www.maledatimes.com ፈረንሳዮች ካቴድራላቸውን መልሶ ለመገንባት እየተረባረቡ ነው - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ፈረንሳዮች ካቴድራላቸውን መልሶ ለመገንባት እየተረባረቡ ነው

By   /   April 16, 2019  /   Comments Off on ፈረንሳዮች ካቴድራላቸውን መልሶ ለመገንባት እየተረባረቡ ነው

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 9 Second

ጴጥሮስ አሸናፊ እንደጻፈው

በአሳዛኝ ሁኔታ በትናንትናው ዕለት የመቃጠል አደጋ የደረሰበትን ታሪካዊው የፓሪሱን ካቴድራል ኖትር ዳም በፍጥነት መልሶ ለመገንባት ፈረንሳዮች በመረባረብ ላይ ናቸው። እስካሁን ከሁለት ፈረንሳያዊ ባለሀብቶች ብቻ 300 ሚሊዮን ዩሮ ቃል ተገብቷል።

የቤርናር አርኖ ቤተሰቦች 200 ሚሊዮን ዩሮ ለመስጠት ቃል ገብተዋል። አርኖ የዝነኞቹ ሉዊ ቩይቶ ( Louis Vuitton)፣ ክርስቲያን ዲዮር እና ዢቮንሺ (Givenchy)ምርቶች አምራችና ባለቤት የሆነው LVMH ዋና ስራ አስፈፃሚና ቢሊዬነር ነው።
የጉቺና የሌሎች ፋሽን ምርቶች ባለቤት ሌላው ቢዬየነር ፍራንሷ ኦንሪ ፒኖ ለመልሶ ግንባታው 100 ሚሊዮን ዩሮ እንደሚሰጥ ቃል ገብቷል። ፒኖ ቃል የገባው በፒኖ ቤተሰቦች የበጎ አደራጎት ድርጅት በሆነው በአርቴሚስ ፋንድ በኩል ነው።
አርኖ በአለማችን 3ኛው ባለሃብት ሲሆን የሃብት መጠኑም 90.4 ቢሊዬን ዶላር ይደርሳል። ሌላኛው ፈረንሳዊ ቢሊዬነር ፒኖም 37.3 ቢሊዬን ዶላር ሃብት ያለውና የታዋቂዋ የፊልም አክትረስ ሳልማን ሃዬክ ባለቤት ነው።

”ካቴድራላችንን መልሰን እንገነባዋለን፣ ኖትር ዳም የታሪካችን አካል ነው። የፈረንሳይ ሕዝብ የሚጠብቀውም ይህንኑ ነው” ያሉት የሃገሪቱ ፕሬዚዳንት ኤማኑኤል ማክሮን መልሶ ግንባታውን በቅርብ የሚከታተልና ድጋፍ የሚያሰባስብ ዐቢይ ኮሚቴ በቅርቡ ስራ እንደሚጀምርም ተናግረዋል።

“ኖትር ዳም የፈረንሳይ ታሪካዊ ምልክት፣ በዋጋ የማይተመን የአውሮፓውያና የአለም አቀፍ ባህል አንጡራ ሃብት፣ የክርስቲያኖች ደግሞ ልዩ ቤተመቅደስ ነው” ያሉት የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን፤ ካቴድራሉን እንደገና መገንባት የሚቻል በሚሆኑ ሩሲያ ያሏትን ምርጥ የስነ ህንጻ ባለሙያዎች ወደ ፓሪስ ለመላክ ዝግጁ መሆኗን አሳውቀዋል።

ኖትር ዳም በመቃጠል ላይ እንዳለ በትዊተር ገፃቸው መልዕክት ያስተላለፉት የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በደረሰው አደጋ ማዘናቸውን ገልፀው የፈረንሳይ የእሳት አደጋ ባለሙያዎች በፍጥነት ” በራሪ የውሃ ታንከሮችን ተጠቀሙ” የሚለው ምክር አዘል መልዕክታቸው ግን ድጋፍና ትችት እያስከተለ ይገኛል።

Image may contain: 2 people, people standing

Image may contain: night

Image may contain: 2 people, people smiling

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 6 years ago on April 16, 2019
  • By:
  • Last Modified: April 16, 2019 @ 11:57 am
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar