ባለፈው ሰኞ፣ ግንቦት 26/2010 በፌደራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ልደታ የንግድ ችሎት የናሁ ቴሌቪዥን እናት ድርጅት በሆነው ጎልደን ኮፊ ሮስተሪ አመልካችነት በዛሚ ኤፍ ኤም 90.7 ሬዲዮ ላይ በቀረበው አቤቱታ መሰረት የሬዲዮ ጣቢው እንዳይሸጥ እንዳይለወጥ እግድ ማውጣቱ ታወቀ። በተጨማሪም በድርጅቱ ተመዝግበው ያሉ ሁለት ተሽከርካሪዎች ላይም እግድ የወጣ ሲሆን እግዱም በፌደራል ትራስፖረት ባለስልጣን፣ በብሮድካስት ባለስልጣን እንዲሁም በቂርቆስ ክፍለከተማ ንግድና ኢንዱስትሪ ጽህፈት ቤት ተልኮ ተፈፃሚ እንደተደረገ የናሁ ቴሌቪዥን ስራ አስኪያኪያጅ ደረጄ ተክሌ ለመረጃ ማእከሎች አስተውቀዋል።
ለመሻሻጥ ተስማምተው ነበር። ለዚህም ቅድሚያ ክፍያ ወደ 5 ሚሊዮን ብር ገደማ ለሻጮች በቼክ የተፈፀመ ሲሆን ይህም ድርጅቱ ያሉበትን የግብር እዳዎች ፈፅሞ ለመጨረስ እና ከዛም የቀረውን ገንዘብ በመክፈል በአጭር ጊዜ ውስጥ ድርጅቱን ለመረካከብ እንደሆነ ደረጄ ተናግረዋል። ነገር ግን በፊርማቸው ድርጅቱን መሸጣቸውን ያረጋገጡት ግለሰቦች በሚዲያ ወጥተው ድርጅቱ አልተሸጠም የሚል ማስተባበያ በመስጠት እና ውሉንም ለማፍረስ ጥያቄ በመምጣቱ ናሁም ጥያቄውን መቀበሉን ተናግረዋል። ኹለቱም ወገኖች ውል ለማፍረስ ተስማምተው የነበረ ሲሆን ገንዘቡ ሲመለስ ግን ሕጋዊ የባንክ ወለድ ሊሰላበት ይገባል በሚለው ላይ አለመስማማቶች መኖራቸውን ገልፀዋል። ደረጄ እንደሚሉት ሚሚን እና የድርጁትን ጠበቃ በጋራ እንዲሁም ዘሪሁንን በሌላ ጊዜ ለብቻ በማነጋገር ከጎልደን ኮፊ ሮስተሪ ባለቤት ቴዎድሮስ ሽፈራው ጋር የተፈጠረውን ያለመግባባት ለመፍታት ጥረት ቢያደርጉም በመጨረሻ መግባባት ባለመቻሉ ወደ ሕግ ለመሔድ መገደዳቸውን ተናግረዋል።
አይደለም ብለዋል። በዝርዝር ጉዳዮች ላይም አስተያየት እንደማይሰጡም ተናግረዋል። ናሁ ቴሌቪዥን እስከዛሬ በሚዲያ ሲባሉ የነበሩ ነገሮች አግባብነት ባይኖራቸውም በዝምታ በማለፍ ጉዳዩን በሕግ ለመፍታት በመሞከር ላይ ሲሆን እየቀረቡ ስላሉ ተከታታይ ጥያቄዎችም በመጪው ሳምንት ጋዜጣዊ መግለጫ ለመስጠት ማሰቡንም ተናግሯል። “ድርጅቱ ሙሉ ለሙሉ ወደ ገዢዎች እጅ ባይገባም ስምምነቶች ነበሩን፣ ይህ የማየሆን ከሆነም አንዱ ገንዘቡን አጥቶ አንዱ ሥሙን አትቶ መቀጠል ስለማገባ ችግሩን በስምምነት ለመፍታት ሙከራ እደረግን ነው” ሲሉ ደረጄ ተናግዋል። ፍርድ ቤቱም እግዱ መፈፀሙን በማረጋገጥ ቀጣይ ቀጠሮ ይሰጣል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተገልጿል።
ወይዘሮ ሚሚ ስብሃቱ በምርጫ ዘጠና ሰባት አመተ ምህረት ኢፍትን በምትባል ጋዜጣ የተቃዋሚ ፖለቲከኞችን እና ጋዜጠኞችን ሲያዋክቡ እና ለእስር እንዲዳረጉ ጉትጎታ ከሚያደርጉት የህወሃት ወግንተኞች መገናኛ ብዙሃን በመሆን የሰሩ ሲሆን ቀድሞ ይሰሩበት የነበረው የአሜሪካን ድምጽ ራዲዮ በችሎታ ማነስ እና በስነ ምግባር ጉድለት መባረራቸውን የስራ ባልደረቦቻቸው ይገልጻሉ ፡፤ ከዚያም በሌላ መልኩ በጠረጴዛ ዙሪያ በተሰኘው የሪርዲዮ ፕሮግራም ህዝቦችን በማብጠልተል ትታወቃለች ።
Average Rating