www.maledatimes.com ሽብርተኛ የተባሉ 37 ዜጎች አንገት ተቀላ ! - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ሽብርተኛ የተባሉ 37 ዜጎች አንገት ተቀላ !

By   /   April 24, 2019  /   Comments Off on ሽብርተኛ የተባሉ 37 ዜጎች አንገት ተቀላ !

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 1 Second

የመረጃ ግብአት ፣
==========================
* የሳውዲ መንግስት ብርቱ ቅጣት

ሳውዲ አረቢያ በከፍተኛ የሽብርተኝነት ወንጀል የተፈረደባቸውን 37 ዜጎችዋን አንገት መቅላቷን በያዝነው ሳምንት አስታውቃለች ። ማክሰኞ ሚያዝያ 15 ቀን 2011 ዓም ከመገናኛ ብዙሃን የተሰራጨው መረጃ እንደሚያስረዳው 37 የሳውዲ ዜጎች አንገታቸው የተቀላው በዋና ከተማዋ በሪያድ በመካ በመዲና በቀሲምና በአሲር ግዛቶች መሆኑ በሀገር ውስጥ ሚኒስቴር መግለጫ ተጠቁሟል ።

ሽብተኝነትን በማስፋፋት ሙስና ፤ ሁከትና ረብሻን በማስፋፋትና ብሎም የሰላማዊ ዜጎችን ደህንነት በሚያውክ እንቅስቃሴ በመሰማራት ፤ በደህንነት ተቋማትነ ኢላማ ያደረገ ፍንዳታ ንብረት በማውደም ፣ በጸጥታ አስከባሪዎች ላይ የግድያ ወንጀል በመፈጸም ተከሰው በሸሪአው ህግ መሰረት አምገታቸውን በመቅላት እንደተላለፈባቸው የሀገር ውስጥ ሚኒስቴር መግለጫ ያስረዳል ። ከ37ቱ
መካከል አንዱ የፈጸመው ወንጀል የከፋ መሆኑ በመረጋገጡ አንገቱ ከተቀላ በኋላ በድኑ ተሰቅሎ እንደነበርም መግለጫው አክሎ አስታውቋል ። “ … one person was crucified after his execution, a punishment reserved for particularly serious crimes”

ከሁለት አመታት በፊት ታህሣሥ ወር 2008 ዓም የአልቃኢዳ የሽብር ጥቃት ላይ ተሰማርተዋል የተባሉ 47 ሰዎች አንገታቸው ተቀልቶ ተመሳሳይ የሞት ቅጣት እንደተላለፈባቸው ይታወሳል ። እአአ ከ2003 እስከ 2006 ዓም በ12 የሳውዲ የተለያዩ ከተሞች ንጹሃንን ኢላማው ባደረገ የሽብር ጥቃት ተሰማርተዋል በሚል አንገታቸው ከተቀሉት 47
ሰዎች መካከል 1 ግብጻዊና 1 ቻዳዊ ዜጎች የሚገኙበት ሲሆን የቀሩት ሲሆኑ አብዛኛው 45ቱ የሳውዲ ዜጎች ነበሩ ። ከ45 ሳውዲዎች መካከልም በምስራቅ የሳውዲ ክፍል በሚገኙ የሸዓ እስልምና ተከታዮች ዘንድ ታዋቂ የነበሩት የሐይማኖት መሪ ኒማር አል ኒማር አንገታቸው መቀላቱ ይታወሳል ።

Image may contain: outdoor

ቸር ያሰማን !

ነቢዩ ሲራክ
ሚያዝያ 16 ቀን 2011 ዓም

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 6 years ago on April 24, 2019
  • By:
  • Last Modified: April 24, 2019 @ 11:52 am
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar