www.maledatimes.com Ethiopian top ten billboard music chart for this week 1 40/60 - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

Ethiopian top ten billboard music chart for this week 1 40/60

By   /   November 18, 2012  /   Comments Off on Ethiopian top ten billboard music chart for this week 1 40/60

    Print       Email
0 0
Read Time:5 Minute, 59 Second

Ethiopian top ten billboard music chart for this week
1 40/60
አቀንቃኞቹ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ሲሆኑ
መሀላቸው ራሱ ከ40/60 ይነጥለኝ እንደሆነ ብርሌ.ኮም ከጠጅ ቤት አካባቢ ዘግቦዋል

2 ድምፃችን ይሰማ
እነዚህ የባንድ አባላት በአብዛኛው ሙዚቃቸው ሀይማኖታዊ ሲሆን በኮንሰርታቸው ላይ አረንጓዴና ቢጫ ማሊያ በማውለብለብ ይታወቃሉ በቅርቢ በሚያቀርቡት ኮንሰርት ላይ ቀይ ማሊያ እንደሚለብሱ ይጠበቃል
3 አባይን የደፈረ ጀግና
ይህ ሙዚቃ ለረጅም ጊዜ የሙዚቃውን ሰንጠረዠ ተቆጣጥሮ የቆየ ሲሆን በነውጠኛ የኢህአዲግ ደጋፌዎች ብሄራዊ መዝሙርነት እያገለገለ ይገኛል
4 ጅራፍ
በሀ/ማሪያም ደስአለኝ
እኒህ አዲስ ራፐር በቅርቡ በፓርላማ ባሰሙት የራፕ ኮንሰርት ከhard rock የሙዚቃ ስልት ጋር አቀላቅለው የተጫወቱት
ጅራፍ እራሱ ገርፎ
እራሱ ይጮሀል እንዲሉ ተረቱ
የሚል ግጥም ያለው ዜማ ከአንዱ ታዳሚ በስተቀር በሌሎቹ ወንበር አሟቂዋች ተወዶላቸዋል

5 ዘ አልወጣም
በአዜብ መስፍን
ይህን አዲስ ዜማ ያቀነቀኑት የሙዚቃው ኢንዱስትሪ ለሀያ አመታት በጉልበት ይሁን በፍቅር ባልታወቀ ሁኔታ የተቆጣጠሩት የአዜብ ጎላ
የስንብት ዜማ ሲሆን ጉልበት እና ድምጽ እያነሳቸውም ቢሆንም ጥሩ አርገው ተጫውተውታል
ይህ ዜማ በድምጽ እጥረት ምክንያት የሴትየዋ የመጨረሻው የbillboard top ten ዘፈናቸው ይሆናል ሲሉ አንዳንድ የወልቂጤ ከተማ አዝማሪዎች ትንታኔ ሰተውበታል

6 እኛንስ አልዳኑም ሊለን ነው ?
በLegendary artist መስፍን ወ/ማሪያም የተቀነቀነ ጥያቂያዊ ዜማ ሲሆን
ሙዚቃው የተለቀቀው ከአመት በፊት gospel ሙዚቀኛ ለነበሩት ኦቦ ሀ/ማሪያም እናቴ በሀይማኖት አልዳነችም እፀልይላታለሁ ለሚለው ጋቢ ዜማቸው
የመልስ ዘፈን መሆኑ ለየት ያደርገዋል ተብሏል አንዳንድ የቦሌ ራፐሮች ይህ ሙዚቃ የአሜሪካኖቹን የኢስት እና ዌስት ኮስት የራፐሮች ጦርነት አስታውሶናል ሲሉ አማረዋል
7 ፎርፌ
በታዋቂው ሱዳናዊ ሙዚቀኛ የተዘፈነ አዲስ ዜማ ሲሆን
እንዲህ መሆናችሁን ብናውቅ ኖሮ በፎርፌ እንሸነፍላችሁ ነበር የሚል ይዘት ያለው ለኢትዬጵያ እግር ኳስ ደጋፊ የተበረከተ ወንድማዊ እና ቅናታዊ ዜማ ዜማ ነው
8 አማራ ወ ኦርቶዶክስ
በአቦይ ስብሀት
እኝህ አወዛጋቢ ሙዚቀኛ ከአልበም ይልቅ ነጠላ መልቀቅ ይወዳሉ ቶሎ ቶሎ በሚለቁት የአንድ ሳምንት ነጠላ ሙዚቃዎች ኢትዬጵያዊው ኤኮን ለመባል በቅተዋል በቅርቡ የለቀቁዋቸው ዜማዎች እንደወረዱ በመሆናቸው አቦይ Eminem የሚል ተጨማሪ ማእረግ ተሸልመዋል
9 GTP plan
ይህ በእንግሊዘኛ የተዜመ ኢትዬጵያዊ ሙዚቃ ሲሆን ኮምፓዘሩ በሞት በመለየታቸው ተሰሚነቱ እየቀነሰ ያለ በስቅታ ካልሆነ የማይነሳ ዜማ ሆኗል በቅርቡም billboard music chart ላይ ተሽቀንጥሮ ይወጣል ሲሉ አንዳንድ የአ.አ አሽሟጣጮች ደስ በሚል ስቃይ አማረዋል
10 ኮብል ስቶን ፎረም ጥቃቅንና አነስተኛ
በጋራ ተደራጅተው ያዜሙት ጃዝ እና ሮክ የሌለበት የታችኛው መደብ አባላት ያዜሙት ዜማ ነው

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on November 18, 2012
  • By:
  • Last Modified: November 18, 2012 @ 11:19 am
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar