የሕወሓትን ወታደራዊ እንቅስቃሴ በቅርብ እየተከታተለ ይፋ የሚያደርገው ከራያ ማንነት ኮሚቴ የሕዝብ ግንኙነት ሀላፊው አቶ ደጀኔ አሰፋ እንደገለጸው የጦርነት እንቅስቃሴ ለማድረግ ሰፊ ዝግጅት ሲያደርግ የቆየው ሕወሓት ዛሬ ጥቅምት 9/2012 ልዩ ሀይሉን ወደ አላማጣ እያስገባ መሆኑን እና የሰሜን ዕዝ ይህ ተስፋ የቆረጠ ሀይል ሕዝብ ላይ ጉዳት እንዳይደርስ ጥንቃቄ እንዲወስድ ጥሪ አቀረበ።
“ዛሬ መስከረም 9/2012 በዚህ ሰዓት ከግራካህሱ ወደ ራያ አላማጣ ከተማ እየገባ ያለ የትህነግ ልዩ ሃይል ነው። ይህ ተስፋ የቆረጠ ድርጅት አጥፍቶ በመጥፋት የመጨረሻ በቀሉን በህዝባችን ላይ እንዳይፈፅም መረጃው ለመከላከያ ሰራዊት በተለይም ለሰሜን እዝ እንዲደርስ እንሻለን።” ሲል የራያ ማንነት ኮሚቴ የሕዝብ ግንኙነት ሀላፊው ጥሪ አድርጉዋል።
ሰሞኑን ሕወሓት በጉልበት ወደ አካለለው ራያ ተገኝቶ ለአካባቢው ሚሊሻዎች በነፍስ ወከፍ ጥይት፣ቃሬዛ፣አካፋና ዶማ ጭምር ማከፋፈሉን መዘገባችን አይዘነጋም።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ትላንት በሚሊኒየም አዳራሽ መደመር የተሰኘውን አዲሱ የገዢው ፓርቲ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ፖሊሲ ይሆናል የተባለ መጽሐፋቸውን ሲያስመርቁ ጦርነት እንደማያስፈልግ ልዩነትን በሰለጠነ እና ሰላማዊ መንገድ ብቻ መፍታት እንደሚገባ አንስተው በስም አይጥቀሱ እንጂ መቀሌ ከመሸጉ በሁዋላ ሆቴል ተቀምጠው ውስኪ ሲራጩ የሚኖሩትን ጠንከር አድርገው መውቀሳቸው አይዘነጋም።
የሕወሓትን የጦርነት ነጋሪት የታከለበት መግለጫ ተከትሎ ከኢህአዴግ እና ኦዴፓ ጠንከር ያለ መግለጫ ማውጣታቸው አይዘነጋም።
Wondering where the comments are? We encourage you to use the share buttons below and start the conversation on your own!
- Click to email a link to a friend (Opens in new window)
- Click to share on Facebook (Opens in new window)
- Click to share on Twitter (Opens in new window)
- Click to share on LinkedIn (Opens in new window)
- Click to share on Pinterest (Opens in new window)
- Click to share on Tumblr (Opens in new window)
- Click to print (Opens in new window)
Average Rating