ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ተፈናቅለው በኦሮሚያ ክልል ተጠልለው ለነበሩና ወደ ቀድሞ ቀያቸው የተመለሱ ከ70 ሺሕ በላይ የሚሆኑ ዜጎች የክልሉ አደጋ ሥጋት አመራር ጽሕፈት ቤት በመንገድ ብልሽት ምክንያት እርዳታ ማከፋፈል አለመቻሉ ታወቀ። ከቦሎጅንፎይና ያሶ ወረዳ ተፈናቅለው ሀሮ ሊሙ እንዲሁም ነቀምት ተጠልለው የነበሩት እነዚህ ተፈናቃዮች የሰብኣዊ እርዳታው በመቋረጡ ችግር ውስጥ መግባታቸውን አስታውቀዋል። በመስከረም 2011 ላይ በአካባቢዎቹ ተፈጥሮ በነበረው ግጭት ከቀዬአቸው ተፈናቅለው የነበሩት ተመላሾቹ ከኢኮኖሚ እና ከሰብኣዊ እርዳታ መቋረጥ ችግሮች ባሻገርም የደኅንነትና የጸጥታ ሥጋት እንዳልባቸውም በተደጋጋሚ ሲገልጹ ይሰማል። ተፈናቃዮቹ ወደ ቀድሞ ቀያቸው ሲመለሱ የመኖሪያ ቤታቸው በመውደሙ፣ የእርሻ መሬታቸው ከጥቅም ውጪ በመሆኑና መሰረታዊ ፍላጎቶቻቸውን ማሟላት በማይችሉበት ሁኔታ ላይ በመገኘታቸው ድጋፉ መቋረጥ ከባድ አደጋ እንደጋረጠባቸው እንዳለው ተናግረዋል። የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ታረቀኝ ተሲሳ፣ ለተፈናቃዮቹ የሚቀርቡ ድጋፎችን የማዳረስና ማሰራጨት ችግሮች መኖራቸውን ተናግረው “በቂ የሆነ እርዳታ በክልሉ አለ፤ ነገር ግን በቡረ አና ሀሮ ሊሙ ወረዳ ለተጠለሉት ሰዎች እርዳታውን ለማድረስ በአካባቢው የመንገድ ብልሽት ሳቢያ ማድረስ አልተቻለም” ሲሉ ተናግረዋል። መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን በማስተባበር ሰብኣዊ ድጋፍ ለሁሉም ተፈናቃዩች እንዲዳረስ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ያስታወቁት ታረቀኝ፣ የክልሉ የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ጽሕፈት ቤት ችግሮቹን በአጭር ጊዜ ለመፍታት እየሠራ መሆኑን ገልጸዋል። ከ73 ሺሕ በላይ የሚሆኑ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው የነበሩ ዜጎች ወደ ቀድሞ ቀያቸው የተመለሱ ሲሆን፣ እነሱን መልሶ ለማቋቋም የክልሉ መንግሥት 13 ሚሊዮን ብር መድቦ እየሠራ መሆኑም ታውቋል። ታረቀኝ እንደገለጹት፣ ተፈናቃዮቹ ከሥጋት ነጻ ሆነው ወደ ቀድሞ የማምረት ሥራችው በመመለስ እራሳቸውንና ቤተሰባቸውን መርዳት እንዲችሉ ከክልሉ መንግሥት ትልቅ እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑን ለማለዳ ተናግረዋል። ሥራቸውን እንዲጀምሩም ለአርሶ አደሮች የእርሻ መሣርያ ማሰራጨትን ጨምሮ የተለያዩ ድጋፎች እየተደረጉ መሆኑንም አክለው ገልጸዋል። በተመሳሳይ ባሳለፍነው ሳምንት በመተከል ዞን በተፈጠረው ግጭት፥ ከዳንጉር እና ፓዌ ወረዳዎች የተፈናቀሉ ከ3 ሺሕ በላይ ዜጎች 5 በሚሆኑ በመጠለያ ጣቢዎች ተጠልው እንደሚገኙም አመልክተዋል። ኹለተኛ ዙር እርዳታ ላልደረሳቸው ሰዎች እርዳታውን በአህያ፣ በፈረስና በጋሪ በመጠቀም ወደ ቦታው ለመላክ እንቅስቃሴ መጀመሩን ያወሱት ታረቀኝ፣ ለሕፃናቱ አልሚ ምግቡን በፈጥነት ለማድረስ እየተሠራ ነውም ብለዋል።
ወደ ቀያቸው የተመለሱ የቤኒሻንጉል ተፈናቃዮች እርዳታ ተቋርጦብናል አሉ!
Read Time:1 Minute, 27 Second
- Published: 5 years ago on July 16, 2019
- By: maleda times
- Last Modified: July 16, 2019 @ 7:14 pm
- Filed Under: Addis Admas, AFRICA, EASTAFRICA, Maleda Media, Media, ማለዳ ራዲዮ, ኣማርኛ, ፍትሕ
- Tagged With: ወያኔ, ለሰላምና ፍትህ ሰባኪያን የእድሜ ልክ ፤ ለነፍስ ገዳይ የአምስት አመት እስራት!, መንግስት, አብይ, ኢሳት, ወደ ቀያቸው የተመለሱ የቤኒሻንጉል ተፈናቃዮች እርዳታ ተቋርጦብናል አሉ!, ዘመነ ኦሮሞ ወረራ, የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ ወደ ሃገሩ እንዲመለስና የጀግና አቀባበል እንደሚያደርጉለትም ገልፀዋል!
Average Rating