ይልቅ ወሬ ልንገርህ –
የአልኮል መጠናቸው ከሁለት ከመቶ በላይ የሆኑ መጠጦችን የሚያስተዋውቁ የቢራ ማስታወቂያዎች በስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራ ላይ እንዳይሸጡና እንዳይተዋወቁ የሚከለክለውና በቅርቡ የጸደቀውን አዋጅ ተከትሎ በአዲስ አበባ ስታዲየም ዙሪያ ያሉ መጠጥ ቤቶች እንደሚታሸጉ አልያም ወደ ሌላ የንግድ ዘርፍ እንዲቀይሩ እንደሚደረግ ተገለፀ፡፡
በባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ስር የሚገኘው ስፖርት ኮሚሽን አዋጁን ተከትሎ በስታዲየም አካባቢ ያለውን የመጠጥ ማስታወቂያና መጠጥ ቤቶች ላይ ለምን እርምጃ እንዳልተሰደ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት የተጠየቁት የኮሚሽኑ የስራ ሀላፊዎች አዋጁ ከወጣ አጭር ጊዜ መሆኑን ጠቅሰው ነገር ግን በስታዲየም ዙሪያ ያሉ መጠጥ ቤቶችን ያከራየው እግር ኳስ ፌዴሬሽኑ በመሆኑ አዋጁ ከአንድ ወር በኋላ ተግባራዊ መሆን ሲጀምር በህግ አግባብ ውሉን እንዲያስፈፅም እየተነጋገርን ነው ብለዋል፡፡
በህጉ መሠረት የአልኮል መጠጥ ንግዳቸውንና የቢራ ማስታወቂዎቻቸውን ከስታዲየም ዙሪያ ውጭ ለማድረግ ፍቃደኛ ያልሆኑ ተከራዮችን ውል በማቋረጥ የማሸግ እርምጃ እንደሚወሰድ ከሀላፊው ገለፀ ለመረዳት ተችሏል፡፡
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከሄኒከን ኢትዮጵያ ጋር ለብሔራዊ ቡድኑ ድጋፍ ለማድረግ የ56 ሚሊዮን ብር የስፖንሰር ሽፕ ስምምነት ለመጪዎቹ አምስት ዓመታ ለማድረግ በቅርቡ መስማማቱ ይታወሳል፡፡
Wondering where the comments are? We encourage you to use the share buttons below and start the conversation on your own!
- Click to email a link to a friend (Opens in new window)
- Click to share on Facebook (Opens in new window)
- Click to share on Twitter (Opens in new window)
- Click to share on LinkedIn (Opens in new window)
- Click to share on Pinterest (Opens in new window)
- Click to share on Tumblr (Opens in new window)
- Click to print (Opens in new window)
Average Rating