www.maledatimes.com የለማ ጉዳይ አያሰጋም! ከጋዜጠኛ ካሳሁን ለማ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የለማ ጉዳይ አያሰጋም! ከጋዜጠኛ ካሳሁን ለማ

By   /   November 30, 2019  /   Comments Off on የለማ ጉዳይ አያሰጋም! ከጋዜጠኛ ካሳሁን ለማ

    Print       Email
0 0
Read Time:2 Minute, 28 Second

Mr.Lema Megeressa

የለማ መገርሳን “አልደመርም” ባይነት ተከትሎ ሶሻል ሚዲያ በተለያዩ ቡዙ ተቃውሞዎች፣ጥቂት የማይባሉ ብዥታ ውስጥ መግባት፣የለውጡ ተቃዋሚዎች መፈንደቅና ግራ መጋባቶች … ወዘተርፈ ተስተዉሏል ።ይህ ይጠበቅ ነበር።

አቶ ለማ መገርሳ ” የቲም ለማ ” ፈጣሪና መሥራችና ባለቤት መሆናቸው ያስታውሷል።ከቲም ለማ መመሥረት እስከመዝለቅ ያለው ሂደትና ውጤቱ ድልበድል እንደነበር የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው።ሆኖም መንገዱ አልጋ በአልጋ እንዳልነበር ማንም አይዘነጋውም ።ትግልና የለውጥ አብዮት መንገዱ ለጥ ያለ የአስፋልት መንገድ አይደለም።

አቶ ለማ መገርሳ ይህ ተመክሮ እንዳለው አይካድም ።

ለማ መገርሳ በኦሖዲድ “ቲኬት” ለኢሕአዴግ ለረጅም ጊዜ በህወሃት ተጠርንፎ መሬት ልሶ፣አፈር ምሶና፤ቁልቁልና ሽቅብ ወጥቶ በካድሬነትም በአመራርም ሠርቷል።ወያኔን አገልግሏል ።በመጨረሻም በኦሮሞ ወጣቶች( ቄሮዎች) አልሞት ባይ ተጋዳይነት ሳቢያ ” ቲም ለማ ” ን እንደ አሰባሳቢ ሴል በመጠቀም ትግሉን ለማቀጣጠል መጠቀሙ ታሪክ ሆኖ ተመዝግቧል ።

ለማ መገርሳ ብቻውን የለውጡ መሪ አልነበረም ።አሁን ኦሮምያንና የፌዴራል መንግስቱን በበላይነት የሚመሩ የኦሮሞ አጋሮቹ በዋናነት ይጠቀሳሉ ።ከነዚህም ውስጥ የአሁኑ ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በዋናነት ይጠቀሳል ።

የለማ ስም ሲጠራ የአብይ ስም ይከተላል ።ሁለቱም ቁንጮ መሪዎች ለኢትዮጵያም ለለውጡም ከፍተኛ አስተዋፅኦ አድርገዋል።

በለውጡ ማግስት ሁለቱም የኦሮሞ ፖለቲከኞች ለኢትዮጵያ ሕዝብ አንድነታቸውንና ቀጣይ ትግላቸው ለኢትዮጵያውያንና ለዓለም ህብረተሰብ ለመግለፅ የሄዱበት ክልል የአማራ ክልል ነው።ያላቸውን የቅርብ፣የመካከለኛና የረጅም ጊዜ መፃኢ አኗኗራችንን በጥሩ ቃላት በአማራ ቤተመንግሥት ውስጥ በቀጥታ አስተላልፈዋል ።ቀኑ ታሪካዊ ነበር።

ለማ መገርሳና አብይ አህመድ ያን ወቅት የተናገሩት ማንም አይረሳውም ።

ለማ ” አትዮጵያዊነት ሱስ ነው ” ሲል፣ አብይ አህመድ ደግሞ ” አማራንና ኦሮሞ ልክ እንደ ሠርገኛ ጤፍ ሊለያዩ የማይችሉ የአንድ አገር ሕዝቦች” መሆናቸውን ገልፆ ነበር።በተለይ የኢትዮጵያ ሕዝብ እርስ በርስ የተጋመደ ፣የተዋለደና የተራባ መሆኑን አፅንኦት ሠጥቶ ተናግሯል።ከዚያ በኋላ ሁለቱም መሪዎች በወንድማማችነት ፣በአብሮነትና በ ” ቲም” ስለመሥራታቸው ኢትዮጵያዊያንና የአለም ህብረተሠብ ያውቃል ።

በኦዴፒ ድክመት እነ ጃዋርና ጽንፈኞች ዘልቀው የቀድሞው ኦሖዲድን ውስጥ ዘልቀው መበታተናቸው እየዋለ ሲያድር ቢስተዋልም፤ሁለቱ እንቁ የኦሮሞ ብሔር አባላትና እንቁ ኢትዮጵያዊያን ሊያይል የሚችል ነገር እንደሌለ ግንዛቤ ተወስዷል።በተጠቃሽ ጽንፈኞች ሳቢያ ማን አቋም ይዞ እነደሚወጣ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በዐይነ ቁራኛነት ይጠብቅ እንደነበር በሂደት ታይቷል።ለዚህ የአቶ ለማ መገርሳ ወደ መከላከያ ሚንስትር ከተዘዋወሩ ወዲህ ያሳዩት ዝምታ አይነተኛ ማስረጃ ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል።

ወደ ነጥቤ ስመለስ ፦ ለማና አብይ የአቋም ግጭት ባይኖራቸውም ፤ለማ መገርሳ እሖዲድን ሲገዘግዙ በነበሩት ጃዋር መሐመድ፣እዝቄኤል ገቢሳ፣ፀጋዬ አራርሳና በቀለ ገርባ መጠለፋቸው ይነገራል።ይኸው ነው።ዛሬ ለማ መገርሳ በሌሎች ተጠልፈው በዚች ቀን በቪኦኤ ውስጣቸውን ተንፍሰዋል።

አቶ ለማ መገርሳ ከላይ በተጠቀሱ ዘረኞችና አክቲቪስት ተብዪዎች አሁን ለደረሱበት አቋማቸው ደርሰዋል፤ይሁንና ለማ መገርሳ በጥቂት ጽንፈኞች ሰበካ ሙሉ ለሙሉ ባሕርዩን ሊቀይር እንዳላስቻለው ይነገራል ።አስተዳደጉና የመጣበት መንገድ በአንዴ ሊቀየር አላስቻለውም ።

በአብይ ላይ ያን ያህል በተቃራኒው እንዲቆም አላስቻለውም ።

ለማ መገርሳ አቋሙ አለመደመር ቢሆንም፤ከዐብይ አህመድ ጋር ያሳለፈው ትግልና መስዋዕትነት እየተፈታተነው ይገኛል ።በዚህም ዓይነቱ “አለመደመሩ” እንዳለ ሆኖ የጠቅላይ ሚንስትሩን ልፋት ላለማደናቀፍ ወስኗል።ይህ አቋም ከተያዘ ቆይቷል።በተቻለ መጠን የብልፅግና ፓርቲ ሙሉ ለሙሉ ወደ አንድ ፓርቲ እስኪተቃለል።ይህ የVOA ቃለ መጠይቅ የተደረገው የኢሕአዴግ ሁሉም አጋር ዴርጅቶች 95% በኋላ መዋሃዳቸው ከተረጋገጠ በኋላ ነው።ከዚህም ጋር አቶ ለማ መገርሳ ከማንም ጽንፈኛ የፖለቲካ ድርጅቶች ጋር በመደራደር ከጠቅላይ ሚንስትሩ በተቃራኒው በመቆም ፤ለሽግግሩ የአብይ መንግሥት እንቅፋት አይሆኑም ።በምንም አይነት ከአብይ ጎን ቆመው የመንግስት ተፃሪሩ አይሞክሩም።ፖርቲ አይመሠርቱም

የኖቬል ተሸላሚ የሆኑትትን የኢትዮጵያን ጠቅላይ ሚንስትር አያሳጡትም፤የዓለምን ህብረተሠብ አግራሞት ውስጥ አይከቱም ።

በአጭሩ በመቃወማቸው ወይም ባለመደመራቸው የትላንቱን ትግል አይረሱትም ።Just protest ነው !

በቃ መቃወም ነው።የአብይ “መደመር” ይቀጥላል ።

የለማ መገርሳ ጉዳይ ስጋት አይደለም !!!

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 5 years ago on November 30, 2019
  • By:
  • Last Modified: November 30, 2019 @ 10:07 am
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar