www.maledatimes.com የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕረዚደንት ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ አረፉ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕረዚደንት ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ አረፉ

By   /   April 27, 2019  /   Comments Off on የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕረዚደንት ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ አረፉ

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 56 Second

የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራቲክ ሪፖብሊክ ፕረዚደንት የነበሩት ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ በአደረባቸው ህመም ምክንያት በህክምና ሲረዱ ቆይተው ዛሬ ማረፋቸውን መረጃ ምንጮቻችን ዘግበዋል።

በወርሃ መስከረም ፰ ፲፱፴፭ አመተ ምህረት በቀድሞው ወለጋ ክፍለ ሃገር በደምቢ ዶሎ የተወለዱት ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ በምእራባዊቷ የኢትዮጵያ ክፍል መሆኑን መረጃዎች ይጠቁማሉ ።

ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ በቀዳማዊ ሃይለስላሴ ዩኒቨርሲቲ የተማሩ ሲሆን ከ፲፱፭፰ -፩፱፷፫ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቅጥር ግቢ ተማሪ ሆነው የቆዩ ሲሆን ከዚያም በመቀጠል ከ፲፱፷፫ -፲፱፮፯ አመተ ምህረት ድረስ በአይራ በምእራብ ወለጋ በሚገኘው ትምህርት ቤት የትምህርትቤቱ ዳይሬክተር በመሆን አገልግለዋል የታሪክ አስተማሪም እንደነበሩ የህይወት ታሪካቸው ያስረዳል። ከዚያም በመቀጠል በ፲፱፷፯ አመተ ምህረት ወደ ጀርመን ያቀኑ ሲሆን ትምህርታቸውን በመከታተል ሲቆዩ እዚያው ጀርመን በቆዩበት ወቅት የጀርመናዊ ዜግነት ያላቸውን ባለቤታቸውን አግብተው ኑሮ የመሰረቱ መሆኑን መረጃዎች ይጠቁማሉ። ዶክተር ነጋሶ እስከ ፲፱፹፫ አመተ ምህረት ድረስ በጀርመን ቢቆዩም ከዚያም ወደ ፍራንክ ፈርት በማቅናት በታሪክ ዲፓርትመንት የባህርይ ጥናት ላይ በማተኮትር የዕያንዳንዱን ሰው የባህርይ ጥናትን በጄ -ደብሊው ጋርታ ( J.W.Goethe University ) ዩኒቨርሲቲ ጥናአት አድርገዋል ። (Goethe ጋርታ ተብሎ ይነበብ ትክክለኛው አጠራር ይህ ሰለሆነ ነው !ብዙዎቻችን ጎቴ ብለን ልናነብ እንችላለን ይህ ስህተት ነው )

በጀመን ቆይታቸው ወቅት አንድ ሴት ልጅ ወልደው እንደነበረም ይታወቃል። መረጃው የማለዳ ታይምስ ብቻ ነው !

ነጋሶ ጊዳዳ ምስል በአዲስ ስታንዳርድ

በ፲፱፹፫ አመተ ምህረት ጀርመንን በመልቀቅ ወደ ኢትዮጵያ በማቅናት የህወሃት የዝንጀሮ ተዋጊ (ጉሬላ ታጋይ ) የሆኑንት በመቀላቀል ወደ ሃገራቸው የገቡ ሲሆን በኦሮሞ ስም ህወሃት አዋቅሮት የነበረውን ኦፒዲኦን በመምራት እና በስራ አመራር እና አገልግሎት ላይ ቆይተዋል ;

በአስራ ዘጠኛውም የመካከለኛ ክፍለ ዘመን ጀምሮ እስከ መገባደጃው ድረስ ነጋሶ ለሃገራቸው ካበረከቱት በላይ የመሰረተ ድንጋይ የጣሉት የሃገሪቱን ህገመንግስት ከሚያረቁት መካከል ሰዎች ተመርጠው ሲሰሩ የቆዩ መሆናቸው ነው ፣ ህገ መንግስቱን በመንደፍ የሰሩት ታላቅ አመርቂ ውጤት ቢኖርም ህወሃትን በሚጠቅም መልኩ ህገ መንግስቱ መነደፉ ዛሬ ኢትዮጵያ ላለችበት አጣብቂኝ እንደዳረገው ቀደም ብለው የተናገሩት የህገመንግስቱን ስህተት እምን ላይ እንደነበር ወደ ኋላ መለስ ብሎ ማየት ይቻላል። ከሰሯቸው ስራዎችም ውስጥ ስህተት እንደነበረው ቢያምኑም ያንን ስህተቶቻቸውን ለማረም ቆርጠው ከህዝብ ጎን ለመሰለፍ የበቁ ጠንካራ ፕረዚዳንት ነበሩ።

የህገመንግስቱን አሴምብሊ በመምራት የቆዩ ሲሆን በ፲፱፹፯ አመተምህረት የሃገሪቱ መሪ በመሆን በፕረዚዳንትነት አገልግለዋል ከዚያም በእራሳቸው ጊዜ መንግስቱን ለቀው የወረዱ ሲሆን ፣ በመለስ አስተዳደር ከፍተኛ ግፍ ከተፈጸመባቸው እና ሃገራቸውን በቀና ካገለገሉ ፕረዚዳንቶች ግንባር ቀደሙን የሚወስዱት ነጋሶ ጊዳዳ ብቻ ናቸው ። በ፲፱፺፯ አመተ ምህረት በህወሃት መንግስት ለአገልግሎታቸው ይሰጣቸው የነበረው ጡረታ እና ከምንግስት ይሰጣቸው የነበረው ጥቅማ ጥቅም ከነ ሙሉ መብታቸው ህወሃት መንግስት (ሟቹ ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ እንዳስነጠቃቸው ይታወሳል) ለዚህም በሰሯቸው የህገመንግስት ረቂቅ አዋች እና በመሯቸው አሴምብሊዎች ሊታወሱ የሚገባ ሲሆን ከቅርብ ጊዜም በኋላ በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ አማካሪ በመሆን ህይወታቸው እስከ አለፈበት ወቅት ድረስ ህዝባቸውን ሲያገለግሉ ቆይተዋል።

ይህንን ኮፒ ከማለዳ ታይምስ ውጭ የሚያትም በህግ ይጠየቃል!!

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 6 years ago on April 27, 2019
  • By:
  • Last Modified: April 27, 2019 @ 12:24 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar