ከ140 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ንብረት ወድሟል
በ2012 በጀት ዓመት የመጀመርያዎቹ ሦስት ወራት ውስጥ፣ በአዲስ አበባ ከተማ በደረሱ አደጋዎች የ28 ሰዎች ሕይወት ማለፉ ታወቀ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ እሳትና አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን እንደገለጸው፣ ሕይወታቸው ካለፈው 28 ሰዎች በተጨማሪ ግምቱ ከ140 ሚሊዮን ብር በላይ የሆነ ንብረት ወድሟል፡፡ ይኼ ሁሉ ውድመት በአጭር ጊዜ ውስጥ የደረሰው በ60 የእሳት ቃጠሎዎችና 65 ሌሎች አደጋዎች መሆኑን፣ በኮሚሽኑ የአደጋ ማሽነሪዎች ምሕንድስና ማዕከል ኃላፊ አቶ ጥላሁን ቶላ ተናግረዋል፡፡
በሩብ ዓመቱ የወደመው ንብረት ግምት 143,797,310 ብር እንደሆነ፣ ካለፈው ዓመት አደጋ ጋር ሲነፃፀር በስምንት እጥፍ ከፍ ያለ መሆኑን ኃላፊው አስረድተዋል፡፡ በደረሰው አደጋ ሊወድም ይችል የነበረ ከሁለት ቢሊዮን ብር በላይ ንብረት ማዳን መቻሉንም አክለዋል፡፡ የተከሰቱት አደጋዎች 125 መሆናቸውን፣ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በዘጠኝ እጥፍ መጨመራቸው ታውቋል፡፡
ኮሚሽኑ በሦስት ወራት ውስጥ ለ6,095 ሰዎች የቅድመ ሆስፒታልና የአምቡላንስ አገልግሎት መስጠቱን አስታውቋል፡፡ አዲስ አበባ ከአምስቱ መውጫ በሮች ጋር ግንኙነት እንዳላት ጠቁመው፣ ግንኙነቱ በርካታ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያለው ቢሆንም፣ ለበርካታ ሥጋቶችም ተጋላጭ እንደሚያደርጋት ኃላፊው ጠቁመዋል፡፡
ሌላው ከተማዋ የምትገኘው በምሥራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ 100 ኪሎ ሜትር ራዲየስ ውስጥ ስለሆነ፣ በከተማዋ የሚገኙ ሕንፃዎች ለአደጋ ተጋላጭ እንዲሆኑ ማድረጉንም አክለዋል፡፡
Wondering where the comments are? We encourage you to use the share buttons below and start the conversation on your own!
- Click to email a link to a friend (Opens in new window)
- Click to share on Facebook (Opens in new window)
- Click to share on Twitter (Opens in new window)
- Click to share on LinkedIn (Opens in new window)
- Click to share on Pinterest (Opens in new window)
- Click to share on Tumblr (Opens in new window)
- Click to print (Opens in new window)
Average Rating