www.maledatimes.com ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ያሉበት አይታወቅም! - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ያሉበት አይታወቅም!

By   /   June 23, 2019  /   Comments Off on ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ያሉበት አይታወቅም!

    Print       Email
0 0
Read Time:58 Second

Image may contain: 1 person

በትናንትናው ዕለት በአማራ ክልል ከተደረገው “የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ” እና ግድያ ጀርባ አሉ ተብለው የተጠረጠሩት ብርጋዲየር ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ያሉበት እንደማይታወቅ የክልሉ የሰላም ግንባታና ህዝብ ደኅንነት ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ገደቤ ኃይሉ ለቢቢሲ ገልፀዋል።

በትናንትናው ዕለት የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድርን ጨምሮ ከፍተኛ አመራሮች ግምገማ እያካሄዱ ባሉበት ወቅት ብርጋዲየር ጄኔራሉ በልዩ ኃይሎች ታጅበው እንደመጡና በመጀመሪያም አጃቢዎቻቸው ላይ ተኩስ እንደተከፈተ ከዚያም አመራሮቹ ላይ በተተኮሰ ጥይት ሦስቱ እንደተመቱ አቶ ገደቤ ይናገራሉ።

“ጥቃቱ በከፍተኛ ደረጃ የተቀነባበረ ነው” ያሉት አቶ ገደቤ የፀጥታ ቢሮ፣ ፖሊስ ኮሚሽን፣ የርዕሰ መስተዳድሩ ቢሮና የአዴፓ ጽህፈት ቤት ላይም ጥቃት እንደደረሰ ገልፀዋል።

“ጥቃቱ ያልተጠበቀ ነው” የሚሉት አቶ ገደቤ በወቅቱም የክልሉ ፀጥታ ኃይል አካባቢውን ለመቆጣጠር ጥረት ባደረገበት ወቅት ብርጋዲየር ጄኔራሉ እንዳመለጡ ገልፀው፤ ከርዕሰ መስተዳድሩና ከአማካሪያቸው በተጨማሪ አጃቢዎቻቸው የተገደሉ ሲሆን እስካሁን ባለው ሁኔታ የሟቾች ቁጥር እንደማይታወቅ ገልፀዋል።

በባህርዳር ሁኔታዎች ቢረጋጉም የርዕሰ መስተዳድሩን ሞት ተከትሎ ከተማዋ በድንጋጤ መዋጧን አቶ ገደቤ ተናግረዋል።

“ርዕሰ መስተዳድሩ ለክልሉ ህዝብ ሌት ተቀን የሚሰራ ሰው ነበር፤ እንዲህ ባለ ሁኔታ መሰዋቱ በጣም አስደንጋጭና አሳዛኝ ነው” በማለት አቶ ገደቤ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

የሀገር መከላከያ ሠራዊት የጦር ኃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም የዘመቻና መረጃ መምሪያ ዋና ኃላፊ ጄኔራል ብርሀኑ ጁላ በትናንትናው ምሽት የተሰውትን የቀድሞው ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል ሰዐረ መኮንን በመተካት የሚሾሙ ሲሆን፤ በጊዜያዊነት የጠቅላይ ኤታማዦርነቱን ቦታ ተክተው እንዲሰሩም ተደርጓል።

Image may contain: 1 person, smiling, sitting

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 5 years ago on June 23, 2019
  • By:
  • Last Modified: June 23, 2019 @ 9:17 am
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar