www.maledatimes.com የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 19 ቢሊዮን ብር አተረፈ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 19 ቢሊዮን ብር አተረፈ

By   /   July 16, 2019  /   Comments Off on የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 19 ቢሊዮን ብር አተረፈ

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 17 Second

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ2011 በጀት ዓመት 19 ቢሊዮን ብር ያልተጣራ ትርፍ ማስመዝገቡ ታወቀ። ባንኩ ከፍተኛ የገንዘብ ትርፍ በማስመዝገብ በኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ ባንኮች ግንባር ቀደም መሆኑ ተመላክቷል። ከዚህም በተጨማሪ የትርፍ ዕድገቱ ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር ከፍተኛ ሲሆን በመቶኛ ሲሰላም ከ90 በመቶ በላይ እንደሚሆን ታውቋል። በ2011 በጀት ዓመት ግማሽ ዓመት ላይ 9 ነጥብ 4 ቢሊዮን ያተረፈው ባንኩ በ2011 ግማሽ ዓመት ላይ 29 ነጥብ 4 ብር ቢሊዮን ብር ተቀማጭ ገንዘብ ማሰባሰቡን ይፋ አድርጓል። ባንኩ በተመሳሳይም 40 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ብድር መስጠቱም ተጠቅሷል።

በመቀነስ ከፍተኛ መቀዛቀዝ ታይቶበት እንደነበር የሚታወስ ነው። ለዚህም የባንኩ የሥራ ኀላፊዎች ስለተፈጠረው የትርፍ መቀዛቀዝ ሲያስረዱ በወቅቱ በነበረው የውጭ ምንዛሬ ማሻሻያ በትርፉ ላይ ጉልህ ለውጥ እንዳስከተለ ገልፀው ነበር። በቀዳሚ ዓመታት የታየው የትርፍ መቀዛቀዝ በ2011 ግማሽ ዓመት ብቻ ባንኩ የአምናውን ሙሉ ዓመት ትርፍ የበለጠ ሲሆን ምንጮች ለማለዳ እንደገለጹት በአሁኑ በጀት ዓመት 19 ቢሊዮን ብር ከፍ በማድረግ ከፍተኛ ትርፍ ማስመዝገቡ ታውቋል። ባንኩ በውጭ ምንዛሪ በኩልም እስከ 2011 ግማሽ ዓመት ድረስ 3 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ የውጪ ምንዛሬ ለደንበኞቹ ፈቅዷል። ከ1 ሺሕ 200 በላይ ቅርንጫፎች በመላው አገሪቱ በመክፈት ቀዳሚ የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፥ 20 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት ጠቅላላ ጥሪት ባለቤት በመሆን ከአፍሪካ ግንባር ቀደም ተጠቃሽ ባንክ ነው። ባንኩ 34 ሺሕ በላይ ሠራተኞችን በኹሉም ቅርንጫፎቹ ያስተዳድራል። ባንኩ በመላው ኢትዮጵያ ባሉት ቅርንጫፎቹ 21 ሚሊዮን የሚደርሱ ደንበኞች አሉት ተብሎ ይታመናል። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አሁን ያስመዘገበው ትርፍ ከሌሎች ተወዳዳሪ የግል ባንኮች ጋር ሲተያይ እጅግ ሰፊ ልዩነት ያለው ሲሆን አዲስ ማለዳ በቁጥር 35 ዕትሟ ባስነበበችው ዘገባ ከግል ባንኮች በቀዳሚነት አዋሽ ባንክ 3 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር ያልተጣራ ትርፍ ማስመዝገቡ ታውቋል ። ይህም ከንግድ ባንክ ትርፍ ጋር ሲነፃፀር የ15 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ልዩነት እንዳለው ለመረዳት ተችሏል።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar