www.maledatimes.com ቴዲ አፍሮ የለንደን ከተማን “በጥቁር ፈረሱ” አሟሟቃት - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ቴዲ አፍሮ የለንደን ከተማን “በጥቁር ፈረሱ” አሟሟቃት

By   /   November 14, 2012  /   Comments Off on ቴዲ አፍሮ የለንደን ከተማን “በጥቁር ፈረሱ” አሟሟቃት

    Print       Email
0 0
Read Time:18 Minute, 25 Second

በታምሩ ገዳ
እውቁ የሙዚቃ አቀንቃኝ ቴዲ አፍሮ (ቴድሮስ ካሳሁን ) በረካታ አርቲስቶችን ባሳተፈው እና በአጭር ቀናት ውስጥ ገበያውን በተቆጣጠረበት “ጥቁር ሰው” አልበሙ ጨምሮ በበረካታ ተወዳጅ ዘፈኖቹ እማካኝነት በታላቋ ብርታኒያ ውስጥ ለሚገኙ የሙዚቃ አድናቂዎቹ በለንደን ከተማ ወስጥ ታላቅ የሙዚቃ ምሽት አቀረበ ፡፡ በክብር እንግድነት የተጋበዘው አትሌት ሃይሌ ገ|ስላሴ በመድረኩ ላይ ብቅ ሳይል ቀረ፡፡
ባለፈው ቅዳሜ ሃምሌ 28 2004 አ.ም (ነሃሴ 4 2012 እ.ኤ.አ ) በተደረገው የሙዚቃ ምሽት ላይ ለመገኘት ብዛቱ ከሁለት ሺህ ሰባት መቶ በላይ የሚገመት የሙዚቃ አፍቃሪ ወደ አዳራሹ ለመግባት ወረፋ መያዝ የጀመረው ገና በጊዜ ነበር ፡፡ከአደናቂዎቹ ጋር በግንባር ከተገናኘ ከአመት በላይ ያስቆጠረው አርቲስት ቴዲ አፍሮ በመድረኩ ላይ ከስድስት በላይ አዳዲስ ዘፈኖቹን ጨምሮ ከሃያ አንድ በላይ የተለያዩ የራሱ እና የሌሎች ታዋቂ አርቲስቶች ዘፈኖችን ለአድናቂዎቹ አቅርቧል፡፡
የለንደን ከተማ የአስራ ሶስተኛው ኦሎምፒክ እና ፓራ ኦሎምፒክ (የአካለ ስንኩላን) ውድድድሮችን በማሰተናገድ በተጠመደችበት ወቅት ወደ መዲናይቱ ብቅ ያለው አርቲስት ቴዲ አፍሮ ለኢትዮጵያ አትሌቶች ዘወትር ያለውን እክብሮት እና መልካም ምኞቱን ሳይገልጽ አላለፈም ፡፡ በቅርቡ በገበያ ላይ የዋለው አልበሙ ኢትዮጵያዊያን በተለይ በአጼ ምንሊክ ቆራጥ አመራር የወራሪው የፋሺስት ኢጣሊያን ሰራዊትን አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት ድል ያድርጉበትን ተጋድሎን የሚዘክረው “ጥቁር ሰው” የተሰኘው ዘፈኑን ለአድናቁዎቹ ሁለት ጊዜ ያቀነቀነ ሲሆን በረካታ አደናቂዎቹም አረንጓዴ ፡ቢጫ እና ቀዩን የኢትዮጵያ ሰንድቅ አላማን በማውልብለብ ለአጼ ምኒሌክ ሆነ ለቴዲ አፍሮ ያላቸውን እክብሮት እና ፍቅር ገለጸዋል፡፡
አርቲስት ቴዲ አፍሮ (ፎቶ ዘለአለም ጌታሁን)
የጥቁር ሰው ዘፈኑን በተመለከተ ቴዲ አፍሮ ከሙዚቃው ባሻገር መልእክቱን በልዩ እንቅስቃሴ ለህዝቡ ለማቅረብ አስቦ እንደ ነበር እና ፍላጎቱ በመጨረሻው ሰአት ላይ ያለመሳካቱን የቴዲ አፍሮ ፕሮመተሮች ከሆኑት መካከል አንዱ የሆነው የአቤሲኒያ ኤንተርቴይንመንት ፕሬዘንተር ድርጅት ሃላፊ የሆኑት ወ|ት ትግስት ወ|የስ በምድረ አሜሪካ ከላስቭጋስ ከተማ ለሚሰራጨው የህብር ራዲዮ የምእራብ አውሮፓ ልዩ ዘጋቢ ለሆነው ለዚህ ጸሃፊ ገልጸዋል፡፡ፕሮግራሙን እንዲሰሩ ሃሳብ የቀረበላቸው ዳንኪራ መዝናኛ የተባለው ባንድ ረዳት ማናጀር የሆኑት አርቲስት ዳንኤል በበኩሉ እርሱም ሆነ የተቀሩት የሙያ ባልደረቦቹ እቅዱን ለማሳካት የተቻላቸውን ጥረት ቢያደርጉም “ውስብስብ በሆነ ምክንያት” የታቀደው የመድረክ ላይ ፕሮግራም ያለመሳካቱን አርቲስት ዳንኤል ገልጿል፡፡
በቴዲ አፍሮ የሙዚቃ ኮንሰርት ላይ አትሌት ሃይሌ ገ|ስላሴ በክብር እንግድነት ይገኛል ተብሎ ማስታወቂያ ላይ ከተለጠፈ በሁዋላ የሃይሌ በአዳራሹ አካባቢ ዝር ያለማለቱ በአንዳንድ ወገኖች ዘንድ “ምናልባት አዘጋጆቹ በሀይሌ ስም ተጨማሪ ታዳሜ እና ገንዝብ ለማግኘት አስበው ይሆናል” የሚል ጠርጣሬ የተሰማ ሲሆን ወ|ት ትግስት በበኩላቸው ለቀረበው ቅሬታ በሰጡት አስተያየት “አትሌት ሃይሌ ለዚህ ፕሮግራም መሳካት ተባብሮናል፡፡ በተለይ ደግሞ በአዲስ አበባ ያለውን የቪዛ የማግኘት ውጣውረድን አቃልሎናል፡፡ እንደ አጋጣሚ ሆኖ ፕሮግራሙ ከመጀመሩ ከአንድ ቀን በፊት ለአስቸኳይ ስራ ወደ አገር ቤት በመሄዱ በፕሮግራሙ ላይ አለተገኘም፡፡” ሲሉ ሃሜታውን አስተባብልዋል ፡፡ አትሌት ሃይሌ በምን መልኩ ነው የቪዛ የማግኘት ውጣውርድን ያቃለለላችሁ? ለሚለው ተከታይ ጥያቄ ወ|ት ትግስት “ጉዳዩ የግል ጉዳይ ነው” በማለት ዝርዝር አስተያየት ከመስጠት ተቆጥበዋል፡፡
በዚህ በቴዲ አፍሮ የሙዚቃ ፕሮግራም ላይ ከተገኙት አደናቂዎቹ መካከል በቅርቡ የለንደንን ታሪካዊ ከተማነት የሚያወሱ የተለያዩ ዘፈኖችን በማቀነባበር የተለያዩ አሰራ ሶስት ባንዶች በጋራ በሰሩት አልበም ኢትዮጵያን በመወከል የእንግሊዘኛውን “ለንደን” የተሰኘውን የታዋቂዋ አቀንቃኝ ሊሊያን አለን ዘፈንን ከፊሉን ወደ አማሪኛ በመለወጥ በቅርቡ ብሄራዊ እና አለማቀፋዊ ተደማጭነት ያገኙት “ክራር ኮሌክቲቭ” የተሰኘው የሙዚቃ ባንድ አባል የሆነው እርቲስት ግሩም በጋሻው በሰጠው አሰተያየት ” አርቲስት ቴዲ አፍሮ ሁል ጊዜ ወደ አድናቂዎቹ ዘንድ ሲመጣ በደንብ ተዘጋጅቶ በአዳዲስ ስራዎቹ መቅረብ የሚፈልግ ወጣት አርቲስት በመሆኑ በአሁን ሰአት የበረካታ ታዋቂ አርቲስቶች አዳዲስ ክሮች ገበያ ሲያጡ ቴዲ አፍሮ ግን በሚያስገርም ሁኔታ ገበያውን እና አድናቂዎቹን መቆጣጠር የሚችል ተስጥኦ ያለው አርቲስት ነው ፡፡ በዚህ ዝግጅት ሆነ ከዚህ ቀደም ባሳያቸው በርካታ ዝግጅቶቹ ላይ እንደተመለከትኩት ቴዲ ዝግጅቶቹን አንደ ምእራባዊያን አርቲስቶች በመዝናኛ ስፍራ (ፓርክ ውስጥ) እንኳን ቢያዘጋጅ ብዛት ያለውን የሙዚቃ አፍቃሪን ቀልብን መሳብ ይችላል፡፡በዚህ ፕሮግራም ላይ የነበረው የሰአት አጠቃቀም በጣም ጥሩ ነበር ፡በቴዲ ኮንሰርት ላይ ጃማይካኖች ነጮች እና የተለያዩ አገር ተወላጆች መታደማቸው የሙዚቃ ስራው ምን ያህል ሰዎችን የመሳብ ጉልበት እናዳለው ያመላክታል፡፡ ቴዲ ከወራት አይደለም ከሳምንታት ቆይታ በሁዋላ ተመልሶ ወደ ለንደን ቢመጣ ዛሬ ከነበረው የማይተናነስ ቁጥር ያለው ታዳሚ እነደሚመጣ ከነበረው ግርግር በቀላሉ መግመት ይቻላል፡፡” ብሏል ፡፡ የመግቢያ ዋጋን በተመለከት ከእኩለ ሌሊት በሁዋላ በሰው ሰላሳ ፓውንድ ማሰከፈሉ ቅር አንዳሰኘው አርቲስት ግሩም ሳይገልጽ አላለፈም፡፡
የቴዲ አፍሮ የሙዚቃ አድናቂዎች በከፊል (ፎቶ ዘለአለም ጌታሁን)
ይህንን ያህል የተመልካች ፍቅር እና አክብሮት ያለው አርቲስት “ቴዲ አፍሮ የማን ነው?” ለሚለው የዚህ ጸሃፊ ጥያቄ አንድ ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ ነገር ግን ቴዲን በመድረኩ ላይ ሆነ ከመድረኩ በስተጀርባ ለማየት እድሉን እንዳገኙ የገለጹ ታዛቢ ለዚህ ጸሃፊ በሰጡት አስተያየት “ቴዲ አፍሮ የህዝብ ልጅ ለመሆኑ ምንም ጥርጥር የለኝም ፡፡ነግር ግን ከመጋረጃው በስተጀርባ ቴዲ በማያውቀው ወይም ባልተረዳው መልኩ የቴዲን እንቅስቃሴዎችን ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር የሞከሩ በአሜሪካ እና በለንደን የሚኖሩ የሼክ አላሙዲን ደጋፊዎች አይን ያወጣ እና ዱላ ቀረሽ እንቅስቃሴዎችን ሲያደርጉ ታዝቤያልሁ ፡፡ቴዲ አፍሮ ከዚህ ቀደም ስብእናዮን እና ክብሬን ለገንዘብ አለሸጥም በማለት በአዲስ አበባው ሻራተን ሆቴል የተደረገለትን ግብዣ ውድቅ ማድረጉን አስታውሳለሁ ፡፡ አሁንም ቢሆን ከዚያ ያልተናነስ ስውር ተንኮላቸው መጥንቀቅ ይኖርበታል ብዪ ውገናዊ ምክሬን እንደ አድናቂ እና እንደ ታዛቤ ማስተላለፍ እፈልጋለሁ፡፡”ብለውል፡፡
ወጣት ኤሻያው ማቴያስ ይባላል፡፡ የቴዲ አፍሮ የኮንሰርት ፕሮግራምን ለመመልከት ከለንደን ውጭ ሌስተር ከተባለው ከተማ ከአንድ ቀን ቀደም ብሎ ወደ ለንደን ከተማ መምጣቱን ይናገራል፡፡በፕሮግራሙ ላይ ምን ታዘብክ? ለሚለው ለዚህ ጸሃፊ ጥያቄ “ቴዴ አፍሮ ዘወትር እንደ ህዝባዊ መፈክር የሚጠቀምበትን “ፍቅር ያሸንፋል!!” የምትለውን ጥቅስን ሲያሰማ በአዳራሹ ውስጥ የነበረው ህዝብ በምላሹ “አዎ ፍቅር ያሸንፋል…!!!” የሚል ምላሽ ሲሰጠው ልቤ በስሜት ተላውሷል፡፡ ምክንያቱም ሁሉም ነገር በፍቅር ሊሆን እንደሚችል በቴዲ ኮንስርቶች(ሾው) ስለተማርኩኝ ነው ፡፡በኮንስርቱ ላይ ምንም እንኳን የሚበላ ምግብ ባይኖርም ህዝቡ ከነገ ጀምሮ መጠጥ ያቆማል የተባለ ይመስል ባንኮኒ አካባቢ ሲተራመስ ታዝቤያለሁ ፡፡ በሚያስገርም ሁኔታ ግን እንደ ከዚህ ቀደሙ ጸብ እና ድብድብ አላየሁም ፡፡ ሴቶች እህቶች ሆኑ ወንዶች እራሳቸውን ጠብቀው ነበር ምሽቱን በመዝናናት ያሳለፉት ፡፡ አዳራሹ ውስጥ በተለይ ደግሞ ከእኩለ ሌሊት በህዋላ የነበሩት ተንቀሳቃሽ ስልኮች (ሞባይሎች) ጥሪ መቀበል ያቆሙ እስከ ሚመስል ድረስ ሁሉም በመድረኩ ላይ የነበረውን አርቲስት ቴዲ አፍሮን ለምቅርጽ ሲሯርጡ ነበር ያመሹት ፡፡ ሲል በፕሮግራሙ መደሰቱን ተናግሯል፡፡
ይህ ቴዲ አፍሮ ለስራው ከአርባ ሺህ የአሜሪካ ዶላር (ሃያ አምስት ሺህ ፓውንድ) በላይ አንደተከፈለው የገለጹት የቅርብ ምንጮች አዘጋጆቹ በአጠቃላይ ከሃምሳ አንድ ሺህ ዶላር በላይ ትርፍ ሳያገኙ እንዳልቀረ ግምታቸውን ለዚህ ጸሃፊ ስንዝረዋል፡፡ አርቲስት ቴዲ አፍሮ በለንደኑ ፕሮግራም ላይ እጮኛውን እና የወደ ፊት የትዳር ጓደኛው ወ|ት አምለሰት ሙጪን ይዞ የመጣ ሲሆን ከፕሮግራሙ በሁዋላ በመዲናይቱ በሚገኙ የኢትዮጵያዊያን ንብረት በሆኑ የመዝናኛ ስፍራዎች(ሬስቶራንቶች ) ይዟት ሲዝናና እንደነበር የቅርብ ምንጮቹ ለዚህ ጸሃፊ አክለው ተናግረዋል ፡፡ ቴዲ አፍሮ ከእጮእኝው ጋር በመጪው መስከረም ወር የጋብቻ ስነስርአታቸውን ይፈጽማሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን አርቲስቱ ለተመሳሳይ የሙዚቃ ትርኢት በ ተለያዩ አሜሪካ ግዛቶች ወደ ሃያ ኮንሰርቶችን ለማሳየት የአትላንቲክ ውቅንያኖስን ይሻገራል ተበሎ የጠብቃል፡፡
ለተጨማሪ ጥያቄዎች ወይም ማብራሪያዎች ጸሃፊውን tamgeda@gmail.com ያገኙታል፡፡

About Post Author

Abby

Internet reporter, freelancer and webmaster.
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email

About the author

Internet reporter, freelancer and webmaster.

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar