በቃሊቲ ፍረኞች ላይ ፖሊስ ግቢውን ሰብሮ በመግባት ጥቃት መፈጸሙን ተገለጸ ።
የአዲስ አበባ ፖሊስ ከኦሮሚያ ፖሊስ ጋር በመተባበር የማረሚያ ቤቱን ህግ እና ደንብ በመጣስ ከማረሚያ ቤቱ አዛዥ ጀርባ በተደረገ ደባ ወጣት ታራሚ እስረኞችን ስርአተ ጸሎት በሚያደርጉበት መስጅድ ውስጥ ዘልቆ በመግባት በንጹሃን ዜጎች ላይ ድብደባ ማድረጋቸው ተገልጿል ።
መነሻው ምንም ያልታወቀው እና ያልተጣራው ይሄው ጥቃት የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽንን ሊያስጠይቀው ይገባል በህግ ፊት ሊቀርብ እና አቤቱታውን ማሰማት አለበት ሲሉ የፍርደኞች ቤተሰቦች ገልጠዋል።
ብዙ እስረኞች የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው የተጠቆመ ሲሆን ሁለት ሰዎች መሞታቸውንም እስከአሁን የደረሰን መረጃ ይጠቁማል ።
ባለፈው ወር እስረኞች እርስ በእርስ በመደባደብ ብዛት ያላቸው እስረኞች መሞታቸው የሚታወቅ ሲሆን እስረኞችንም ሆነ በማረሚያ ቤት አስተዳደር ይህ ጉዳይ እንዳይታወቅ የሸፋፈኑት እና መገናኛ ብዙሃኖች እንዳይዘግቡት ከፍተኛ ጥረት ሲደረግ መክረሙን ከውስጥ ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል።
በአዲስ አበባ ኮሚሽን ስር የሚተዳደረው የቃሊቲ እስርቤት ብዙሃኖችን በማሰቃየት እና ለሞት በመዳረግ ከሚታወቁት ትልልቅ አሰቃቂ እስርቤቶች ውስጥ ግንባር ቀደሙን እንደሚወስድ የደረሰን መረጃ ያጠናክራል።
በተለይም በዞን አንድ እና ሁለት የሞት ፍርደኞች እና የእድሜ ልክ ፍርደኞች ላይ የሚበዛው ሰቆቃ ሰፊ እንደሆነ እና በፖሊሶች ድብደባ ብዙዎቹ ህይወታቸው እንደሚያልፍ እስረኞች አዲስ አበባ ለሚገኘው ለማለዳ ታይምስ ዘጋቢ አሳስበዋል።
Wondering where the comments are? We encourage you to use the share buttons below and start the conversation on your own!
- Click to email a link to a friend (Opens in new window)
- Click to share on Facebook (Opens in new window)
- Click to share on Twitter (Opens in new window)
- Click to share on LinkedIn (Opens in new window)
- Click to share on Pinterest (Opens in new window)
- Click to share on Tumblr (Opens in new window)
- Click to print (Opens in new window)
Average Rating