Read Time:2 Minute, 0 Second
በእዚህ ውስጥ ያልተካተቱ በርካታ ሲሆኑ ከነዚህ አንዱ የኢንጂነሪንግ ዳይሬክተር አቶ ዮናስ ዮሀንስ ይገኝበታል።
የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈፃሚ አየር መንገዱን መደበቂያ አድርጎ ውሎ እና አዳሩን ሚዲያ ላይ አድርጎ ተአምር የሰራ ቢያስመስልም ብዙ የተበላሹ እና የተቀበሩ ነገሮች ነገ ላይ ሲመነዘሩ አየር መንገዱን አደጋ ውስጥ የሚጥሉ ነገሮች እንዳሉ የሚያውቁ እና ለውጥ ይመጣል ብለው ሲጠብቁ የነበሩ ሰራተኛ አቶ ተወልደ በአየር መንገዱ ገንዘብ ለተለያዮ ሚዲያዎች በስፖንሰር ድርድር እና በታከለ ኡማ(የዮንቨርሲቲው የቦርድ አባል) እና በጃዋር መሀመድ አስተባባሪነት ከአዲስ አበባ ዮኒቨርስቲ የክብር ዶክትሬት ማግኘት እና እንደገና ስሙን የሚያድሱ መድረኮች እየተመቻቹለት በመምጣቱ ስሙን እየገነባ እሱ ብቻ ለአየር መንገዱ ያለ ብቸኛ አማራጭ እንዲሆን ዛሬም የሱን ስብስብ እያጠናከረ ነገ አየር መንገዱን በብቃት መምራት የሚችሉ ሰራተኞችን እንዲለቁ የመግፋት ሴራውን ቀጥሎል። አየር መንገዱ ብቃት ያላቸውን ሰራተኞች ማጣቱ እንዱ ዋነኛው ችግር ቢሆንም ትክክለኛ እድገት እንደሌለ የሚያሳየን በቅርቡ በገንዘብ ሚኒስቴር የወጣው ሪፖርት ላይ እንደተገለፀው ባለፉት 5 አመታት ይሄ ድርጅት የብድሩን ወለድ ብቻ ሲከፍል እንደነበር የተገለፀ ሲሆን ይሄ እየተገፋ የመጣ እዳ ነገ ላይ ዋናውን ብድር ክፈሉ የሚል ግዳጅ ሲመጣ ይሄ አየር መንገድ እጣ ፈንታው በቻይና መወረስ ነው።
በቀጣይ የሚቀርቡ
*ማኔጅመንቱ ተጠያቂ የሚያደርጉን ሚስጢሮች የድርጅቱ ሰራተኞች በተለያየ መንገድ ለማጋለጥ የሚያደርጉትን እንቅስቃሴዎች ለማፈን እየሄደባቸው ስላለው መንገዶች እና ከመንግስት ተቀባይነትን ለማግኘት አየር መንገዱ ውስጥ እራሱን በመደበቅ እያደረገ ስላለው እንቅስቃሴ
* የሰው ሀይል አስተዳደሩ በከፊል ከአየር መንገዱ ውጪ በተለየ ምልመላ በተቀጠሩ እና በፍጥነት ባደጉ ሰራተኞች የተሞላ እንደሆነና ቀጥታ ከዋና ስራ አስፈፃሚው ጋር እንደሚሰሩ። ሰው ሀይል አስተዳደሩ ከላይ በሚመጣ ትእዛዝ የታዘዘውን እንደሚቀጥር፣ በሶሻል ሚዲያ ሰራተኛውን እንደሚሰልል፣ እንደሚከታተል፣ እንደሚቀጣ፣ ከስራ ጋር የተያያዘ ሰበብ በመፋጠር ከስራ እንደሚያግድ፣ እንደሚያባርር።
*የውጭ ሀገር ጥሩ ክፍያ ያላቸው ምደባዎችና ሹመቶች በተደጋጋሚ ለአንድ ወገን ብቻ በከፊል እንደ ቀድሞው መሰጠት መቀጠሉን እንዲሁም የተወሰኑ ወገኖች ላይ ብቻ ያነጣጠረ ሌላ ምክንያት እየቀቡ ከስራ ገበታቸው የሚባረሩ ፣የሚቀጡ እና ተገፍተው እንዲለቁ እየተደረጉ ስላሉ ሰራተኞች። እየለቀቁ ያሉትን ሰራተኞች ስም ዝርዝር ማየት ይቻላል ከስራ አስፈፃሚው ወገን ማንም እንደሌለ ያሳያል
*አቶ ተወልደ ከጃዎር እና ከታከለ ኡማ ጋር የፈጠሩት የእከክልኝ ልከክልህ ቁርኝት
*የሰራተኛ ማህበሩን እንደ ቀድሞ ጊዜ በማስፈራራት እና በማባረር የማኔጅመንቱ ተላላኪ ለማድረግ እየተደረገ ስላለው ወከባ
*የቴክኒሺያን እና የፓይለት ማህበሮች ላይ እንደ ቀድሞ ጊዜ በማስፈራራት እና በማባረር የማኔጅመንቱ ተላላኪ ለማድረግ ወይም ለማፍረስ እየተደረገ ስላለው ወከባ
* ከዚህ ቀደም ሰራተኛው ላይ በርካታ በደል ሲፈጽሙ፣ ሲያስባርሩ የነበሩ ሰራተኞች እንደገና ወደየ ቦታቸው መመለስ መጀመራቸው
*ሙስናዋች
*በዚሁ ከቀጠለ ለወደፊት በአየር መንገዱ ውስጥ መፈጠራቸው የማይቀር ነገሮችን ለህዝብ እና ለመንግስት ይፉ ለማድረግ በሰሜን አሜሪካ የሚኖሩ የቀድሞ የአውሮፕላን ቴክኒሽያኖች እና መሀንዲሶች በመሰባሰብ አሁን ያለው ማኔጅመንት በሚዲያ ላይ ጊዜ እና ገንዘብ በማጥፋት እየሸፈነ ያለውን እውነታዎች ለማጋለጥ እየተንቀሳቀሰ ሰመሆኑን
*እውነት አሁን አየር መንገዱ አድጎል ወይ?
* እና ሌሎችም
Sponsored by Revcontent
Average Rating