www.maledatimes.com ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አገር መምራት አልቻሉም! - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አገር መምራት አልቻሉም!

By   /   April 10, 2019  /   Comments Off on ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አገር መምራት አልቻሉም!

    Print       Email
0 0
Read Time:2 Minute, 3 Second

ዶ/ር አብይ መምራት አልቻሉም የውጭ እርዳታን የአመራር ድጋፍን ይሻሉ

ዛሬ በጠቅላይ ሚኒስትሩ እና በፓርቲያቸው ላይ አለማቀፍ ታላላቅ ሚዲያወች ለመጀመሪያ ጊዜ በሚባልበት ደረጃ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አገሪቱን መምራት እንዳልቻሉ በከባድ ነቁፋ ጠቅሰዋል።

ከዛም አልፈው ኢትዮጵያ ወደከባድ መንገድ እያመራች በመሆኑ የውጭ አገራት ጣልቃ ገብነት እርዳታን አስፈላጊ ወደመሆን ደረጃ እንደደረሰ አሳስበዋል

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በገቡት ቃል መሰረት አገሪቱ እየተመራች አይደለም በርካታ የዘር ጭፍጨፋወች አሉ በርካታ ዜጎች እየተገደሉ ነው ሚሊየኖችም ተፈናቅለዋል በሚል የአደጋውን መጠን አሳይተዋል።

ታላቁ ዘሎሳንጀለስ ታይምስ በዛሬ ፅሁፉ የአለም አቀፍ አገራት የውጭ እርዳታ ያስፈልጋል ሲልም አሳሳቡዋል።

ብሎምበርግ በበኩሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በከፍተኛ መጠን አገሪቱ ላይ የሚፈጠሩውን ችግር እያዩ ከባድ የዜጎች ሞት በየቀኑ እየተካሄደ አገሪቱን ወደተሻለ መንገድ የሚመራትን መንገድ ቀርፀው መጉዋዝ አልቻሉም ድህነት በከፍተኛ ፍጥነት እየወረራት ነው የዜጎች መፈናቀል በአንድ አገር የሚፈጥረው ከባድ ቀውስን ዘንግተውታል ሲልም አሳስቡዋል።

የተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ጉዳዮች ኮሚሽነሩ በበኩላቸው ” ኢትዮጵያ ላይ የሚታየው የሰብአዊ ቀውስ ከችግር በላይ ነው አገሪቱ መንግስት አላባ ትመስላለች ንፁሀን በዘራቸው ተለይተው ጭፍጨፋ ተካሂዶባቸዋል በየቀኑ በርካቶች እየሞቱ ነው ይህ በትኩረት ሊታይ ይገባዋል ሲሉ ነው ያሳሰቡት”

የውጭ አገራት እገዛ ያስፈልጋል ያለው ዘሎሳንጀለስን ጨምሮ አገሪቱን እየመራት ያለው መንግስት ዜጎችን በዘር ለይተው ለገደሉ በህግ እንኩዋን አልጠየቀም ሲል የአብይን መንግስት በሰላ ወቀሳ የተቹ ሌሎች ታላላቅ ሚዲያወችም አሉ።

አልጀዚራ በበኩሉ ” ኢትዮጵያ ውስጥ እየተፈጠረ ያለው ጉዳይ ሀያላን አገራት በትኩረት ያዩት ዘንድ አሳስቡዋል”

ከ8.5 ሚልዮን በላይ ዜጎች የአስቸኩዋይ እርዳታን ይሻሉ የጌዲዮ ህዝብ ጉዳይ እስካሁንም እልባት ሳያገኝ በየቀኑ በአሳዛኝ ሁኔታ ዜጎች በረሀብ እየሞቱ ነው ።

በመላ አገሪቱም በከፍተኛ ሁኔታ ቁጣ እየነገሰ ነው የመከላከያን መሳሪያን ታጥቆ የሚገልን ሀይል የአገሪቱ መሪ ዛሬም በዝምታ አልፈውታል።

በአማራ ክልል ወሎ ላይ የተፈጠረው የመንግስት የዘር ማጥፋት ወንጀል እየወጡ ያሉት ከባድ የሰው ዘር ጭፍጨፋ ቪዲዮወች ወደ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን እጅ ደርሰዋል።
የአገሪቱን መከላከያ ሰራዊት አዘው አስገብተው በቀጥታ ዘር አስፈጅተዋል ደብረብርሀን ላይም ወጣቶች በመከላከያ ተገድለዋል።

በመላው አማራ ክልል ቁጣ ነግሱዋል የክልሉን ወሰን ጥሶ በመግባት በመከላከያ መሳሪያ በመታገዝ ንፁሀንን የገደለውን ኦነግን ከመጠየቅ ይልቅ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በእጅ አዙር መከላከያን በማስገባት የዘር ማጥፋት ወንጀል አስፈፅመዋል።

ኢትዮጵያ አሁን ባለችበት መንገድ ከቀጠለች ጣልቃ ገብ ሀያላን አገራት እጃቸውን ሊያስገቡ እንደሚችሉ ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉ ይገልፃሉ።

የአንድ አገር መንግስት በዜጎቹ ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል ሲፈፅም ሲገኝ የተባበሩት መንግስታት የጉዳዩን አሳሳቢነት ካመነበት ሰላም አስከባሪ ጦር በመሀል ያስገባል።

የአብይ መንግስት አሁን ከባድ ችግር እየገጠመው ነው በርካታ ሚሊዮን ዶላር ኢትዮጵያን የሚረዳት የአውሮፓ ህብረትም ጉዳዩ እንዳሳሰበው ገልፁዋል የአሜሪካ መንግስትም ኢትዮጵያ ባላት ኤምባሲዋ በኩል ያለው መረጃ በዶክተር አብይ መንግስት ደስተኛ አለመሆኑ ታይቱዋል።

አሁንም በየቀኑ በርካቶች እየተፈናቀሉ ወደ ድህነት አዘቅት እየወረዱ ነው ይህ ደግሞ ለአገር የሚፈጥረው ጉዳይ ከባድ ነው ።

ኢትዮጵያ የወደቀች አገር ሆናለች በሚል Ethiopia is failed state መሆኑዋንም ይፋዊ መግለጫን ሰተዋል።

https://www.latimes.com/opinion/op-ed/la-oe-horne-ethiopia-abiy-ahmed-democracy-20190408-story.html

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 6 years ago on April 10, 2019
  • By:
  • Last Modified: April 10, 2019 @ 10:31 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar