እየጫኑ በሰው ሕይወት ላይ አደጋ እያስከተሉ መሆኑን አንስቷል።
˝እነዚህ ሞተር ሳይክሎች የሠሌዳ ቁጥር እንዲኖራቸውና የሚያደርሱትንም አደጋ ለመቆጣጠር ለምን አልተሰራም? አሁንስ ባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ ይሄንን ለማስተካከል ምን እየሠራ ነው?˝ በማለት የመንግሥት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ለፌደራል ትራንስፖርት ባለሥልጣን ጥያቄ አቅርቧል።

ለጥያቄው ምላሽ የሰጠው የፌደራል ትራንስፖርት ባለሥልጣን፣ በደቡብ ክልል ሃያ ሺሕ ሞተር ሳይክሎች ወደ ሕጋዊነት እንዲገቡ ማድረጉን ገልጾ፣ በቀሪዎቹም ላይ ተመሳሳይ ሥራ በመሥራት ላይ እንደሚገኝ አመላክቷል።

ሞተር ሳይክሎች የሕዝብ ማመላለሻ መሆናቸው ችግር እየፈጠረ መሆኑን ያነሱት የምክር ቤቱ አባል ወይንሸት ገላምሶ፣ በዘጠኝ የተለያዩ ድንበሮች (መንገዶች) በሕገ ወጥ መንገድ ሞተር ሳይክሎች እየገቡ እንዳሉ ጠቁመው፤ የፌደራል መንገድ ትራንስፖርት ያቀረበው፣ በደቡብ ክልል አጠቃላይ የሚገኙት የሞተር ሳይክል ቁጥሮች በደቡብ ክልል ካለው ሕዝብ የሚስተካከል መሆኑን በማንሳት ተጨማሪ ጥናት እንደሚያስፈልገው ጠቁመዋል።

በተጨማሪም የፌደራል ትራንስፖርት ባለሥልጣን የመንገድ ትራፊክ ደኅንነትን ለማስጠበቅ በሚሠራው ሥራ ላይ የመንግሥት ተቋማት በተቀናጀ መልኩ መሥራት ባለመቻላቸው፤ እንደቴሌና መብራት ኃይል ያሉ ተቋማት መንገድ እየቆፈሩ በመተው፤ በመንገድ ላይ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተግባራትን እንዳያከናውን የወጣው የደንብ ቁጥር 208/2003 ተግባራዊ እንዲሆን ማድረግ አለመቻሉና ተፈጻሚነቱንም በተሟላ ሁኔታ እንዳለተከታተለ በኦዲት ሪፖርቱ አስታውቋል።

በሌላ በኩል በከፍተኛ ወጪ የተሠሩ የእግረኛና የተሽከርካሪ መንገዶች ላይ የሚፈጸሙ ሕገ ወጥ ተግባራትን፣ ለምሳሌ የግንባታ ዕቃዎች (አሸዋ፣ ብረት፣ ድንጋይ) በማስቀመጥ የእግረኞችን መንገድ በመዝጋት እና በማጣበብ መንገዶች እንዲጨናነቁና እግረኞች ለትራፊክ አደጋ እንዲጋለጡና የመንገዱም ዕድሜ እያጠረ እንዲሔድ የሚያደርጉ ሕገ ወጥ ተግባራትን ባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ ለምን ማስቆም እንዳልቻለ በቋሚ ኮሚቴው ተጠይቆ፣ በቀረቡት ዝርዝር ጉዳዮች ላይ ጥናት አድርጎ እየሠራ መሆኑን አስታውቋል።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 6 years ago on April 9, 2019
  • By:
  • Last Modified: April 9, 2019 @ 8:31 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar