www.maledatimes.com የአሜሪካ ምርጫ አጭር ታሪክ (ጥንቅር በአድማስ ሬዲዮ – አትላንታ፣ ጆርጂያ) - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የአሜሪካ ምርጫ አጭር ታሪክ (ጥንቅር በአድማስ ሬዲዮ – አትላንታ፣ ጆርጂያ)

By   /   November 4, 2012  /   1 Comment

    Print       Email
0 0
Read Time:13 Minute, 57 Second

(ጥንቅር በአድማስ ሬዲዮ – አትላንታ፣ ጆርጂያ)

የአሜሪካ መስራች አባቶች ፣ አሜሪካኖች የገዛ መሪያቸውን በቀጥታ መምረጥ የሚችሉበትን ስርዓት የዘረጉት በ 1789 ዓ.ም ነበር። ያን ጊዜ ፣ በዚሁ ስርዓት መሰረት ጆርጅ ዋሽንግተን የመጀመሪያው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ሆነው ተመረጡ። ያን ጊዜ መምረጥ የሚችሉት ታዲያ ንግድ ቤት ያላቸው ነጮች ብቻ ነበሩ። በኋላ ላይ በ15ኛው፣  በ19ኛው እና በ26ኛው የህገመንግስቱ አንቀጾች ላይ ማሻሻያ ተደርጎ እድሜው 18 ዓመት የሞላው አሜሪካዊ ሁሉ መምረጥ እንዲችል ሆነ።  በዚሁ መሰረት በ1792  ጆርጅ ዋሽንግተን እንደገና ተመረጡ። የሚገርመው ግን ጆርጅ ዋሽንግተን ሲመረጡ እንዳሁኑ ጊዜ በምረጡኝ ዘመቻ ሳይሆን “እባክዎ እሺ ይበሉ- እምቢ ማለት ነውር አይደለም እንዴ?” ተብለው ተለምነው ነበር።
በ1796 ጆን አዳምስ ለውድድር ሲቀርቡ ለመጀመሪያ ጊዜ ተፎካካፊ ተገኘ፣ ያም ቶማስ ጀፈርሰን ነበር። ያን ጊዜ የነበሩት ፓርቲዎች ፌዴራሊስት እና ሪፓብሊካን ይባሉ ነበር፣ እናም 71-68 በሆነ ድምጽ ጆን አዳምስ ከፌዴራሊስት ፓርቲ አሸንፈው ፕሬዚዳንት ሆኑ፣ የሚገርመው ግን ተፎካካሪያቸው ሪፓብሊካኑ ቶማስ ጀፈርሰን ምክትል ፕሬዚዳንት ነበር የሆኑት።
በ1800 እንደገና ጆን አዳምስ እና ቶማስ ጀፈርሰን ተወዳዳሪ ሆነው ቀረቡ፣ አሁን ቶማስ ጀፈርሰን አሸነፉ። ቶማስ ጀፈርሰን ለሁለተኛ ጊዜ በ 1804 ተወዳድረው እንደገና ፕሬዚዳንት ሆኑ …፣ የፕሬዚዳንት ምርጫውም በየ 4 ዓመቱ እየተደረገ ቆየ።
ወደ 1820 እንምጣ።
በ1816 ዓ.ም የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ሆነው የተመረጡት ጀምስ ሞኖሬ፣ በ1820 ድጋሚ ሲወዳደሩ ሊቀናቀናቸው የቀረበ ተወዳዳሪ አልነበረም። ስለዚህ በቀጥታ ፕሬዚዳንት እንዲሆኑ ድምጽ ተሰጣቸው። ከአንድ ድምጽ በቀር የ231 ምክር ቤት አባላትን ድምጽ በማግኘት ተመረጡ። ያን ጊዜ ሌላ ፕሬዚዳንት ለውድድር ያልቀረበው አገሪቷ በትልቁ የኢኮኖሚ ድቀት  (Great Depression) ወቅት ላይ ስለነበረች ይሆን?
በ1824 አራት ተወዳዳሪዎች ለፕሬዚዳንትነት ቀረቡ፣ ጆን አዳምስ፣ ሄንሪ ክሌይ፣ አንድሪው ጃክሰን እና ዊሊያም ክራውፎርድ ነበሩ። የተሰጠው ድምጽ ሲቆጠር ለፕሬዚዳንትነት የሚያበቃ ድምጽ አንዳቸውም ሳያገኙ ቀሩ፣ ስለዚህ ምክር ቤቱ በድምጽ ብልጫ እንዲወስን ተደረገ። በተለይ የምክር ቤቱ አፈ ጉባዔ ሄንሪ ክሌይ የሚሰጡት ድምጽ ወሳኝ ነበር። ምንም እንኳን ራሳቸውም ከተወዳዳሪዎቹ አንዱ ቢሆኑም፣ ራስን መምረጥ አይቻልምና ለጆን አዳምስ ድምጻቸው ሰጡ፣ ጆን አዳምስ ፕሬዚዳንት ሆኑ። ይህ ወቅት ሪፓብሊካን ፓርቲ ለ 4 የተከፈለበት ወቅት ተብሎም ይታወቃል።
በ1828 ዓ.ም የሪፓብሊካን ፓርቲ ከአራት ቦታ ክፍፍል ወደተጠናከረ ሁለት ክፍፍል መጣ፣ አንደኛው ሪፓብሊካን ሆኖ ሲቀር፣ ሌላኛው ዲሞክራት ሪፓብሊካን እያለ ራሱን መጥራት ጀመረ፣ ጥቂት ቆይቶም ዲሞክራት በሚለው እየታወቀ መጣ። በዚሁ ዓመት የመጀመሪያው ዲሞክራት ሆኖ አንድሪው ጃክሰን ተመረጠ።

ትንሽ ወደፊት እንሂድና 1860 ላይ ቆም እንበል፡
ይህ ዓመት ለየት ያለ ታሪክ አለው። በ1860 ምርጫ ለውድድር የቀረቡት አብርሃም ሊንከን፣ ስቴፈን ዳግላስ እና ጆን ብሪክሪጅ ነበሩ። አብርሃም ሊንከን ሪፓብሊካን ፓርቲን ወክሎ ሲወዳደር፣ የቀሩት ሁለቱ ግን የዲሞክራት ፓርቲ ተወካዮች ነበሩ። ይህም የሆነው ዲሞክራቶች በወቅቱ በአንድ ተወዳዳሪ ምርጫ ላይ መስማማት ባለመቻላቸው ሁለት ቦታ ተከፍለው ስብሰባቸውን (ዛሬ ኮንቬንሽን) የምንለውን አደረጉትና ሁለት ተወዳዳሪ አመጡ። በዚህ ምክንያት የዲሞክራቶች ድምጽ በመከፋፈሉ አብርሃም ሊንከን አሸነፉ። በሚቀጥለውም ምርጫ አብርሃም ሊንከን ድጋሚ አሽነፉ።
አሁንም ወደፊት ሄደናል፣….. 1896 ላይ ሪፓብሊካን ፓርቲ ሁለት ቦታ ተከፍሎ ሪፓብሊካን እና ሲልቨር ሪፓብሊካን ሲሰኝ፣ ዲሞክራቶቹም ለሁለት ተከፍለው፣ ዲሞክራት እና ጎልድ ዲሞክራት ተባባሉ ስለዚህም አራት ተወዳዳሪዎች ለፕሬዚዳንትነት ቀረቡ፣ ሪፓብሊካኑ ዊሊያም ማኬንሊም አሸነፉ። 1900 á‹“.ም ላይ ዊሊያም ማኬንሊ ድጋሚ አሸነፉ። በኋላ ላይ ግን እኚሁ ዊሊያም ማኬንሊ በሰው እጅ ተገደሉ።
በ1904 ቲኦዶር ሩዝቬልት እና አልተን ፓርከር ተወዳደሩ፣ ሩዝቬልት ሪፓብሊካን ሲሆኑ ፓርከር ዲሞክራት ነበሩ፣ ጥሩ ክርክርም አደረጉ፣ ሪፓብሊካኑ ሩዝቬልትም አሸነፉ። በሚቀጥለው ምርጫ ግን ሩዝቬልት ደጋሚ አልወዳደርም በማለታቸው ሌላው ሪፓብሊካን ዊሊያም ታፍት ተወዳደረው አሸነፉ።
በ1932 á‹“.ም ፍራንክሊን ሩዝቬልት እና ለሁለተኛ ጊዜ ፕሬዚዳንት ለመሆን ኽርበርት ሁቨር ተፎካካሪ ሆነው ቀረቡ። ዲሞክራቱ ፍራንክሊን ሩዝቬልት ተመረጡ።፡ ፍራንክሊን ሩዝቬልት እንደገና በ1936 ድጋሚ ተወዳደሩና አሸነፉ። ይህም ብቻ አይደለም፣ እንደገና በሚቀጥለውም ምርጫ ለሶስተኛ ጊዜ የተወዳደሩት ፍራንክሊን ሩዝቬልት ለሶስተኛ ጊዜ አሸንፈው አሁንም ፕሬዚዳንት ሆኑ። á‹« ጊዜ በዓለማችን ሁለተኛው የአለም ጦርነት የተጀመረበት ወቅት ነበር። አስገራሚ ነገር፣ በ 1944 ሩዝቬልት ለ 4ኛ ጊዜ ፕሬዚዳንት ለመሆን ተወዳደሩ፣ ምክትላቸውን በሃሪ ትሩማን ቀየሩ – እናም ምርጫውን አሸንፈው ለ 4ኛ ጊዜ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ሆኑ።  በወቅቱ 62 ዓመታቸው የነበረው ሩዝቬልት የጤናቸውም ጉዳይ ተጨምሮ፣ አንድ ፕሬዚዳንት 4 ጊዜ መወዳደር መቻሉ ጥያቄ እያስነሳ ሄደ።
ፌብሩዋሪ 27/1951 ዓ.ም በጸደቀውና በተሻሻለው የአሜሪካ ህገመንግስት 22ኛ ማሻሻያ መሰረት ማንም ሰው ለአሜሪካ ፕሬዚዳንትነት ከሁለት ጊዜ በላይ እንዳይወዳደር ህግ ሆነ። ከዚያ በኋላ በ1952 እና በ1956 ዲዋይት አይዘናወር ሁለት ጊዜ አሸንፈው ፕሬዚዳንት ሆነዋል። በ1968 እና በ 1972 ፕሬዚዳንት ሪቻርድ ኒክሰን ሁለት ጊዜ በተከታታይ አሸንፈው ፕሬዚዳንት ሆነዋል። በ1976 ጂሚ ካርተር አንድ ጊዜ አሸንፈው ፕሬዚዳንት ሲሆኑ፣ በ 1980 እና 84 ሮናልድ ሬገን ሁለት ጊዜ አሸንፈዋል። በ 1988 ትልቁ ቡሽ  አንድ ጊዜ አሸነፉ፣ በ1992 በቢል ክሊንተን ተሸነፉ፣ ቢል ክሊንተን በበኩላቸው በ 1996 ዓ.ም እንደገና አሸነፉና የሁለት ጊዜ ፕሬዚዳንት ሆኑ።
በ2000 ትንሹ ቡሽ ፣ እንደገና በ2004 ዓ.ም እንዲሁ ድጋሚ አሸንፈው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ሆኑ። በመጀመሪያው ከአልጎር ጋር በሁለተኛው ከጆን ኬሪ ጋር ነበር የተጋጠሙት። በ 2008 ዓ.ም ባራክ ኦባማ ና ጆን ሜኬን ገጠሙና ኦባማ አሸንፉ፣ አሁን በ 2012 ኦባማ እንደገና ሚት ራምኒን ገጥመዋል። አሸንፈው ድጋሚ ፕሬዚዳንት ይሆኑ ይሆን? በመጪው ማክሰኞ ቁርጡ ይታወቃል።
ጠቅለለ አድርግን ለግንዛቤ ያህል ስናስቀምጠው እስከዛሬ በአሜሪካ ምርጫ
-    16 ጊዜ ዲሞክራቶች አሸንፈዋል።
-    18 ጊዜ ሪፓብሊካኖች አሸንፈዋል።
-    5 ጊዘ ዲሞክራቲክ ሪፓብሊካን ነን ያሉ ፕሬዚዳንቶች አሸንፈዋል
-    4 ጊዜ ዊግ የተሰኘ ፓርቲ ወክለናል ያሉ አሸንፈዋል
-    2 ጊዜ ፌዴራሊስት ፓርቲን የወከሉ ፕሬዚዳንቶች ሲያሸንፉ ….፣ 2 ጊዜ ደግሞ ምንም ፓርቲ የሌላቸው አሸንፈዋል።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on November 4, 2012
  • By:
  • Last Modified: November 4, 2012 @ 6:33 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%

One thought on “የአሜሪካ ምርጫ አጭር ታሪክ (ጥንቅር በአድማስ ሬዲዮ – አትላንታ፣ ጆርጂያ)

Comments are closed.

<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar