አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፀረ-ፕላጃሪዝም (Anti-Plagiarism) ፖሊሲ ከየካቲት 22/2012 ዓ.ም ጀምሮ ሊተገብር መሆኑን በይፋ እየገለጸ ይህ ፖሊሲ ተግባራዊ የሚሆን ሲሆን በፖሊሲው መሰረት ከዚህ በኋላ ማንኛውም መመረቂያ ጽሁፍ (Thesis/Dissertation) በኧርከንድ (URKUND) ሶፍትዌር አማካኝነት ተመርምሮ ከፕላጃሪዝም ነፃ መሆኑ ሳይረጋገጥ ዲግሪ እንደማይሰጥ ያሳውቃል፡፡
ፕላጃሪዝም አንድ የምረቃ ፅሁፍ የሚያዘጋጅ ወይም የምርምር ስራ የሚሰራ ሰው ሌሎች ሰዎች የሰሩትን ስራ የራሱ እንደሆነ አድርጎ በመውሰድ የአካዳሚክ እና የምርምር ሕግጋትን በመጣስ የሚፈፅመው ሕገወጥ ተግባር ነው፡፡
ፕላጃሪዝም ተማሪዎች የመመረቂያ ጽሁፍ በሚያዘጋጁበት ጊዜ በራሳቸው ጥረት እና ልፋት የራሳቸው የሆነ (original) ስራ ሰርተው እንዳያቀርቡ በማድረግ ዩኒቨርሲቲው ጥራትን ለማረጋገጥ በሚያደርገው ጥረት ላይ ትልቅ ጉዳት ሲያደርግ የቆየ ሕገወጥ ተግባር ነው፡፡ ቀደም ሲል የዩኒቨርሲቲው ሴኔት ፕላጃሪዝም በመጠቀም የመመረቂያ ጽሁፉን በማዘጋጀት 2ኛ ዲግሪ ወስዶ ከነበረ ተማሪ ላይ ድርጊቱ በማስረጃ በማረጋገጡ በሴኔት ሕጉ መሰረት ዲግሪው እንዲነጠቅ አድርጓል፡፡ ስለሆነም ዩኒቨርሲቲው ይህ ችግር በመማር ማስተማሩና በምርምር ስራ ላይ በየጊዜው እያስከተለ ያለው አሉታዊ ተፅእኖ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን በመገንዘቡ የፀረ-ፕላጃሪዝም ፖሊሲ ማውጣት አስፈላጊ ሆኖ አግኝቶታል፡፡ በመሆኑም ይህ ፖሊሲ ተግባራዊ ሲሆን ችግሩ ከሞላ ጎደል ይቃለላል የሚል ሙሉ እምነት አለው፡፡
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ
ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት
Wondering where the comments are? We encourage you to use the share buttons below and start the conversation on your own!
- Click to email a link to a friend (Opens in new window)
- Click to share on Facebook (Opens in new window)
- Click to share on Twitter (Opens in new window)
- Click to share on LinkedIn (Opens in new window)
- Click to share on Pinterest (Opens in new window)
- Click to share on Tumblr (Opens in new window)
- Click to print (Opens in new window)
Average Rating