www.maledatimes.com በጎፋ ዞን 49 ተጠርጣሪዎች ላይ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ባለመፈጸሙ እስካሁን አልተፈቱም ተባለ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

በጎፋ ዞን 49 ተጠርጣሪዎች ላይ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ባለመፈጸሙ እስካሁን አልተፈቱም ተባለ

By   /   April 9, 2019  /   Comments Off on በጎፋ ዞን 49 ተጠርጣሪዎች ላይ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ባለመፈጸሙ እስካሁን አልተፈቱም ተባለ

    Print       Email
0 0
Read Time:2 Minute, 1 Second

  • የሰብኣዊ መብት ኮሚሽን የተፋጠነ ፍትሕ እንዲያገኙ ተናግሬ ነበር ብሏል

በደቡብ ክልል፣ በጎፋ ዞን ዛላ ወረዳ ገልማና ገንዳ ቀበሌዎች መካከል ነዋሪ የሆኑ 49 ሰዎች ከትምህርት ቤት ሥያሜ ቅሬታ ጋር በተያያዘ የወረዳው አስተዳደርና አመራር ከወረዳው ፖሊስ ጋር በመሆን ይዟቸው፣ ለስድስት ወራት ያህል ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ ተይዘው ማረፊያ ቤት ይገኙ የነበሩ ተጠርጣሪዎች በፍርድ ቤት በ5ሺሕ ብር ዋስ እንዲፈቱ ትዕዛዝ ቢሰጥም እስካሁን አለመፈታታቸውን የተጠርጣሪ ቤተሰቦች ለአዲስ ማለዳ ገለጹ።

አቤት ባዮቹ፣ መስከረም 7/2011 በወረዳው አስተዳደርና ፖሊስ ተይዘው የተከሰሱበት ክስና ምክንያት ሳይነገራቸው፣ በዛላ ወረዳ ፖሊስ ማረፊያ፣ በጊዜ ቀጠሮ አንድ ወር ያህል ከቆዩ በኋላ ያለምንም ክስና የጊዜ ቀጠሮ ለስድስት ወር ያህል በእስር መቆየታቸውንና የዋስትና መብት ለመጠየቅም ፍርድ ቤት የሚቀርቡበት ዕድል ያለማግኘታቸውን አዲስ ማለዳ በየካቲት 23፣ ቁጥር 16 ዕትሟ ላይ መዘገቧ ይታወሳል።

በጉዳዩ ዙሪያ ያነጋገርናቸው የጎፋ ዞን ፍትሕ መምሪያ ዐቃቤ ሕግ አንዱዓለም ጀማል፣ ተጠርጣሪዎቹ በመጋቢት 15/2011 በፍርድ ቤት ትዕዛዝ እያንዳንዳቸው በ5 ሺሕ ብር ዋስ እንዲወጡ መደረጋቸውን ተናግረው፣ 35 የሚሆኑ ተጠርጣሪዎች ግን በሰው ነፍስ ማጥፋትና በንብረት መውደም የተጠረጠሩ በመሆናቸው ጉዳያቸው ተጣርቶ ክስ ሊመሰረትባቸው መሆኑን ለአዲስ ማለዳ አስረድተዋል፡፡

̋ጉዳዩን ለማጣራትና ክስ ለመመስረት ሰባት ወር መፍጀቱና ተጠርጣሪዎቹ በሰባት ወር ውስጥ ፍርድ ቤት አልቀረቡም የሚለው አቤቱታ ምን ያህል ዕውነት ነው?̋ በሚል አዲሰ ማለዳ ላቀረበችላቸው ጥያቄ ምላሽ የሰጡት አንዱዓለም፣ ወንጀሉ የተወሳሰበ በመሆኑና በቂ የምርመራ ጊዜ ያስፈለገው በመሆኑ መዘግየቱን ጠቅሰው አሁን ግን መዝገቡን መርምረን ክስ የሚያስፈልጋቸውን ክስ መስርተን ቀሪዎቹን ተጠርጣሪዎች በዋስ ለቀናል ብለዋል፡፡

አቤት ባዮቹ የታሰሩበት ምክንያት በገንዳ ቀበሌ ውስጥ የሚገኘው ትምህርት ቤት በእኛ ሥም ይጠራ በሚል ጥያቄ፣ በኹለቱ ቀበሌዎች በተነሳው ኹከት፣ በንብረትና በሰው አካል ላይ በደረሰው ጉዳት ተጠርጥረው የተያዙ ናቸው። በተወሰኑ ሰዎች ቅስቀሳ አለመግባባት ተፈጥሮ መቆየቱን ገልጸዋል። በዚህ ጸብ መነሻነት የዛላ ወረዳ አስተዳደርና አመራር ከወረዳ ፖሊስ ጋር በመሆን የኹለቱን ቀበሌ ሕዝብ እናስታርቃለን በማለት ስብሰባ ጠርቶ፣ ከስብሰባው ቦታ አፍኖ በመውሰድ እንዲታሰሩ ማድረጉን አዲስ ማለዳ መዘገቧ ይታወሳል።

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 19(4) እና 37(4) መሰረት፣ ማንኛውም ሰው በተጠረጠረበት ወንጀል ፍርድ ቤት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ሲወስን፣ የሕግ አስከባሪ አካላት ምርመራውን አጣርተው የተያዘውን ሰው በተቻለ ፍጥነት ፍርድ ቤት እንዲቀርብ በማድረግ እና የተፋጠነ ፍትሕ የማግኘት መብቱን የማስከበር ኃላፊነት እንዳለባቸው በግልጽ ይደነግጋል።

ከዚህ በተጨማሪም፣ የወንጀለኝ መቅጫ ሕግ ሥነ ስርዓት 109(1) ዐቃቤ ሕግ የፖሊስ የምርመራ መዝገብ ተጠናቆ ከቀረበለት ቀን አንስቶ ባሉት 15 ቀናት ውስጥ በተጠርጣሪው ላይ ክስ የመመስረት ኃላፊነትና ግዴታ እንዳለበት የሚገልጽ ቢሆንም፣ ይህንን በመጣስ በእነዚህ ሰዎች ላይ የተፈጸመው ኢሰብኣዊ ድርጊት እንዳሳሰበው የሰብኣዊ መብት ኮሚሽን አስታውቆ ከሦስት ቀን በፊት ከወረዳው ዐቃቤ ሕግ በደረሰን መረጃ መሰረት አቤቱታ አቅራቢዎቹ በ5 ሺሕ ብር ዋስ መፈታተቸውን ሰምተናል እኛም ይህንን የሚያጣራ መርማሪ ቡድን በቀጣዩ ሳምንት ወደ ሥፍራው እንልካለን ሲሉ የኢትዮጵያ ሰብኣዊ መብት ኮሚሽን የአዋሳ ቅርንጫፍ ኮሚሽነር አስቴር ዶሎቾ ለአዲስ ማለዳ ገልጸዋል።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 6 years ago on April 9, 2019
  • By:
  • Last Modified: April 9, 2019 @ 8:50 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar