www.maledatimes.com ከ72 በላይ ኢትዮጵያዊያንን የያዘ ጀልባ የመን ድንበር አቅራቢያ ሰመጠግሩም ተ/ሀይማት - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ከ72 በላይ ኢትዮጵያዊያንን የያዘ ጀልባ የመን ድንበር አቅራቢያ ሰመጠ ግሩም ተ/ሀይማት

By   /   November 3, 2012  /   Comments Off on ከ72 በላይ ኢትዮጵያዊያንን የያዘ ጀልባ የመን ድንበር አቅራቢያ ሰመጠ ግሩም ተ/ሀይማት

    Print       Email
0 0
Read Time:4 Minute, 25 Second
      በአመት ከሁለት ሺ በላይ ኢትዮጵያዊያን እንደሚሞቱ IOM የገለፀበት ገልፍ ኦፍ አደን ባህረ ሰላጤ ላይ ከሶስት ቀን በፊት 72 ኢትዮጵያዊያን እንደሞቱ ተረጋገጠ፡፡ ከሶማሊያዋ ቦሳሶ ወደብ የተነሱ ሁለት ስደተኞችን የጫኑ ጀልባዎች ከነጫኑት ሰው ሰመጡ፡፡ በዚህ የመስመጥ አደጋ የሞተው ሰው ቁጥር በትክክል የማይታውቅ ሲሆን ለጊዜው ባህሩ ላይ ሬሳቸው የተለቀመ እና ባህሩ ዳር ተፍቶት የተገኘ ሲሆን ከዛ ውስጥ 72 ኢትዮጵያዊያን መሆናቸውን ታውቋል፡፡ ሸቡዋ የተባለው የየመን ጠረፍ ላይ ለመድረስ ጥቂት ሲቀረው እንደሰመጠ የተነገረው ይህ ጀልባ ምን ህል ሰው እንደጫነ አልታወቀም፡፡ እኛ ስንጓዝ በምናውቀው ምን ጊዜም የሚጭኑት ከአንድ መቶ ላይ ሰው ነው፡፡ ሁለተኛው ጀልባ ይስመጥ አይስመጥ እስካሁን የታወቀ ነገር የለም፡፡ መግባታቸውም አልተረጋገጠም፡፡
     የየመን መንግስት ባለስልጣናት ከዚህ በኋላ በህገ-ወጥ መንገድ የሚገቡት ላይ ጥብቅ ቁጥጥር እናደርጋለን ብለዋል፡፡ ይህንን አባባላቸውን 2011 መግቢያ ላይ ከጅቡቲ በጀልባ ሲገቡ በ3 ቀናት ልዩነት ሶስት ጀልባዎች ሲሰምጡ ተናግረውት እንደነበር ይታወሳል፡፡ ተመሳሳይ ነገር ቢናገሩም ስደተኞችን ክፍት በተተወ ድንበር ህገ-ወጥ አጓጓዦች እንደልብ እያስገቡበት በመሆኑ በአመት እስከ 75 ሺህ ስደተኞች ወደ የመን እንደሚገቡ አለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት መግለጹ ይታወሳል፡፡ ይህ ችላ ባይነት በየመን መንግስትም ሆን በኢትዮጵያ መንግስት በመታየቱ ከባህር መስመጥ አልፈው የሚገቡት ኢትዮጵያዊያን ላይ በተደራጀ ሁኔታ የማፈን እና 5000 የኢትዮጵያ ብር ከቤተሰብ ማስላክ አለበለዚያ ታጋቹ ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረስ የተለመደ ሆኗል፡፡
       ይህ ከሶማሊያዋ ቦሳሶ አነስተኛ ወደብ የሚነሳው የህገ-ወጥ አዘዋዋሪዎች ጀልባ አደጋው የደረሰበት በአየር መዛባት የተነሳ ሀይለኛ ንፋስ /ማዕበል/ ምክንያት እንደሆነ ታውቋል፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ የዛሬ ሳምንት ከየመን ወደ ሳዑዲ አረቢያ ሲጓዙ የነበሩ ሰዎች ላይ በተከፈተ ተኩስ ሰዒድ የሚባል ኢትዮጵያዊ ህገ-ወጥ አጓጓዥ ጨምሮ ሶስት ኢትዮጵያዊያኖች መሞታቸው ታውቋል፡፡
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on November 3, 2012
  • By:
  • Last Modified: November 3, 2012 @ 12:15 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar