ፓወር ኮን የግንባታ ተቋራጭ ድርጀት ለመንግሥት መክፈል የነበረበትን 51 ሚሊዮን ብር ግብር ሰውሯል በሚል በፌደራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ንግድ ችሎት ክስ ተመሰረተበት።
በድርጅቱ ግብይት ላይ ከ2006 ጀምሮ በተሠራ የምርመራ ኦዲት 25 የሚሆኑ ሐሰተኛ ደረሰኞችን ተጠቅሟል በሚል በግብር ስወራ ክስ ዐቃቤ ሕግክሱን መስርቷል። በሁሉም የግብር ዓይነቶች መንግሥት ማግኘት የነበረበትን ገቢ ሰውሯል በሚል በድርጅቱ ላይ በሰኔ ወር መጨረሻ ክስ መመስረቱንም ለማወቅ ተችሏል።
የኮንስትራክሽን ዘርፉን ጨምሮ በተለያዩ ዘርፎች ላይ እየታየ ያለው የሐሰተኛ ደረሰኝ አጠቃቀም እየጨመረ መምጣቱን የገቢዎች ሚኒስቴር መግለጹ ይታወቃል።
በሚኒስቴሩ ፈቃድ የወጡ የሺያጭ መመዝገቢያ ማሽኖችን ለሕገወጥ ዓላማ በመጠቀም ሐሰተኛ ሰነዶችን በማተም የሚደረጉ ግብይቶች እየተንሰራፉ የመጡ መምጣታቸውን እና ደረሰኞቹን ወደ ገበያ የሚያስገቡ ግለሰቦች ላይ እርምጃ መውሰድ መጀመሩን ሚኒስቴሯ የኮንስተራክሽን ድርጅቶች በበኩላቸው የግብዓት በሚቀርቡላቸው ወቅት የሚያቀርቡት ግለሰቦች ሐሰተኛ ደረሰኞችን እንደሚያቀርቡላቸው እና ከመመሳሰላቸው የተነሳ እንደሚቸገሩ ይገልፃሉ።
ከግንባታ ሥራው ባሕሪ ጋር በተያየዘም የተለያዩ ግብዓቶች ወደ ግንባታ ቦታቸው በሚቀርቡ ጊዜ ደረሰኞችም እንደሚመጡ እና ይህም ለችግር እንዳጋለጣቸው ሲናገሩ ይደመጣሉ። በተለይም የሺያጭ መመዝገቢያ መሣሪዎች ከመሰወራቸው ጋር ተያይዞ በሕጋዊ መልኩ በወጡ መሣሪዎች ሐሰተኛ ግብይቶች መፈፀማቸው ራስ ምታት እንደሆኑበት ሚኒስቴሩ ሲገልፅ ቆይቷል።
በተጨማሪም ማንኛውም ግብይት ድርጅቱ በተመዘገበበት አድራሻ መደረግ እንዳለበት እና የጠፉ እንዲሁም ሕገወጥ ድርጊት እየተፈፀመባቸው ያሉ ማሽኖችን ዝርዝር በማውጣት በማስጠንቀቅ ላይ እንደሚገኝ ይታወቃል።
Average Rating