በወልዲያ አርሴማ ጸበል ለመጸበል ሄዶ በዚያው ላይመለስ ያመለጠው አርቲስት ፍቃዱ ተክለ ማርያም ፣ በኩላሊት ህመም ሲሰቃይ እንደነበር የሁላችንም ትውስታ የሁላችንም ህመም ሆኖ እንደነበር ይታወሳል። በዚህም ወቅት የወገን ደራሽ ወገን ነው በሚል ፣ በቴዎድሮስ ተሾመ እና በወንድሙ ሙሉቀን ተሾመ በኩል የተከፈተ የጎ ፈንድሚ አካውንት እንደነበር እና ከመጠን በላይ ገንዘብ ተሰብስቦ ፣ ለታማሚ ለነበረው አርቲስት ፍቃዱ ተክለማርያም ይሰጣል ተብሎ የታሰበው ገንዘብ ፣ በተባለበት ወቅት እና ጊዜ ሳይሰጥ ፣ ለእረጂም ጊዜ ከመቆየቱም ባሻገር ፣ በፍቃዱ ህይወት ላይ ያገባኛል የሚል ሃሳብ ይዘው የመጡትን አርቲስቶች ከእነ መሰረት መብራቴ ጋርም ጸብን ያጫረ ከፍተኛ ሽኩቻም እንደነበር ይታወሳል።
በፍቃዱ ተክለማርያም
ለመጀመሪያ ጊዜ የመሪ ተዋናይነት ሚና ያገኘው በአባተ መኩሪያው “እሳት ሲነድ” ነበር። ከዛ በኋላ በበርካታ ቴአትሮች ላይ ተሳትፏል። እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ የጥበብ ቤቱ ከነበረው ብሔራዊ ቴአትር አይጠፋምም ነበር።
ፍቃዱ እጅግ ገናና ከሆነበት “ቴዎድሮስ” ቴአትር በተጨማሪ በ”ኤዲፐስ ንጉስ”፣ “ሐምሌት” እና “ንጉስ አርማህ” ተውኔቶችም እንደ ንጉስ ተጫውቷል።
አዲስ አባባ አራት ኪሎ አካባቢ ተወልዶ ያደገው ፍቃዱ መነሻው ቴአትር ቢሆንም በተከታታይ የቴሌቭዥን ድራማዎች፣ በፊልሞች እንዲሁም በማስታወቂያ ሥራዎቹ እና በሬድዮ ትረካዎችም ጭምር ይታወቃል።
ከተወነባቸው የቴሌቭዥን ድራማዎች መካከል “ባለጉዳይ”፣ “ያልተከፈለ እዳ”፣ “የአበቅየለሽ ኑዛዜ”፣ ”ገመና” ይጠቀሳሉ። ማህበራዊ ትችት አዘሉ “ባለጉዳይ” በቴሌቭዥን ይተላለፍ በነበረበት ወቅት ተመልካቾች ‘ብሶታችንን አደባባይ አወጣልን’ ይሉ እንደነበር ይታወሳል።
በኢትዮጵያ ራድዮ ይተላለፍ የነበረው “ከመጻሕፍት አለም” ላይ ያቀርባቸው በነበሩ ትረካዎች በርካታ መጻሕፍት ላይ ህይወት ዘርቷል። “ሞገደኛው ነውጤ”፣ “ጥቁር ደም”፣ “ሳቤላ”፣ “ወንጀለኛው ዳኛ” እና “ግራጫ ቃጭሎች” ከተረካቸው መጻሕፍት መካከል ይጠቀሳሉ።
በአበራ ለማ የተጻፈው “ሞገደኛው ነውጤ” ላይ ያለው ነውጤ የተሰኘው ገጸ ባህሪ ከብዙዎች ሕሊና አይጠፋም። ብዙዎች ነውጤን ሲያስቡ ፍቃዱ ትውስ ይለቸዋል። የሀዲስ አለማየሁ “ወንጀለኛው ዳኛ”ም ፍቃዱ ከሚታወስባቸው ስራዎች ይገኝበታል።
ገንዘቡን በውል ሳይሰጡ ቆይተው እስከዛሬ ድረስ የተደበቀ ሚስጥር የሖነው ይሄው የደባ እንቅስቃሴ ዛሬ ላይ ይፋ (ገሃድ ወጥቷል) ።
መረጃ ቁጥር፡አንድ፡
ለበፍቃዱ፡ተክለማያም፡የህክምና፡ የወጭ መሸፈኛ ጎፈንድሚ እንዲከፈት ሲደረግ ቦርዱ ከመስማማቱ ቀደም ብሎ አሜሪካ በሚገኘው የቴዎድሮስ ተሾመ ወንድም ሙሉቀን ተሾመ የባንክ አካውንት እንዲከፈት ተደርጓል።
መረጃ ቁጥር ሁለት
ገንዘቡ ከተሰበሰበ ጊዜ ጀምሮ በፍቃዱም በህይወት እያለም ሆነ ሳይኖር ለእረጂም ግዜያት ከፍተኛ ክርክር አስነስቶ በህዝብ ዘንድ እና በሚዲያ ጭምር ቴዎድሮስ ተሾመ እንዲወቀስ የተደረገ ቢሆንም ይህንን ሁኔታ ለመከታተል በተደረገ ጥረት የተከፈለውን ገንዘብ አንድ አራተኛ በማይሞላ ገንዘብ ሰጥቶ አፋቸውን እንዳዘጋቸው ሪፖርቶች ገልጸዋል።
መረጃ ሦስት
የገንዘቡን መጠን እየታወቀ ያለ አግባብ መጭበርበር ምክንያት በሰው ደም ሃብት ለማጋበስ መሞከራቸው ይታወቃል። ሆኖም ሙሉቀን ተሾመ ወደ አሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ አካባቢ ከመጣ ጊዜ ጀምሮ ስራ በቅጡ ሰርቶ የማያውቅ ሲሆን፣ ከ፫ ሲን የማይበልጥ የፊልም ስራ ላይ ከሰነሰለት ድራማ ጋር መሳተፉ የሚታወስ ነው ። ይህ በእንዲህ እንዳለ ከሰሞኑ እየተነገረ የመጣው ነገር አስገራሚ ሆኖ መጥቷል።
የዚህም ዋና ፍሬ ነገር ፣ ሙሉቀን እና ቴዎድሮስ ተሾመ በጋራ በመሆን ከጀርባቸው ተዋናይት የነበረችውን እና በአሁን ሰአት በአሜሪካ በምግብ ቤት በመስተንግዶ ስራ የምትሰራውን ረቂቅ ተሾመን ስም በማስገባት ሉሲ የተባለውን ምግብ ቤት በቅርቡ እንደሚከፍቱ እየተነገረ ይገኛል።
አንዳንድ ምንጮቻችን እንደገለጹልን ከሆነ ሉሲ የተሰኘውም የምግብ ቤት ባለቤት ፣ የምግቤቱ ያለበት ቦታ ለኢንቨስትመንት ስለተፈለገ ለቀጣዩ አመታት መስራት እንደማይችል ስለአወቀ ቁልፉን ሸጦላቸዋል፣ ሲሉ በሌላም በኩል ደግሞ ሌሎች ምንጮቻችን እንደሚሉት ከሆነ በፍቃዱ በተሰበሰበ ገንዘብ ሙሉ በሙሉ ነው የገዙት ፣ በዚህም ምክንያት የፍቃዱ መታሰቢያ ምግብ ቤት ሊባል ይችላል ሲሉ ተናግረዋ።
በሌላም መልኩ በምግብ ዝርዝር ላይ “ኩላሊት” የሚል የምግብ ዝርዝር ይጨመርበት ሲሉ በዲሲ እና አካባቢዋ የሚገኙ ማህበረሰቦች በቴዎድሮስ እና ሙሉቀን ተሾመ ላይ ሲያሾፉ ይሰማሉ።
በሌላም በኩል በእነ አለምጸሃይ ወዳጆ ጀርባ የሚወራው ወሬ ግን ረቂቅ ተሾመ ምግብ ቤቱን ልትከፍት እንደሆነ የሚወራ ሲሆን ፣ አንዳንድ አስተያየት ሰጭዎች ግን የሚሰጡት ገንቢ አስተያየት ፣አስር አመት እንኳን በአሜሪካ ያልኖረች አንድ ግለሰብ በአምስት አመታት ውስጥ አምሳ ሽህ የአሜሪካን ዶላር በጥሬ ገንዘብ ለማስያዣ እንኳን መስራት በማትችልበት ሃገር ላይ እንዴት አድርጋ የቤቱ ቁልፍ ከሚሸጥበት ዋጋ ሃያ በመቶ ልትከፍል ትችላለች ?
ይህ ክፍያ በጥሬ ገንዘብ የሚከፈል ሲሆን ሌላውን በወለድ እዳ ገብታም ልትከፍል የምትችልበት አጋጣሚ ይኖትራል ፣ ስለዚህ ከጀርባ የተቀመጠ ሰው አለ ሲሉ ጥርጣሬአቸውን ያጎሉታል።
ለዚህም ሲባል ቴዎድሮስ ተሾመ እና ረቂቅ ተሾመ ባላቸው የረቀቀ ግንኙነት እርሷን እንደባለቤት በማድረግ ከዚያም ሙሉቀን ተሾመን ደግሞ የስራ ባልደረባ እና የገንዘብ ተጋሪ በማድረግ እንዲከፈት አድርገዋል ሲሉ ገልጸዋል።
ሆኖም በአሁን ሰአት ረቂቅ ተሾመ ወደ አዲስ አበባ በማቅናት የተለያዩ የምግብ ቤት ቁሳቁሶችን ለማምጣት እንደሄደች ምንጮቻችን አክለው ነግረውናል።
«አስተያየታችሁን ጻፉልን ፣ የተሟላ መረጃ እስክናገኝ ድረስ ሃሳባችሁን አጋሩን»
Average Rating