www.maledatimes.com Stop Abusing Ethiopian Refugees Sex Assault, Racketeering in Germany by Mr. Leul Keskis’s group ስለ ስደተኞች ዝም አልልም - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  AFRICA  >  Current Article

Stop Abusing Ethiopian Refugees Sex Assault, Racketeering in Germany by Mr. Leul Keskis’s group ስለ ስደተኞች ዝም አልልም

By   /   November 11, 2012  /   Comments Off on Stop Abusing Ethiopian Refugees Sex Assault, Racketeering in Germany by Mr. Leul Keskis’s group ስለ ስደተኞች ዝም አልልም

    Print       Email
0 0
Read Time:14 Minute, 12 Second

መቼም የኢትዮጵያዊ ወገኖቻችንን ስደትና በስደት ህይወት ውስጥ የሚገጥማቸው ፈተና ስፋቱም ሆነ ጥልቀቱ ´´ኤሎሄ´´ የሚያስብል ሆኗል።በባህር ውስጥ መስጠም፣በኮንቴይነር ታፍኖ መሞት፣የሰውነት ክፍላቸው እየወጣ እንደሸቀጥ መሸጥ፣በበረሀ እባቦች መነደፍ፣የሴት እህቶቻችን መደፈር፣በድንበር ጠባቂ ወታደሮች ጥይት መመታት………ወዘተ።

ታዲያ ይህንን ሁሉ ፈተና እና ውጣ ውረድ በጠበበ ዕድል አልፈው ወደ አረብ ሃገራት የሚገቡት ወገኖቻችን እዚያም የሚጠብቃቸው ስቃይ ኑሯቸውን ሁሉ መራራ ያደርገዋል።ይሁን እንጂ ያንን ሌላ ፈተና ተጋፍጠው ጥቂት ዕድለኞች ወደ አውሮፓ ይሻገራሉ።ከነዚህ መዳረሻ ሀገራት መካከልም በጠንካራ ኢኮኖሚዋ የምትታወቀው ጀርመን አንዷ ናት።

በጀርመን ´´ለሀገሩ እንግዳ ለህዝቡ ባዳ´´ ነኝ ብሎ መሳቀቅ አያስፈልግም።እንደሌሎች ሀገራት ከህዝቡም ሆነ ከመንግስት የሚመጣ እንግልታና ስቃይ የሚባል ነገር አይታሰብም።እንዲያውም የጀርመን መንግስት የምግብ፣የቤት፣የመብራት፣የውሃ፣የህክምና፣የልብስ፣የጫማና የንጽህና ዕቃ ወጪዎችን ሁሉ ከመሸፈኑም በላይ የኪስ ገንዘብም ለስደተኞች ይሰጣል።የጀርመን ህዝብም እጅግ ጨዋና ህግን አክባሪ ሲሆን ማንም ሰው በጀርመን ባዕድነት የሚሰማው አይመስለኝም።የጀርመን የኢሚግሬሽን ህግም ቢሆን ከሌሎች የምዕራብ ሀገራት የሚለይ ስላልሆነ ማንኛውም የፖለቲካ ጥገኝነት የጠየቀ ሰው ወይ ያሳለፈው የፖለቲካ ህይወት አልያም አሁን እያደረገ ያለው የፖለቲካ እንቅስቃሴ ከግምት ይገባል።

ታዲያ የኢትዮጵያ ስደተኞች ሌላ የስቃይ አቡጊዳ የሚጀምረው እዚህ ጋር ነው።የስቃዩ ምንጭ ደግሞ የጀርመን መንግስት አልያም የጀርመን ህዝብ እንዳይመስላችሁ፤ይልቁን ´´ወገናችን´´ የሆኑ ኢትዮጵያውያን ናቸው እንጂ።

በጀርመን የሚኖሩ የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር /ኢ.ህ.አ.ግ./ አመራር ነን የሚሉ ጥቂት ግለሰቦች ናቸው እንግዲህ ´´የስቃያችን ዘመን አበቃ´´ ብለው በተቀመጡ ስደተኞች ጫንቃ ላይ ሌላ የመከራ ቀንበር የሚጭኑት።የነዚህን ግለሰቦች ማንነትና ድርጊት በዝርዝር ማየቱ ታሪኩን የተሟላ ያደርገዋል የሚል እምነት ስላለኝ እነሆ በዝርዝር አስቀምጬዋለሁ።

´´መቶ አለቃዎቹ´´

እነዚህ የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር /ኢ.ህ.አ.ግ./ አመራር ነን የሚሉት የቀድሞው የኢትዮጵያ ጦር (ወያኔ ´´የደርግ ወታደር´´ እያለ የሚጠራው) አባል የነበሩ ሲሆን የተረጋገጠ ነገር ባይኖርም እስከ መቶ አለቃ ማዕረግ ደርሰው እንደነበር የቅርብ ሰዎቻቸው ይናገራሉ።ስለ አቶ ልዑል ቀስቅስና ስለ አቶ ጥላሁን ጉደታ።

በሌላ በኩል የፖለቲካ ጥገኝነት የጠየቁት ስደተኞች የፖለቲካ እንቅስቃሴያቸውን ለማጠናከር በተቃዋሚ ፓርቲ መታቀፍ የግድ ስለሚሆንባቸው በእነልዑልና ጥላሁን መረብ ውስጥ ይወድቃሉ።ከአባልነት ምዝገባ እስከ´´ስልጣን እንስጣችሁ´´ ያለውን ሂደት ከነዚህ ግለሰቦች ሚና አንፃር እንመልከት።

ዜና መዋዕሊሁ ለልዑል ቀስቅስ

ልዑል ቀስቅስ የዘረጋው አሰራር አዲስ አባል ሲመዘገብ የግድ በሱ በኩል እንዲያልፍ ያስገድዳል።በመሆኑም አባል ለመሆን ፆታው ወንድ ከሆነ መንግስት ለስደተኞች የኪስ ብሎ ከሚሰጠው ገንዘብ በላይ እንዲከፍል ይጠየቃል፤ሴት ከሆነች ሴትነቷን እንድትገብር በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ይነገራታል።ይህ እንግዲህ የጣር መጀመሪያ መሆኑ ነው።

ብራቸውንም ሆነ ሴትነታቸውን ገብረው የአባልነት ደብዳቤ ይደርሰናል ብለው ሲጠብቁ ታዲያ ደብዳቤው በልዑልና በጥላሁን መፈረም አለበት በሚል ልዑል የልቡን ካደረሰ በኋላ ´´ጥላሁንን አናግሩት´´ በማለት እንደ ጎበዝ ኳስ ተጫዋች ለጥላሁን ያቀብላቸዋል።

ይህ እንዲሁ የሚደረግ የስም ማጥፋት ሳይሆን በቅርቡ በዚህ የልዑልና አጋሮቹ ድርጊት ሰለባ የሆኑ ወገኖች በኢንተርኔት ድምፅ በማሰባሰብ ለመክሰስ ተሰናድተው የነበር ሲሆን ጉዳዩ ለጥቂት ጊዜያት ቢቋረጥም በብርቱ ኢትዮጵያውያን ድጋፍ በቂ ማስረጃዎች ከሰው ምስክር ጋር በበቂ እየተዘጋጀ ሲሆን ይህም እነዚህን በፍቅረ-ነዋይና በሴሰኝነት ልባቸው ታውሮ በወገኖቻችን ላይ የሚፈጽሙትን በደል ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በህግ ለመፋረድና በሌሎችም ላይ ከዚህ በኋላ እንዳይደገም ለማስተማር ነው።

በዚህ አጋጣሚ በጎግል ድረ-ገጽ ላይ ´´Stop Abusing Ethiopian Refugees Sex Assault, Racketeering in Germany by Mr. Leul Keskis’s group´´ ብላችሁ ብትገቡ የድምጽ ማሰባሰቢያ ቅጹን ከነይዘቱ ማግኘት ሲቻል እኔም የቅጹን ኮፒ ከታች አያይዤዋለሁ።

ዜና መዋዕሊሁ ለጥላሁን ጉደታ

ጥላሁን ጉደታን ለመግለጽ ሁለት ቃላት ብቻ መጠቀም  በቂ ይሆናል።ሴሰኛና ሱሰኛ።

ጥላሁን ከልዑል የተሰጠውን የቅብብሎሽ ጨዋታ የወንዶችን ሱሰኛ (በተለይ የመጠጥ) በመሆኑ በስንፍና ምክንያት ያዘገይ ይሆናል እንጂ ገንዘብ አይጠይቅም።የሱ የግፍ ቀንበር በሴት እህቶቻችን ላይ ያተኩራል።በሌላ በኩል የአባልነት ደብዳቤው ከደረሳቸው በኋላ በአቶ ጥላሁን አማካኝነት የ´´ስልጣን እንስጣችሁ´´ ጥያቄ ለእህቶቻችን የሚቀርብ ሲሆን አሁን ደግሞ የቅብብሎሽ ሂደቱ ተገልብጦ ከጥላሁን ወደ ልዑል ይሆናል።

ማጠቃለያ

ሲጽፉት እንዲህ ይቅለል እንጂ እነዚህ ግለሰቦች ያደረሱት ግፍና በደል ማንም ኢትዮጵያዊ በወገኑ ላይ ያውም በስደት በሚገኝ ወገኑ ላይ ያደርገዋል ተብሎ የማይገመት ነው።የምንኖርበት ሀገር የህግ የበላይነት የሰፈነበት ነው።በመሆኑም በተሰበሰበው እና እየተሰበሰ ባለው የሰው እና የወረቀት ማስረጃ መሰረት እነዚህ ግለሰቦች በቅርቡ ለፍርድ ይቀርባሉ።

ስለ ወገኖቻችን ዝም አንልም!!!

ይልቃል በቃሉ

ኑረንበርግ ጀርመን

 

care2 petitionsite

Stop Abusing Ethiopian Refugees Sex Assault, Racketeering in Germany by Mr. Leul Keskis’s group

 

Many young desperate
Ethiopian girls have been sexually assaulted and boys have
been abused at their arrival in Germany for a demanded of political
asylum. Young and inexperienced arriving from Ethiopia have been
abused by group of mafia established in Germany led by Mr. Leul Kekis
member of the dictatorial regime

of Melese Zenawi parliament of in Ethiopia.
The Following abuses have been committed - Their support allowances have been ripped off , The Young girls have been sexually assaulted , Their cases were
sabotaged to the federal refugee’s office , Many have been rejected
and they are in verge of deportation, To those of them requesting explanation,
letters of abuse have been written to the authorities and to their lawyers as
they are not genuine refuges… We are asking the Government of Federal
Republic of Germany to stop Mr. Leul Kekis and his Mafia group from
abusing the refuges and to reconsider their cases and bring him to court of law
for his criminal act. The following 21 video a… more

we signed “Stop Abusing Ethiopian Refugees Sex Assault, Racketeering in Germany by Mr. Leul Keskis’s group”

# 25

11:02, Aug 04, Mr. Tsegu WoldeMichael, CA

# 24

11:28, Jul 28, Mr. girma dawit, Uganda

# 23

23:57, Jul 25, Mr. Mohammed Omer

# 22

21:32, Jul 24, Mr. you idiot, NY

# 21

07:03, Jul 15, Mr. Brehane Reda

# 20

15:14, Jul 01, michael zeleke, Germany

# 19

19:29, Jun 27, Ms. Addie Stone, AZ

# 18

13:23, Jun 26, Mr. senyange patrick jr, Uganda

# 17

16:03, Jun 24, Ms. Pepe Pops, Germany

# 16

08:20, Jun 23, Arat Mekera, MO

# 15

16:08, Jun 22, Ms. Déborah Moine, Belgium

# 14

12:40, Jun 22, Mrs. Ela Gotkowska, Poland

# 13

11:22, Jun 22, Mr. simon willder, United Kingdom

# 12

10:03, Jun 22, Ms. Li Prudhomme, ON
Sexual abuse and assault is wrong and a crime everywhere. Wherever there is abuse there is a crime being committed. It’s the German Government’s responsibility to take care of the crimes that are being committed by Mr. Leul Kekis and his Mafia gang. This Ethiopian girls and boys have a right to a good and safe life.

# 11

06:57, Jun 22, Mr. Rob Meyer, Netherlands

# 10

03:09, Jun 22, Name not displayed, CA

# 9

03:08, Jun 22, Mr. Bill C, Germany

# 8

02:03, Jun 22, Mrs. Anita Ketel, Netherlands

# 7

01:29, Jun 22, Mr. Richard Hollister, AZ

# 6

23:32, Jun 21, Ms. Annick Dori, Switzerland

# 5

23:10, Jun 21, Mr. Muse Tegegne, Switzerland

# 4

22:52, Jun 21, Ms. annie statton, United Kingdom

# 3

20:42, Jun 21, Name not displayed, NJ
Germany should investigate because if abuses and crimes are happening then it needs to stop.

# 2

20:41, Jun 21, Ms. Vicky Pitchford, ON

# 1

15:26, Jun 21, Ms. Mary Furlong, QC

 

 

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on November 11, 2012
  • By:
  • Last Modified: November 11, 2012 @ 3:15 pm
  • Filed Under: AFRICA, Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

Traveler’s Alleged Crimes and Robbery at Bole Airport Raise Concerns

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar