መብቶች ጋር በተያያዘ በተነሳው ውዝግብ ራይድ ባቀረበው አቤቱታ መሰረት በንግድ ውድድር እና ሸማቾች ጥበቃ ባለሥልጣን ምርመራ ተጀመረ። ከአራት ወራት በፊት ራይድ ትራንስፖርት አገልግሎት የስያሜው የባለቤትነት መብት ይገባኛል በሚል ለኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ጽሕፈት ቤት እና ለንግድ ውድድር እና ሸማቾች መብት ጥበቃ ባለሥልጣን ማመልከቻ ማስገባቱን ተከትሎ ነው ምርመራው የተጀመረው።
‹‹ራይድ›› የሚለው ቃል በራሱ አገልግሎትን የሚያመላክት ገላጭ ቃል እንጂ ስያሜ መሆን የሚችል ቃል አይደለም ያሉት የዛይ ራይድ ሜትር ታክሲ መሥራች እና ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሀብታሙ ታደሰ፣ ከራይድ ትራንስፖርት አገልግሎት ከአንድ ዓመት ቀድመው ወደ ሥራ መግባታቸውን እና በዘርፉ መጀመሪያው መሆናቸውንም ይናገራሉ። ‹‹የኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ጽሕፈት ቤት ለራይድ ከአንድ ዓመት በፊት የንግድ ስያሜ ባለቤትነት ማረጋገጫ መፍቀዱ አግባብ ያልሆነ መሆኑን እያወቅን፣ ያለው ገበያ ሰፊ መሆኑን ተከትሎ አብሮ ለመሥራት እና ለመነጋገር ያደረግነው ጥረት አልተሳካም›› ሲሉም ተናግረዋል።
የራይድ ትራንስፖርት ባለቤቶች ዛይ ራይድ የሚለው ስያሜ ከእኛ ጋር መመሳሰሉ ደንበኞች ላይ መደናገር በመፍጠሩ የእኛ አገልግሎት እየመሰላቸው ወደ ዛይ ራይድ እየሄዱ ነው ብለው ክስ በማቅረባቸው ጉዳዩን የንግድ ውድድር እና ሸማቾች ጥበቃ ባለሥልጣን በመመልከት ላይ እንደሚገኝ ሀብታሙ ጌታቸው ተናግረዋል።
እንደ ሀብታሙ ታደሰ ገለፃ፣ ራይድ ትራንስፖርት እኛ ከአራት ዓመታት በፊት ዛይ ራይድ በሚል ስም ለኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ጽሕፈት ቤት ያስገባነውን ስያሜ የራሳቸው በማስመሰል ለማስመዝገብ መሞከራቸውን እና ለጽሕፈት ቤቱ ያስገቡትን ማመልከቻ ማግኘት መቻላቸውን፣ ይህንንም ተከትሎ ባደረግነው ማጣራት በራይድ ስም የተመዘገበ መረጃ ሳይኖር ሰርተፍኬት ማግኘት መቻላቸውን ይናገራሉ።
እንዲሁም ትራንስፖርት ሚኒስቴር የኹለቱንም ቢሮ ባሸገበት ወቅት የራይድ ትራንስፖርት ባለቤት ሳምራዊት ፍቅሩ ጠበቃቸው እና ሌላ አንድ ግለሰብ ቢሮአችን ድረስ መጥተው መታሸጉን ለመመልከት ሲሞክሩ በወቅቱ በአካባቢው በመኖራችን ተመልክተናል፤ የተንቀሳቃሽ ምስል ማስረጃም ይዘናል ብለዋል።
Average Rating