www.maledatimes.com በአዲስ አበባ በጠራራ ጸሐይ ዝርፊያ ተጠናክሯል - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  AFRICA  >  Current Article

በአዲስ አበባ በጠራራ ጸሐይ ዝርፊያ ተጠናክሯል

By   /   June 18, 2019  /   Comments Off on በአዲስ አበባ በጠራራ ጸሐይ ዝርፊያ ተጠናክሯል

    Print       Email
0 0
Read Time:2 Minute, 10 Second

በአዲስ አበባ በጠራራ ጸሐይ ዝርፊያ ተጠናክሯል

የከተማዋ ም/ል ከንቲባ ታከለ ኡማ በአዲስ አበባ የተንሰራፋውን ዝርፊያ አደብ ለማስገዛት ከፌደራል ፖሊስ ፣አዲስ አበባ ፖሊስ እና ኦሮሚያ ፖሊስ በቅንጅት በአንድ ሳምንት ውስጥ የተቀናጀ ሥራ ለመሥራት የጋራ ግብረ ሀይል ተቋቁሟል ማለታቸው አይዘነጋም። ይህ ውሳኔ የተሰማው በከተማዋ በመሳሪያ ጭምር የተደገፈው ዝርፊያ የአፍሪካ ክብረትን ጭምር አሳስቦ ለሰራተኞቹ ማስጠንቀቂያ ካወጣ በሁዋላ ነበር። ዝርፊያው ግን ዛሬም ቀጥሏል።ለጥንቃቄ ይረዳ ዘንድ የጋዜጠኛ ዮሐንስ አምበርብርን ምስክርነት ያንብቡት ሼር ያድርጉትታርጋ ኮ2 A 11191 
————–
የቤት አውቶሞቢል በመጠቀም በአዲስ አበባ ውስጥ በጠራራ ጸሀይ ቅልጥ ባለ ጎዳና ላይ የሚደረገው ዝርፊያ ተጧጡፎ ቀጥሏል። ከመኪናው ውስጥ የተማመ ሰው ወደ ውጭ በድንገት እግረኛ ላይ ያስመልሳል። መኪናው ይቆምና አንድ ሰው ወርዶ በጨርቅ ወይም ልብሱን አውልቆ የተበላሸውን ልብሶን ይጠርግሎታል ፣ ከሚከናው መስኮት ሌላ ሰው የታሸገ ውሃ አውጥቶ እጆን እንዲታጠቡ ያፈስሎታል ነገሩ ግን ትኩረቶን ልብሶን ከሚጠርግሎት ወጣት ላይ እንዲያነሱ ነው። በመጨረሻም ይቅርታ ጠይቀዎት ይፈተለካሉ። ወደ ቀልቦ ሲመለሱ ኪሶ ውስጥ ያሉ ነገሮች ሞባይል ፣ ዋሌት ወይም ገንዘቦ የለም። ቮሚቱን ይጠርግሎ የነበረው ወጣት ወስዶታል። ቮሚት የመሰሎት ነገርም ወጣቱ ተጎነጭቶት የነበረው እርጎ ስለመሆኑ በኃላ ላይ ይገነዘባሉ። 
በዚህ መንገድ ከተሸወዱት መካከል አንዱ ነኝ። ዛሬ ወደ ገርጂ መብራት ኃይል አካባቢ ከአንድ ቪትስ መኪና ውስጥ ያው እርጎውን አንድ ወጣት ልጅ ላይ ተፍተውበት አጽድተውለትና ጠርገውት መኪናው ሲንቀሳቀስ ደረስኩ። አጠገቡ የነበረ ሊስትሮ ቀና ብሎ እያየ ስራውን ቀጥሏል ፣ መንገደኛውም ፣ ታክሲ የሚጠብቀውም ሁሉ ዝም ብሎ ነገሩን ያስተውላል። ወይ ሰግተው ወይም ነገሩ ስላልገባቸው እንደሆነ እገምታለው። እኔ ስደርስ መኪናው እየተንቀሳቀሰ ቢሆንም ታርጋውን ከመመዝገብ ውጪ ሌላ ምንም ማድረግ አልቻልኩም። የአዲስ አበባ ተወላጅ ወይም ከተሜ እንዳልሆነ በግልጽ የሚያስታውቀው ወጣቱ ልጅ አጠገብ ስደርስ ጉድ እንደተሰራ የገባው ይመስላል። እኔ ሞባይል ስለሆነ የተዘረፍኩት ሞባይልህ አለ? ስል ጠየኩት። “እሱ እንኳን አለ” አለኝ። ምንም አልወሰዱብህም ? ቀጣዩ ጥያቄ ነበር። በኪሴ ውስጥ የነበረ 4500 ብር ነው የወሰዱት ብሎ በማቃሰት እጁን ግራ ደረቱ ላይ አሳርፎ በርከክ አለ። ደገፍኩትና ለማረጋጋት ሞከርኩ። ያስቀረውትን የመኪናውን ታርጋ አቀበልኩት ፤ ልጁ ግን ለመራመድ ይሞክርና እግሩ አልታዘዝ ይለዋል ። ጥሎም ልቡን በእጁ የደግፋል። ድንጋጤና ንዴት ጤንነቱን እያወኩት መሆኑ ስለገባኝ ፤ አየር በረጅሙ እንዲስብና እንዲተነፍስ ይህንንም ለሶስት አራቴ እንዲያደርግ ከረዳሁት በኃላ የሰጠውትን ታርጋ ቁጥር ይዞ በአቅራቢያው ወደነበረች የትራፊክ ፖሊስ እንዲመራ እረዳሁት። አላማዬ ሬድዮ ተጠቅማ ታርጋውን መኪናው ወዳመራበት አካባቢ እና በዛ ርቀት ውስጥ ወዳሉ ባልደረቦቿ እኖድታሳውቅ ነበር። ነገር ግን ትራፊክ ፖሊሷ ደንብ ጥሷል ብላ ላስቆመችው ተሽከርካሪ ቅድሚያ በመስጠቷ ዘራፊዎቹን የያዘው ተሽከርካሪ የመያዝ እድሉ እንደመነመነ ተሰማኝ። ለማንኛውም ወጣቱ ጤንነቱ እየተመለሰለት በመሆኑ እራሱ ነገራት እኔ ግን ተስፋ ቆርጫለው። እሷም የመከረችው ጣቢያ እንዲያመለክት ነበር። ለማንኛውም ያስቀረውት ተሽከርካሪ ታርጋ ኮድ 2 A11191 ነው። ተሽከርካሪው የኪራይ እንደሚሆንና ግንኙነት እንደሌለው ብገምትም በእለቱ ተከራይተው የነበሩትን ሰዎች ማንነት ማወቅ ይቻላል። ግን ደግሞ ታርጋው ተመሳስሎ የተሰራ እና በትራንስፖርት ባለስልጣን ያልተመዘገበ አለመሆኑንስ እንዴት እርግጠኛ መሆን ይቻላል ? 
ለማንኛውም የሚሰማ ካለ ይስማና ነገሩን አደብ ያበጅለት። ይህንን የዘረፋ ዘዴ የማታውቁም ተማሩበትና ተጠንቀቁ። 
ወጣቱ ልጅ ደረቱን ይዞ ያቃሰተው ግን አሁንም ይመሰማኛል ቢሆንም የከፋ ነገር ስላልሆነበት መልካም ነው።

About Post Author

Abby

Internet reporter, freelancer and webmaster.
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email

About the author

Internet reporter, freelancer and webmaster.

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

Ethiopia’s Media Under Siege Amid Escalating Conflict in Amhara

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar