ማክሰኞ ጥቅምት 25 ቀን 2012 ዓ.ም. ከቀትር በኋላ በአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት፣ የዘመናዊ ስናይፐር የጦር መሣሪያ ተጓዳኝ ዕቃዎች (Accessories) በቁጥጥር ሥር ዋሉ፡፡
የገቢዎች ሚኒስቴር ማምሻውን እንዳስታወቀው፣ በአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ የግል መገልገያ ዕቃዎችን ሽፋን በማድረግ በዓረቢያን መጅሊስ ውስጥ በሕገወጥ መንገድ ተደብቀው በግለሰብ ስም የመጡ የተለያዩ የስናይፐር የጦር መሣሪያ ተጓዳኝ ዕቃዎች ተይዘዋል፡፡
በኤክስሬይና በዕቃ ፍተሻ ኦፊሰሮች አማካይነት የስናይፐር ጦር መሣሪያ ተጓዳኝ ዕቃዎች በቁጥጥር ሥር ሲውሉ፣ ስሙና ማንነቱ ያልተገለጸ ተጠርጣሪም አብሮ መያዙን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
የጦር መሣሪያው ተጓዳኝ ዕቃዎች ከየት እንደመጡና በየትኛው አየር መንገድ እንደተጓጓዙ ግን አልተገለጸም፡፡ የተጓዳኝ ዕቃዎቹ ሥሪት የት እንደሆነም አልታወቀም፡፡
በኢትዮጵያ ሕገወጥ የጦር መሣሪያዎች ዝውውር በመስፋፋቱ ምክንያት፣ እንዲህ ያለው የጦር መሣሪያ ተጓዳኝ ዕቃዎች በኤርፖርት በኩል ሊገቡ ሲሉ መያዛቸው መደናገር መፍጠሩን ለማወቅ ተችሏል፡፡
እጅግ ዘመናዊ ለሆነ ስናይፐር የጦር መሣሪያ በተጓዳኝነት የሚያገለግሉ ዕቃዎች በኤርፖርት በኩል ወደ አገር ውስጥ ሊገቡ ሲሉ መያዛቸው፣ የጦር መሣሪያ ዝውውሩ ምን ያህል አደገኛ እየሆነ እንደመጣ ማመላከቻ ነው ተብሏል፡፡
Wondering where the comments are? We encourage you to use the share buttons below and start the conversation on your own!
- Click to email a link to a friend (Opens in new window)
- Click to share on Facebook (Opens in new window)
- Click to share on Twitter (Opens in new window)
- Click to share on LinkedIn (Opens in new window)
- Click to share on Pinterest (Opens in new window)
- Click to share on Tumblr (Opens in new window)
- Click to print (Opens in new window)
Average Rating