0
0
Read Time:39 Second
በትላንትናው እለት በዋሽንግተን ዲሲ የተመረቀውን የፌስቡክ አርበኞች የተሰኘውን ድራማ ላይ በዋና ተዋናይነት ከሚሳተፉበት ውስጥ አንዷ የሆነችው አንጋፋዋ አለምጸሃይ ወዳጆ በምርቃቱ ስነ ስርአት ላይ በተገኙት ማህበረሰቦች ፊት ለፊት አለምጸሃይ ወዳጆ መሸለሟን ተገልጿል።
በቴዎድሮስ ለገሰ ፣ በረዳት አማካሪ ፍሬህይወት መለሰ እና ማሩ አበበ የተዘጋጀው ይህ ዝግጅት በሙዚቃው አለም እና በቴአትር አለም ውስጥ እውቅና ያላቸው ሰዎች እንደተሳተፉበት ተገልጿል።
ይህንን ዝግጅት ለመመረቅ ከአዲስ አበባ ወደ ዋሽንግተን ዲሲ የተገኘችው የናሁ ቴሌቪዥን ባልደረባ እና (አስተዳደር ሃላፊ) እንዳለችው ከሆነ የአለምጸሃይ ወዳጆን የቤት ችግር መኖሯን ያወቅነው ባለፈው አመት ወደ ኢትዮጵያ በመጣችበት ወቅት የት እንዳለች ስናጣራ በሸራተን ሆቴል እንዳረፈች እና ምንም የመኖሪያ ቤት በአዲስ አበባ እንደሌላት የናሁ ቲቪ ባለቤት በሰማበት ወቅት ከጎ ትራቭል እህት ድርጅት ጋር በመሆን ይህንን ሽልማት እንዲሰጣት ወስነዋል ብላለች።
በዚህም ሁኔታ ሲጠበቅ በነበረው በዚህ ዝግጅት ላይ ሽልማቱን የሰጧት ሲሆን ቤቱ በቦሌ ክፍለ ከተማ ፒኮክ አካባቢ እንደሚገኝም አክላ ገልጻለች።
Wondering where the comments are? We encourage you to use the share buttons below and start the conversation on your own!
- Click to email a link to a friend (Opens in new window)
- Click to share on Facebook (Opens in new window)
- Click to share on Twitter (Opens in new window)
- Click to share on LinkedIn (Opens in new window)
- Click to share on Pinterest (Opens in new window)
- Click to share on Tumblr (Opens in new window)
- Click to print (Opens in new window)
Average Rating