www.maledatimes.com የብሔራዊ አልኮል የቀድሞ ባለቤት ንብረት እንዲጣራ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሰጠ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የብሔራዊ አልኮል የቀድሞ ባለቤት ንብረት እንዲጣራ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሰጠ

By   /   April 9, 2019  /   Comments Off on የብሔራዊ አልኮል የቀድሞ ባለቤት ንብረት እንዲጣራ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሰጠ

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 48 Second

የብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ ሽያጭ መታገድን ተከትሎ የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ሚኒስቴር ባቀረበው ቅሬታ መሰረት የፋብሪካው የቀድሞ ባለሀብት ብርሃኔ ገብረ መድን በአሜሪካ ያላቸው ንብረት በአገሪቱ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ተጣርቶ እንዲቀርብ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሰጠ።

በትውልድ ኤርትራዊ ዜግነታቸው ደግሞ አሜሪካዊ የሆኑት ብርሃኔ የተጠየቁትን የዳኝነት ክፍያ መክፈል ስለማይችሉ የባለቤትነት ጥያቄያቸው በደሀ ደንብ እንዲታይላቸው ጥያቄ ማቅረባቸውን ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የተቃወመ ሲሆን በአገረ አሜሪካ ያላቸው ንብረት እንዲጣራ ጥያቄ አቅርቧል።

በዚህም መሰረት ፍርድ ቤቱ አሜሪካ ለሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ ጉዳዩን አጣርቶ እንዲያቀርብላቸው ትዕዛዝ አስተላልፏል። ይሁን እንጂ ትዕዛዙን ቢያስተላልፍም ኢምባሲው ለፍርድ ቤቱ እስካሁን ምላሽ መስጠት አለመቻሉ ታውቋል።
ፍርድ ቤቱም ኤምባሲው ለተጠየቀው ጥያቄ ማረጋገጫ የሚሆነውን ምላሽ ማቅረብ ያልቻለበትን ምክንያት የኤምባሲው የሚመለከተው ኃላፊ ለፍርድ ቤቱ ቀርበው እንዲያስረዱ በተለዋጭ ቀጠሮ ለሚያዝያ 30 /2011 ትዕዛዝ አስተላልፏል።

መንግሥት ሙሉ በሙሉ ወደ ግል ይዞታ እንዲዛወር ካቀዳቸው ድርጅቶች አንዱ የሆነው የብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ ሽያጭ ዙርያ ከሳሽ ብርሃኔ በፋብሪካው ላይ የባለቤትነት ጥያቄ ማንሳታቸውን ተከትሎ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሽያጭ ሒደቱ እንዳይቀጥል የእግድ ትዕዛዝ ማስተላለፉ ይታወሳል።

ከዚህ ቀደም ፋብሪካውን ለመሸጥ ጨረታ መውጣቱን ተከትሎ የጨረታ አሸናፊ የነበረው ሎሚናት መጠጥ ፋብሪካ በ3 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ፋብሪካውን እንዲጠቀልለው ተወሰኖለት የነበረ ቢሆንም የረጅም ጊዜ የባለቤትነት ጥያቄ ባቀረቡት ብርሃኔ ክስ የተመሰረተ በመሆኑና ሽያጩ በመታገዱ እስከአሁን ሊጠናቀቅ አልቻለም።

በቀድሞ ሥሙ ኤሊያስ ፓፓሲኖስ መጠጥ ፋብሪካ የአሁን ብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ ከዛሬ 106 ዓመታት በፊት የተመሰረተ ሲሆን እስከ 1969 ድረስ በብርሃኔ ሥር ይተዳደር የነበረ ፋብሪካ ነበር። ይሁንና በቀድሞ የጊዜያዊ ወታደራዊ አስተዳደር ደርግ ዋና ፀሐፊ ፍቅረሥላሴ ወግደረስ ትዕዛዝ 1969 በመንግሥት እንዲወረስ ተደርጎ ነበር።

በአፈቀላጤ የተወረሱ ንብረቶች ወደ ባለቤቶቻቸው እንዲመለሱ ፓርላማው በ1983 ሕጉን ካፀደቀ በኃላ ብርሃኔም ድርጅታቸው እንዲመለስላቸው ጥያቄ አቅርበው ነበር። ከዚያም በ1990 በቀድሞ የፕራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ ቦርድ ሊቀ መንበር በነበሩት አሰፋ አብረሃ እና ሌሎች የቦርድ አባላት ትዕዛዝ የአልኮል ፋብሪካውን በወቅቱ የወጣበትን ወጪ 26 ሚሊዮን ብር ከፍለው አልያም አቅሙ ከሌላቸው ካሳ እንዲከፈላቸው አዞ ነበር።

ይሁን እንጂ በ1991 በኢትዮጵያና ኤርትራ መንግሥታት የተፈጠረውን ጦርነት ተከትሎ የቀድሞ ባለቤቱ ከአገር እንዲወጡ በመደረጋቸው ኹለቱንም ማድረግ አልቻሉም ነበር። ከዚያም በ2001 ወደ ኢትዮጵያ አንዲገቡ ከተፈቀደላቸው በኋላ ግለሰቡ ድርጅቱ ይመለስልኝ የሚለውን ጥያቄ አቅርበው፤ የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ትብብር ሚኒስቴር ካሳ እንዲከፍላቸው ቢወስንም ሳይቀበሉት ቀርተዋል።

ብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ ከፍተኛ ሽያጭ እና ትርፍ በማስመዝገብ ስኬታማ እንደሆነም የሚታወቅ ሲሆን ፋብሪካው 42 በመቶ የሚሆነውን የኢትዮጵያ የአረቄ ገቢያን ተቆጣጥሯል። ፋብሪካውም በ2008 በጀት ዓመት ብቻ 475 ሚሊዮን ብር ሽያጭ ያስመዘገበ ሲሆን ትርፉም ከታክስ በፊት 132 ሚሊዮን ብር ነበር።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 6 years ago on April 9, 2019
  • By:
  • Last Modified: April 9, 2019 @ 8:34 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar