www.maledatimes.com እህ.ህ ወይ ነዶ!!!! - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

እህ.ህ ወይ ነዶ!!!!

By   /   November 4, 2012  /   1 Comment

    Print       Email
0 0
Read Time:2 Minute, 30 Second

 እህ.ህ ወይ ነዶ!!!!

ከማተቤ መለሰ ተሰማ

አያበሳጭም ወይ እስኪ እየው ወገኔ፣

ተባለኮ አማራ ሽንታም በወያኔ፡

ይታይህ ያገር ልጅ ይህን የግፍ ስራ፣

ስው እንዲህ በዘሩ ሲሰደብ ሲአራ፡

እንዲህ ጉድ ይሰማል፡ እናንት ወይ ነዶ፣

ተሰደበ አማራ በቋንቋው ተዋርዶ፡

እርር ድብን ብሎ ተቃጠለ አንጀቴ፣

ስው እንዲሀ በዘሩ ሲናቅ በማየቴ፡

ምነው አይቆረቁር አይገባ አጥንት ሰብሮ፣

ጀግናው ፈሪ ሲባል በባንዳ ደነቆሮ፡

ማንም የማይክደው ነበር ታሪክ ሰሪ፣

የሀገሩን ድንበር በህይወቱ አጣሪ፡

የሚዋረድበት እንዲህ በእየለቱ፣

ምንድን ይሆን ከቶ አማራ ጥፋቱ?

ለሀገሩ ክብር ከምር በታገለ፣

ዛሪ በከፋፋይ ሽንታም ነህ ተባለ፡

ከመንቋሸሽ በላይ ሰው እንዲህ በዘሩ፣

ምን መጥፎ ይመጣል እስኪ ተናገሩ፡

በቃ ተነስ እንጅ ምን ትጠብቃለህ፣

እንዴት በጠቅላላ ሽንታም ትባላለህ፡

ትግስትህ ከፍራት እንደዚህ ተቆጥሮ፣

ፈሪነህ ስትባል ተቀበልከው ድሮ?

ሞራልን የሚገድል የሚያስደፋ አንገት፣

ከዚህ የመረረ ምን ይምጣ ውርደት?

እንቢ በል!!! አማራ  አሁን በቃ ብለህ፣

እስከመቸ ድረስ ቆመህ ተሞታለህ?

በአንተ የደረሰው ነውና የሞት ሞት፣

ከእንግዴህ ተነሳ ይበቃል ዝም ማለት፡

ከእንግዴህ ተነሳ ይበቃል ዝም ማላት።

 

ኢሜልmatebemelese@yahoo.com

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%

One thought on “እህ.ህ ወይ ነዶ!!!!

  1. Dr.Matebe this poem is not from you I know you.Where are you coming
    you are comiming from Arebegnch Ginbar yes as you told us but that is not true .You have a big family in Norway I know.Any way you better stop asking telefon number from all Ethiopia women.Nex time I will writ about your story.

Comments are closed.

<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar