www.maledatimes.com በደብረ ማርቆስ 31 የጥቃቅንና አነስተኛ አንቀሳቃሾች በጎርፍ አደጋ ወደሙ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

በደብረ ማርቆስ 31 የጥቃቅንና አነስተኛ አንቀሳቃሾች በጎርፍ አደጋ ወደሙ

By   /   August 5, 2019  /   Comments Off on በደብረ ማርቆስ 31 የጥቃቅንና አነስተኛ አንቀሳቃሾች በጎርፍ አደጋ ወደሙ

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 20 Second

በምሥራቅ ጎጃም ዞን፣ ደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር የሚገኘው የሁሰታ ወንዝ ሞልቶ ባደረሰው የጎርፍ አደጋ ምክንያት 25 አባወራዎች፣ 111 ቤተሰብና 31 የጥቃቅንና አነስተኛ አንቀሳቃሾች በጎርፉ ጉዳት ደረሰባቸው።

ከሐምሌ 18/2011 ጀምሮ እየጣለ ባለው ከባድ ዝናብ ምክንያት ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ተሽከርካሪም ሆነ ሰው ማለፍ ባለመቻሉ በመማር ማስተማሩ ላይም መስተጓጎል እየፈጠረ ነውም ተብሏል።

የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ተወካይ አስምሮም ሞስነህ ለአዲስ ማለዳ እንደተናገሩት፥ ከተማ አስተዳደሩ በጎርፉ ምክንያት ጉዳት ለደረሰባቸው አባወራዎች ከ71 ሺሕ ብር በላይ የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል። ችግሩን በጊዚያዊነት ለመከላከል 2 ኤክስካቫተሮችን በመመደብ ጎርፍ ወደ ሰፈሮቹ እንዳይገባ የመከላከልና ደለል የማውጣት ሥራ እየተሠራ እንደሆነም አስታውቀዋል።

ከተማ አስተዳደሩ በጎርፍ አደጋው ጉዳት የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ታፈረ መላኩ (ዶ/ር) ጎርፉ በመማር ማስተማሩ ላይ እንቅፋት እንዳይሆን በእግረኛ መንገዱ ላይ ከፍ ያለ ለሰዎች መሸጋገሪያ አገልግሎት የሚሰጥ ድልድይ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። ከብሔራዊ የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ባገኘነው መረጃ መሰረት፥ በኹለት ወር ውስጥ ብቻ በሰባት ክልሎች በ38 ወረዳዎች በደረሱ የጎርፍ አደጋዎች 42 ሺሕ 417 ቤተሰቦች ከቀያቸው ተፈናቅለዋል።

ስድስት ሰዎችና 3 ሺሕ 256 እንስሳት ሞተዋል የሞቱ ሲሆን በ6 ሺሕ ሔክታር በላይ መሬት ላይ የበቀለ ሰብልም ወድሟል። 62 ኩንታል ማዳበሪያ የመወደመ ሲሆን የጎርፍ አደጋዎቹ የደረሱት ካለፈው ግንቦት ወር ጀምሮ እንደሆነም ታውቋል። ወረዳዎቹ በደቡብ፣ በአፋር፣ በአማራ፣ በጋምቤላ፣ በኦሮሚያ፣ በሶማሌና በትግራይ ክልሎች የሚገኙ ሲሆን የጎርፍ አደጋው ከፍተኛ ጉዳት ባደረሰበት በአፋር ክልል የሚገኙ 36 ሺሕ ቤተሰቦች እንዲፈናቀሉ ምክንያት መሆኑም ተገጿል። በአደጋው 2 ሺሕ 210 እንስሳት እንደሞቱም ሪፖርቱ አመልክቷል። ከአፋር በመቀጠል ከፍተኛ የጎርፍ አደጋ በተመዘገበበት በደቡብ ክልል በ13 ወረዳዎች የጎርፍ ጥቃት ተከስቷል።

በአደጋው 5 ሺሕ 958 ቤተሰቦች ከቀያቸው እንደተፈናቀሉ፣ በ4 ሺሕ 721 ሔክታር ላይ የበቀለ ሰብል እንደወደመ፣ በ150 መኖርያ ቤቶች ላይ ከባድ ጉዳት እንደደረሰ፣ በ13 ትምህርት ቤቶችና በሌሎች የመሠረተ ልማት አውታሮች ላይም መጠነ ሰፊ ጉዳት እንደተከሰተ የኮሚሽኑ ሪፖርት ያሳያል።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 5 years ago on August 5, 2019
  • By:
  • Last Modified: August 5, 2019 @ 8:58 am
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar