www.maledatimes.com የታክስ ይግባኝ ኮሚሽን መመሪያ ሊወጣለት ነው - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የታክስ ይግባኝ ኮሚሽን መመሪያ ሊወጣለት ነው

By   /   April 9, 2019  /   Comments Off on የታክስ ይግባኝ ኮሚሽን መመሪያ ሊወጣለት ነው

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 12 Second

ታክስ ይግባኝ ማቅረቢያ ጊዜ የሚራዘምበትና ይግባኙን ዘግይቶ ማቅረብ የሚቻልበት አካሔድን ለመፍጠር በታክስ አስተዳደር አዋጅ መሰረት አዲስ መመሪያ ሊወጣ ነው።

ከገቢዎች ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው በመመሪያው ውስጥ የይግባኝ ባዩ ወይም ወኪሉ የይግባኝ መቅረቢያው ጊዜ ከማለፉ በፊት እንዲራዘምለት በጽሁፍ ለኮሚሽኑ ሊያመለክት የሚችልበት አሰራር ይኖረዋል።

ከዚህ ቀደም አዲስ ማለዳ በቁጥር 17 ዕትሟ የ30 ቀናት የመክፈያ ጊዜ የተሰጣቸው ግብር ከፋዮች፣ በቀነ ገደቡ ሳይጠቀሙ ካለፈ በኋላ ያለአግባብ ግብር ተወስኖብናል በሚል አቤቱታ ወይም ይግባኝ በሚያቀርቡበት ጊዜም እንደ ውዝፍ ዕዳ የሚቆጠር አሰራር መኖሩን መዘገቧ ይታወሳል። በዚህም ሕግ መሰረት በ2011 በጀት ዓመት እስከ ጥር መጨረሻ ድረስ ውዝፍ ዕዳ ተብሎ የተመዘገበ ያልተሰበሰበ ስድስት ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር መኖሩ የሚታወስ ነው።

ይሁን እንጂ በአዲሱ መመሪያ መሰረት ኮሚሽኑ ከይግባኝ ባዩ የቀረበለት የይራዘምልኝ ጥያቄ አሳማኝ መሆኑን ካመነበት እስከ 15 ቀናት ሊያራዝምለት የሚችልበት አሰራር እንዳለውና፤ በይግባኝ ሒደት ላይ የሚገኙ ጉዳዮች እንደ ውዝፍ ዕዳ የማይቆጠሩበት አሰራር እንደሚፈጠር ይጠበቃል።

ከዚህ በተጓዳኝ ደግሞ ዘግይቶ ለሚቀርብ ይግባኝ አቤቱታ አቅራቢው የቆየበትን ምክንያት ማቅረብ የሚኖርበት ሲሆን፤ አሉኝ የሚላቸውን ሌሎች መረጃዎችንም በዝርዝር ማቅረብ እንዳለበት በመመሪያው ተቀምጧል።

ኮሚሽኑም አቤቱታው በደረሰው በሦስት ቀናት ውስጥ መልስ ለይግባኝ ባዩ መስጠት የሚኖርበት መሆኑን መመሪያው የሚደነግግ ሲሆን፤ መልስ ሰጪው በተሰጠው ቀነ ገደብ ምላሽ ካልሰጠ ኮሚሽኑ በቀረበው አቤቱታ ላይ ውሳኔ ይሰጣል። በተጨማሪ ዘግይቶ የቀረበ ይግባኝን ተቀባይነት ለመወሰን ኮሚሽኑ በችሎት ክርክሩን ሊሰማ ይችላል የሚል ድንጋጌ በአዲሱ መመሪያ ላይ ተካቷል።

ከግብር አከፋፈልና አሰባሰብ ጋር በተያያዘ በገቢዎች ሚኒስቴር የተቀመጠው ሕግ እንደሚያመለክተው ግብር ያለአግባብ ተጥሎብኛል የሚል ወገን አቤቱታውን ፍርድ ቤት ድረስ በመውሰድ መክሰስ ይችላል።

አቤቱታቸው በፍርድ ቤት ተጠናቆ እግድ ላይ የደረሱ ግብር ከፋዮች ቁጥር እስከ የካቲት መጨረሻ ድረስ ቁጥራቸው 128 ደርሶ ነበር።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 6 years ago on April 9, 2019
  • By:
  • Last Modified: April 9, 2019 @ 8:57 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar