www.maledatimes.com ኢትዮጵያ የጥላቻ ንግግርና የሐሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር አዋጅ ልታጸድቅ ነው - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ኢትዮጵያ የጥላቻ ንግግርና የሐሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር አዋጅ ልታጸድቅ ነው

By   /   November 10, 2019  /   Comments Off on ኢትዮጵያ የጥላቻ ንግግርና የሐሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር አዋጅ ልታጸድቅ ነው

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 16 Second

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ ላይ

የኢትዮጵያ ሚኒስትሮች ምክር ቤት ዛሬ ጥቅምት 29/2012 ባካሄደው መደበኛ ስብሰባው የጥላቻ ንግግርና የሐሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የተዘጋጀ ረቂቅ አዋጅ ላይ ተወያይቶ እንዲጸድቅ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መራ።

ከሚኒስትሮች ምክር ቤት የወጣው መግለጫ እንዳመለከተው የጥላቻ ንግግርና የሐሰተኛ መረጃ ስርጭት የሚፈጥረውን ችግር አሁን አገሪቱ ባሏት ሕጎች መፍታት የማይቻል በመሆኑ የጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ረቂቅ አዋጅ አዘጋጅቶ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔ አቅርቦ ነው ውይይት የተደረገበት ተብሏል።

የሚኒስትሮች ምክር ቤት “የጥላቻ ንግግርና የሐሰተኛ መረጃ ስርጭት ለማህበራዊ ህይወት ስምረት፣ ለፖለቲካ መረጋጋት፣ ለአገራዊ አንድነት፣ ለሰብዓዊ ክብር፣ ለብዝሃነት ጠንቅ መሆኑን” ጠቅሶ በረቂቅ አዋጁ ላይ በስፋት መነጋገሩን ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽህፈት ቤት የወጣው መግለጫ አመልክቷል።

ምክር ቤቱም በረቂቅ አዋጁ ላይ በስፋት ከተወያየ በኋላ ማስተካከያዎችን በማድረግ ተቀብሎ ይጸድቅ ዘንድ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ ወስኗል።

መግለጫው ጨምሮም “በተለይ በአሁኑ ወቅት በሕብረተሰቡ መካከል ያሉ መልካም እሴቶች በጥላቻ ንግግሮችና በሐሰተኛ መረጃ ስርጭት ምክንያት በከፍተኛ ደረጃ እየተሸረሸሩና ለአገርም ስጋት የደቀኑ መሆናቸውን” ጠቅሷል።

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በተመራው በዚህ መደበኛ ስብሰባው ላይ ከዚህ የጥላቻ ንግግርና የሐሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የተዘጋጀ ረቂቅ አዋጅ በተጨማሪም በሌሎች ረቂቅ ደንቦችና አዋጆች ላይ ተወያይቶ ውሳኔን አሳልፏል።

ምክር ቤቱ የተመለከታቸው ሌሎች ጉዳዮች ደግሞ የአገሪቱ የመከላከያ ሠራዊት መተዳደሪያ ረቂቅ ደንብ፣ የመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን ማቋቋሚያ ረቂቅ ደንብ፣ የፌዴራል የአስተዳደር ሥነ ሥርዓትን ለመደንገግ በተዘጋጀ ረቂቅ አዋጅ እና በኢትዮጵያና በጅቡቲ መንግሥታት መካከል የተፈጥሮ ጋዝ ቧንቧ መስመር ለማስተላለፍ የተደረገውን ስምምነት ለማጽደቅ የተዘጋጀ ረቂቅ አዋጅ ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል።

የሚኒስትሮች ምክር ቤቱ በዛሬው 75ኛ መደበኛ ስብሰባው ላይ በአጀንዳነት ይዞ የተመለከታቸው ጉዳዮች ላይ መወያየቱንና ማሻሻያ የሚያስፈልጓቸው ላይ ማስተካከያዎች እንዲካተቱ በማድረግ ረቂቅ አዋጆቹ እንዲጸድቁ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሲመራ ረቂቅ ደንቦቹን ደግሞ ሥራ ላይ እንዲውሉ ውሳኔ አሳልፏል።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 5 years ago on November 10, 2019
  • By:
  • Last Modified: November 10, 2019 @ 8:27 am
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar