www.maledatimes.com ኢንጂነር አዜብ አስናቀ ላይ የተመሠረተው ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ በዝርዝር በጥቂቱ! - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ኢንጂነር አዜብ አስናቀ ላይ የተመሠረተው ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ በዝርዝር በጥቂቱ!

By   /   December 27, 2019  /   Comments Off on ኢንጂነር አዜብ አስናቀ ላይ የተመሠረተው ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ በዝርዝር በጥቂቱ!

    Print       Email
0 0
Read Time:47 Second

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ የነበሩት ኢንጂነር አዜብ አስናቀ ክስ ተመሰረተባቸው።

በዚህ የክስ መዝገብ የቀድሞ የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ምክትል ዋና ዳይሬክተር የነበሩት ኮሎኔል ሙሉ ወልደ ገብርኤልን ጨምሮ 50 ሰዎች ይገኙበታል።

Image may contain: 1 person, sitting

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን የታላቁ ህዳሴ ግድብ ውሃ የሚያርፍበት 123,189 ሄክታር ስፋት የሪዘርቬየር ክሊሪንግና ባዮማስ ዝግጅት ስራ ደኖችን የመመንጠር፣ የማጽዳትና ከአካባቢው (ከግድቡ አርቆ) ወደ ተዘጋጀለት ቦታ የማጓጓዝ ሥራን ለመስራት ከኢፌዴሪ ብረታብረትና ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን ጋር የተጨማሪ እሴት ታክስን ሳይጨምር በብር 5,158,611,599.03 (አምስት ቢሊዮን አንድ መቶ አምሳ ስምንት ሚሊዮን ስድስት መቶ አስራ አንድ ሺ አምስት መቶ ዘጠና ዘጠኝ ከ ዜሮ ሦስት) በተዋዋሉት ውል መሠረት ስራው መጠናቀቅ በሚገባው ጊዜ መጠናቀቁን ባለመቻሉ ከፍተኛ መጠን ያለው የመንግስት ገንዘብ እንዲባክንና ጉዳት እንዲደርስ ያደረጉ በመሆኑ ሁሉም ተከሳሾች በዋና ወንጀል አድራጊነት ተካፋይ በመሆን ተከሳሾች በፈፀሙት በስልጣን አላግባብ መገልገል፣ አንዳንዶቹ የማይገባ ጥቅም ለራሳቸው ለማግኘት ወይም ለማስገኘት በማሰብ እና ሃላፊነታቸውን በመጠቀም ከባድ የሙስና ወንጀል ተከሰዋል፡፡

ኢንጂነር አዜብ አስናቀ በነሐሴ ወር 2010 ዓ.ም ከሀላፊነታቸው መነሳታቸው ይታወሳል።
ምንጭ፦ አቃቤ ህግ

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 5 years ago on December 27, 2019
  • By:
  • Last Modified: December 27, 2019 @ 10:53 am
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar