0
0
Read Time:27 Second
አዲስ አበባ፣ሰኔ 7፣2011 (ኤፍ ቢ ሲ) በዛሬው ዕለት ኢትዮጵያ ቡና ከመቐለ ሰባ እንደርታ ሊያደርጉት የነበረው ጨዋታ በመጪው ማክሰኞ እንዲካሄድ ተወሰነ። በፀጥታ ስጋት ምክንያት በተደጋጋሚ ሳይካሄድ የቆየው ይህ ጨዋታ በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ ስታድየም ይካሄዳል ተብሎ ሲጠበቅ ነበር። ሆኖም በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተሰጠ በሚገኘው ፈተና ምክንያት በፀጥታ አካላት ላይ ጫና በመኖሩ ፈተናው ከተጠናቀቀ በኋላ ጨዋታው እንዲካሄድ ፓሊስ በመጠየቁ ለማክሰኞ መዘዋወሩን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳን አቶ ኢሳያስ ጂራ አስታውቀዋል። ፓሊስም ሆነ የእግር ኳስ ክለቦቹ ሀላፊነት የሚወስዱ መሆናቸውን በመግለፃቸው ጨዋታው ደጋፊዎች በተገኙበት ማክሰኞ በ10 ሰዓት በአዲስ አበባ ስታድየም ይካሄዳል።
Wondering where the comments are? We encourage you to use the share buttons below and start the conversation on your own!
- Click to email a link to a friend (Opens in new window)
- Click to share on Facebook (Opens in new window)
- Click to share on Twitter (Opens in new window)
- Click to share on LinkedIn (Opens in new window)
- Click to share on Pinterest (Opens in new window)
- Click to share on Tumblr (Opens in new window)
- Click to print (Opens in new window)
Average Rating